'ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ክልል'

ከ "ሕወሓት ነፃ" በሆኑ አካባቢዎች የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መዋቅሩን እንደሚያደራጅ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ገለፁ።

ዶ/ር ሙሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ "ዋና ሥራ አስፈጻሚው የፕሬዚዳንቱን ሥራ ስለሚሠራ ክልሉ ሙሉ ለሙሉ ነፃ ሲወጣ መንግሥታዊ ሥራውን ተክቶ ይሰራል" ብለዋል።

በዚህ መሠረትም የክልሉን ካቢኔ እንደሚያደራጅ እና የዞን አስተዳዳሪዎችን እንደሚሾም ገልጸዋል።

የወረዳ እና የቀበሌ ምክር ቤቶች ደግሞ ባሉበት እንዲቀጥሉ የሚደረግ መሆኑን አመልክተዋል።

ሥራ አስፈጻሚውን አካል እንደሚመራ ፣ እንደሚያስተባብር እንዲሁም የክልሉን ዕቅድ እና በጀት እንደሚያጸድቅ ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia