TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ማስተካከያ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬ 'ደጎል አደባባይ' ተብሎ በሚጠራው አካባቢ "ፖሊስ ፈንጂ አመከነ" በሚል የተሰራጨው መረጃ 'ስህተት' መሆኑን ማምሻውን አሳውቋል።

ፖሊስ አረጋግጥኩት ባለው መሰረት ቦታው የነበረ በላስቲክ የተሞላ 'ድራፍት ቢራ' እንጂ 'ፈንጂ' አለመሆኑን ህብረተሰቡ እዲገነዘብ ብሏል።

የአ/አ ፖሊስ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

* ከቲክቫህ አባላት ሁኔታውን በሚመለከት የሰጡት መረጃም ተነስቷል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ከ30,000 ለሚልቁ የጦር እና የብሄራዊ አገልግሎት አባላቷ የኮቪድ-19 ክትባት መስጠቷን አስታወቀች፡፡

ክትባቱ አባላቱን ከወረርሽኙ ለመጠበቅ ወሳኝ ነው ተብሏል፡፡

ዩኤኢ በቻይናዊው መድኃኒት አምራች "ሲኖፎርማር" የተዘጋጀው የኮቪድ -19 ክትባት የምዕራፍ 3 ሙከራ በሃገሯ ከተካሄደ በኋላ በተወሰነ መልኩ ክትባቱ ግልጋሎት ላይ እንዲውል ፈቅዳለች፡፡

ከዚያ ወዲህ ክትባቱ "ግንባር ቀደም ተጋላጭ" የሆኑ የህክምና፣ የፖሊስ አባላትን እና ከፍተኛ ባለስልጣናትን እንዲሁም የዱባይ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ገዥ ሼክ መሀመድ ቢን ራሺድን ጨምሮ ለሃገሪቱ የካቢኔ አባላት ተሰጥቷል እንደ ዘ ናሽናል ዘገባ፡፡

Via AlAin News
@tikvahethiopiaBOT @tikahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
'ህወሓት ለጥቃቱ ኃላፊነት ወሰደ' "ህወሓት" ትላንትና ምሽት በኤርትራ አስመራ ከተማ የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን አረጋግጧል። ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ፥ የአስመራ ኤርፖርትን ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈፀማቸውን ዛሬ "ለሮይተርስ" ተናግረዋል። በትላንት ምሽቱ ጥቃት ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር እስካሁን አልታወቀም። * የኤርትራ መንግስት እስካሁን ይፋዊ መረጃ አልሰጠም። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

የስፔን መንግስት በኤርትራ (አስመራ ከተማ) ላይ ህወሓት 'ፈጽሞታል' የተባለውን የአየር ጥቃት ማውገዙን ዶቼ ቨለ አስነብቧል።

የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና ሕገ-መንግሥታዊ ተቋማት የሚያከብር መፍትሔ እንዲፈለግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

የስፔን መንግስት ቀውሱ ከመባባስ እንዲገታ ጠይቋል።

ስፔን የአፍሪካ ህብረት እና የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የሚወስዱትን እርምጃ እንደምትደግፍ አስታውቃለች።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#የፌዴራል_ፖሊስ_ማሳሰቢያ

በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፈንታ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የተናገሩት ፦

"በአዲስ አበባ እያየን ያለነው በጣም ብዙ የጦር መሳሪያዎች በጆንያ ፣ በፌስታል የተጠቀለሉ እየተጣሉ ናቸው።

የጦር መሳሪያ ስንል ተተኳሽ #ፈንጂዎችን ጭምር ፣ ቦንብ ሌሎች ፈንጂዎች እንዲሁም ክላሽ ፣ ሽጉጥ የመሳሰሉት በተለይ በጋራ የመኖሪያ ቤቶች ፣ በድልድዮች ፣ በመሃል ከተማ ፣ በመንገድ ጋር እየተጣሉ ይገኛሉ።

ይህም የፍተሻው እና የቁጥጥር ስራው እየተጠናከረ በሚመጣበት ጊዜ ወንጀለኞችን ከነጦር መሳሪያው በቁጥጥር ስር ውለው ስለሚመረመሩ እነኚህ አፍራሽ ኃይሎች ተደርሶብናል በማለት የጦር መሳሪያዎችን እየወረወሩ ይገኛሉ።

አሁንም በዚህ የሚጠረጠሩ እና ችግር ይፈጥራሉ ተብለው የሚታሰቡ አካላትን ህብረተሰቡ መጠቆም መቻል አለበት።"

PHOTO : YRD (AA TikvahFamily)
@tikvahethiopiaBOT @Tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,213
• በበሽታው የተያዙ - 336
• ህይወታቸው ያለፈ - 12
• ከበሽታው ያገገሙ - 264

አጠቃላይ 103,056 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,581 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 64,130 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

308 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'ቲክቫህ ኢትዮጵያ'

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በመጪዎቹ ቀናት ድረ ገፁን ይፋ ያደርጋል።

በመላው ሀገሪቱ ያሉ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ አባላት በወረዳ ደረጃ መረጃ ይለዋወጣሉ ፤ የፀጥታ ስጋት ካለም ያሳውቃሉ።

እንዲሁም አባላቶቻችን በየሚሰሩበት ተቋም፣ በሚማሩባት ተቋም፣ በሚኖሩበት አካባቢ የሚደርስባቸውን ማንኛውም አይነት ችግር ያሳውቃሉ።

1. አባላት ያላቸውን መረጃ ወይም ጥቆማ ይፋ ሲያደርጉ ማንነታቸው ለሌሎች አይታይም፤ አይገለፅም።

2. መረጃውን ወይም ጥቆማውን የሚያዩት ፤ ማረጋገጫ እና ቅቡልነቱን የሚያረጋግጡት የዛው ወረዳ ነዋሪዎች ብቻ ናቸው።

በየወረዳው ያለው መረጃዎች፣ጥቆማ እውነተኛ እና በአባላት ቅቡልነት ሲኖረው በዋናው ገፅ @tikvahethiopia ይፋ ይደረጋል።

ከዚህ በተጨማሪም የቲክቫህ አባላት "ቤተሰባዊ ግንኙነት" ከመቼውም ጊዜ በላይ እስከ ታች የሚዘረጋበት እና የበጎ አድራት ስራዎች እና ለወጣቶች ስራ እድሎችን የማመቻቸት ተግባራት የሚጠነክርበት ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

ህዳር 7/2013 ዓ/ም
ቲክቫህ ኢትዮጵያ

@tikvahethiopiaBot
#FDREDefenseForce

ዛሬ ማክሰኞ ከረፋዱ 5:30 ጀምሮ "ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ" በሚል ርእስ የሁለት ደቂቃ ፕሮግራም ይካሄዳል።

ኢትዮጵያውያን በያሉበት ለአንድ ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ አድርገው በመቆም ለመከላከያቸው ያላቸውን ክብር ይገልጣሉ።

ለ1 ደቂቃ የመቆም ሥርዓቱ ሲጠናቀቅ በቀጣዩ አንድ ደቂቃ ባሉበት ሆነው ባለማቋረጥ ያጨበጭባሉ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ 'ጎረቤት ሀገራት' የሚሰደዱ ወገኖችን ለመቀበልና ወደ ቀያቸው ለመመለስ መንግስታቸው ዝግጁ መሆኑን አሳውቀዋል።

መንግስት የተሰደዱ ንጹሃን ዜጎችን ንብረታቸውን ለመጠበቅ ፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ እና ሲመለሱ ሰላማቸውን ለማስጠበቅ ዝግጁ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
'የንፁሃን ዜጎቻችን ስደት'

ዛሬ ድረስ ባለው ሪፖርት መሰረት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ሸሽተው ወደ ሱዳን የገቡ ሰዎች ከ25,000 አልፈዋል።

UNHCR እና አጋሮቹ እገዛ ለማድረግ እየሰሩ የሚገኝ ሲሆን "ሃምዳያት" አካባቢ ያሉ የሱዳን ማህበረሰቦችም ምግብ እና የሚጠጣ እያቀረቡ ነው።

* እየተደረገ ያለው እገዛ ግን አሁንም በቂ አያደለም ፤ ያለው ሁኔታ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግርኛ መልዕክት ፦ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፥ የትግራይ ክልል ልዩ ሃይል እና የፀጥታ አካላት ከቀናት ያልበለጠ ዕድሜ ለሌለው ቡድን ሲሉ ህይወታቸው እንዳያጡ ጥሪ አቀረቡ። የትግራይ ልዩ ሃይል እና የፀጥታ አካላቱ እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት በመስጠት በሚቀጥሉት 2 እና 3 ቀናት ራሳቸውን እንዲያድኑ ጥሪ አቅርበዋል። የትግራይ ህዝብም ልጆቹን እየቀበረ ለሚገኘው 'ሃይል' ሲል…
#DrAbiyAhmed

የትግራይ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ ለመከላከያ እጃቸውን በመስጠት ራሳቸውን እና ሕዝቡን እንዲያድኑ የተሰጠው የ3 ቀን የጊዜ ገደብ ዛሬ መጠናቀቁን ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አስታወቁ።

ዶ/ር አብይ፥ በዚህ ጥሪ የተጠቀሙ የትግራይ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ አባላት ፣ ለወሰዱት ኃላፊነት የተሞላው ሕዝባቸውን የማዳን ውሳኔ ይመሰገናሉ ብለዋል።

የተሰጠው የጊዜ ገደብ ስለተጠናቀቀ በቀጣይ ቀናት "የመጨረሻው ሕግ የማስከበር" ወሳኝ ተግባር ይከናወናል ሲሉ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ ፦

"ኢሰመጉ" በትግራይ ክልል እና አዋሳኝ አካባቢዎች ያለው የጦርነት እንቅስቃሴ የሰላማዊ ሰዎችን ደህንነት እና ሰብዓዊ መብቶቻቸውን ከፍተኛ አደጋ ላይ የጣለ መሆኑ ከፍተኛ ሥጋት እንዳሳደረበት ገልጿል።

ማንኛውም የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ ያገኛቸው መብቶች በሰላማዊም ሆነ በጦርነት ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ መሆናቸው የማይቀርና የሕግ ተጠያቂነትም ያለበት ነው ብሏል።

በመሆኑም፣ በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም ወገኖች በጦርነቱ በቀጥታ ተሳታፊ ያልሆኑና ያልታጠቁ ንጹኃን ሰዎችን ደህንነትና ሰብዓዊ መብቶች የመጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸው አሳስቧል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BREAKING

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ 34 "የሕወሓት የፋይናንስ ተቋማትን" ማሳገዱን ገለፀ።

- ሱር ኮንስትራክሽን ፣
- ጉና የንግድ ስራዎች ፣
- ትራንስ ኢትዮጵያ፣
- መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ ፣
- ሠላም የህዝብ ማመላለሻ ማህበር ፣
- ሜጋ ማተሚያ፣
- ኢፈርት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
- ኢፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ እገዳ ከተጣለባቸው ተቋማት መካከል እንደሚገኙበት ኢቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

"ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ" በሚል ዛሬ ረፋድ 5:30 በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት አሳይተዋል።

ተጨማሪ @tikvahethmagazine ማግኘት ትችላላችሁ።

@TIKVAHETHIOPIA @TIKVAHETHIOPIABOT
TIKVAH-ETHIOPIA
'የንፁሃን ዜጎቻችን ስደት' ዛሬ ድረስ ባለው ሪፖርት መሰረት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ሸሽተው ወደ ሱዳን የገቡ ሰዎች ከ25,000 አልፈዋል። UNHCR እና አጋሮቹ እገዛ ለማድረግ እየሰሩ የሚገኝ ሲሆን "ሃምዳያት" አካባቢ ያሉ የሱዳን ማህበረሰቦችም ምግብ እና የሚጠጣ እያቀረቡ ነው። * እየተደረገ ያለው እገዛ ግን አሁንም በቂ አያደለም ፤ ያለው ሁኔታ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው። @tikvahethiopia…
#UPDATE

ትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ሸሽተው ወደ ሱዳን የገቡ ሰዎች ከ30,000 ማለፋቸውን UNHCR ዛሬ ለቢቢሲ አሳውቋል።

ከቀን ወደ ቀን ቁጥሩ እየጨመረ መሄዱንም ገልጿል።

የUNHCR ድንገተኛ ምላሽ አስተባባሪ ጀንስ የሆኑት ሄዝማን በአካባቢው የሰብዓዊ ቀውስ መባባሱን ገልፀው ፤ ሁኔታው "አስጊ ነው" ብለውታል።

በድንጋጤ የተዋጡ እና እራፊ ጨርቅ ብቻ ላያቸው ላይ ጣል ያደረጉና በፍርሃት የተሞሉ ተፈናቃዮች ወደ ሱዳን ያቀኑ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት ታዳጊዎች ናቸው።

UNHCR እንደገለፀው ትላንት ብቻ 2300 አዲስ ተፈናቃዮች ሱዳን ገብተዋል ፤ ከትናንት በስቲያ ደግሞ ከ5000 በላይ አዲስ ተፈናቃዮች ሱዳን መግባታቸውን ለቢቢሲ አሳውቋል።

@TIKVAHETHIOPIA @TIKVAHETHIOPIABOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ 34 "የሕወሓት የፋይናንስ ተቋማትን" ማሳገዱን ገለፀ። - ሱር ኮንስትራክሽን ፣ - ጉና የንግድ ስራዎች ፣ - ትራንስ ኢትዮጵያ፣ - መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ ፣ - ሠላም የህዝብ ማመላለሻ ማህበር ፣ - ሜጋ ማተሚያ፣ - ኢፈርት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር - ኢፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ እገዳ ከተጣለባቸው ተቋማት መካከል እንደሚገኙበት…
#UPDATE

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የባንክ ሂሳባቸውን ያገደባቸው ድርጅቶች ዝርዝር ከላይ በምስሉ የምትመለከቷቸው ናቸው።

የድርጅቶቹ የባንክ ሂሳብ ለምን ታገደ ?

በተጠረጠሩባቸው ሶስት ወንጀሎች ምርመራ ጋር በተያያዘ ነው።

ድርጅቶች ከተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች መካከል በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የሚፈጸሙ የዘር ተኮር ጥቃቶችን ፣ የሽብር ተግባራት እና የሕገ መንግስታዊ ስርዓትን በኃይል ለመናድ ከሚሰሩ አካላት ጋር በመመሳጠር እና ግንኙነት በመፍጠር በገንዘብ መደገፍ የሚል ይገኝበታል።

የታገዱት ድርጅቶች "በሙስና እና በወንጀል ድርጊት" የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀሎች ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የጠቅላይ አቃቤ ህግ አሳውቋል።

Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር (የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ)
@TIKVAHETHIOPIA @TIKVAHETHIOPIABOT
ችሎት !

ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው በዋስ ከእስር እንዲፈታ መወሰኑን 'አውሎ ሚዲያ' በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ክልል'

ከ "ሕወሓት ነፃ" በሆኑ አካባቢዎች የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መዋቅሩን እንደሚያደራጅ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ገለፁ።

ዶ/ር ሙሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ "ዋና ሥራ አስፈጻሚው የፕሬዚዳንቱን ሥራ ስለሚሠራ ክልሉ ሙሉ ለሙሉ ነፃ ሲወጣ መንግሥታዊ ሥራውን ተክቶ ይሰራል" ብለዋል።

በዚህ መሠረትም የክልሉን ካቢኔ እንደሚያደራጅ እና የዞን አስተዳዳሪዎችን እንደሚሾም ገልጸዋል።

የወረዳ እና የቀበሌ ምክር ቤቶች ደግሞ ባሉበት እንዲቀጥሉ የሚደረግ መሆኑን አመልክተዋል።

ሥራ አስፈጻሚውን አካል እንደሚመራ ፣ እንደሚያስተባብር እንዲሁም የክልሉን ዕቅድ እና በጀት እንደሚያጸድቅ ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#AddisAbabaPolice

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በአራዳ ክፍለ ከተማ በልመና ስራ በሚተዳደሩ አንዲት ግለሰብ ቤት ውስጥ ከ45 ሺህ ብር በላይ መገኘቱን ገለፀ፡፡

በአ/አ "በርሜል ሙሉ ገንዘብ ተከማችቶ ተገኘ" በሚል በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች እየተላለፈ ያለው መረጃ #የተሳሳተ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታዉቋል፡፡

* የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው ዝርዝር መረጃ ከፎቶ ጋር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia