TIKVAH-ETHIOPIA
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግርኛ መልዕክት ፦ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፥ የትግራይ ክልል ልዩ ሃይል እና የፀጥታ አካላት ከቀናት ያልበለጠ ዕድሜ ለሌለው ቡድን ሲሉ ህይወታቸው እንዳያጡ ጥሪ አቀረቡ። የትግራይ ልዩ ሃይል እና የፀጥታ አካላቱ እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት በመስጠት በሚቀጥሉት 2 እና 3 ቀናት ራሳቸውን እንዲያድኑ ጥሪ አቅርበዋል። የትግራይ ህዝብም ልጆቹን እየቀበረ ለሚገኘው 'ሃይል' ሲል…
#DrAbiyAhmed

የትግራይ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ ለመከላከያ እጃቸውን በመስጠት ራሳቸውን እና ሕዝቡን እንዲያድኑ የተሰጠው የ3 ቀን የጊዜ ገደብ ዛሬ መጠናቀቁን ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አስታወቁ።

ዶ/ር አብይ፥ በዚህ ጥሪ የተጠቀሙ የትግራይ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ አባላት ፣ ለወሰዱት ኃላፊነት የተሞላው ሕዝባቸውን የማዳን ውሳኔ ይመሰገናሉ ብለዋል።

የተሰጠው የጊዜ ገደብ ስለተጠናቀቀ በቀጣይ ቀናት "የመጨረሻው ሕግ የማስከበር" ወሳኝ ተግባር ይከናወናል ሲሉ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia