#UPDATE
ትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ሸሽተው ወደ ሱዳን የገቡ ሰዎች ከ30,000 ማለፋቸውን UNHCR ዛሬ ለቢቢሲ አሳውቋል።
ከቀን ወደ ቀን ቁጥሩ እየጨመረ መሄዱንም ገልጿል።
የUNHCR ድንገተኛ ምላሽ አስተባባሪ ጀንስ የሆኑት ሄዝማን በአካባቢው የሰብዓዊ ቀውስ መባባሱን ገልፀው ፤ ሁኔታው "አስጊ ነው" ብለውታል።
በድንጋጤ የተዋጡ እና እራፊ ጨርቅ ብቻ ላያቸው ላይ ጣል ያደረጉና በፍርሃት የተሞሉ ተፈናቃዮች ወደ ሱዳን ያቀኑ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት ታዳጊዎች ናቸው።
UNHCR እንደገለፀው ትላንት ብቻ 2300 አዲስ ተፈናቃዮች ሱዳን ገብተዋል ፤ ከትናንት በስቲያ ደግሞ ከ5000 በላይ አዲስ ተፈናቃዮች ሱዳን መግባታቸውን ለቢቢሲ አሳውቋል።
@TIKVAHETHIOPIA @TIKVAHETHIOPIABOT