'ቲክቫህ ኢትዮጵያ'

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በመጪዎቹ ቀናት ድረ ገፁን ይፋ ያደርጋል።

በመላው ሀገሪቱ ያሉ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ አባላት በወረዳ ደረጃ መረጃ ይለዋወጣሉ ፤ የፀጥታ ስጋት ካለም ያሳውቃሉ።

እንዲሁም አባላቶቻችን በየሚሰሩበት ተቋም፣ በሚማሩባት ተቋም፣ በሚኖሩበት አካባቢ የሚደርስባቸውን ማንኛውም አይነት ችግር ያሳውቃሉ።

1. አባላት ያላቸውን መረጃ ወይም ጥቆማ ይፋ ሲያደርጉ ማንነታቸው ለሌሎች አይታይም፤ አይገለፅም።

2. መረጃውን ወይም ጥቆማውን የሚያዩት ፤ ማረጋገጫ እና ቅቡልነቱን የሚያረጋግጡት የዛው ወረዳ ነዋሪዎች ብቻ ናቸው።

በየወረዳው ያለው መረጃዎች፣ጥቆማ እውነተኛ እና በአባላት ቅቡልነት ሲኖረው በዋናው ገፅ @tikvahethiopia ይፋ ይደረጋል።

ከዚህ በተጨማሪም የቲክቫህ አባላት "ቤተሰባዊ ግንኙነት" ከመቼውም ጊዜ በላይ እስከ ታች የሚዘረጋበት እና የበጎ አድራት ስራዎች እና ለወጣቶች ስራ እድሎችን የማመቻቸት ተግባራት የሚጠነክርበት ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

ህዳር 7/2013 ዓ/ም
ቲክቫህ ኢትዮጵያ

@tikvahethiopiaBot