TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በእነ አቶ #ጌታቸው_አሰፋ መዝገብ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ የተደረገላቸው አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ አፅበሃ ግደይ፣ አሰፋ በላይና ሲሻይ ልዑል በጥሪው መሰረት ባለመቅረባቸው ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የወንጀል ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው ችሎት አቃቤ ሕግ ካሉት ምስክሮች 29ኙ የሕግ ምስክሮች ጥበቃ እንዲደረግላቸው ያቀረበውን አቤቱታ በወቅቱ ችሎቱ ለዳኞች ብቻ ጥበቃ ትዕዛዝ ቢሰጠም ሕጉ ይህን ስለማይፈቅድ ስም ዝርዝሩን ለማቅረብ መቸገሩን አቃቤ ሕግ በችሎቱ ባቀረበው አቤቱታ ገልጿል፡፡

ችሎቱም ጥበቃ የሚደረግላቸው ሰዎች ስም ዝርዝር አቃቤ ሕግ እንዲያቀርብ የተሰጠውን ትዕዛዝ ባለመፈጸሙ እስካሁን ጥበቃ የተደረገለት ምስክር የለም ብሏል፡፡

ከሐምሌ 18/2011ዓ.ም ጀምሮ ምስክሮችን ለመስማት የተያዘው ቀጠሮ እንደተጠበቀው ሆኖ፣ የችሎቱ መደበኛ ሥራ እስከ ሐምሌ 15 የሚቀጥል በመሆኑ፣ ችሎቱ ነሐሴ 7 እና 8ን ለተጨማሪ የምስክርነት መስሚያ ቀናት ይዟል፡፡ ተይዘው ጉዳያቸው በፍርድቤት እየታየ ያሉት ተከሳሾች በሒሳብ ደብተራቸው ያላቸውን ገንዘብ እና በቁጠባ ያጠራቀሙትን ገንዘብ በእግድ ምክንያት እስካሁን ለማንቀሳቀስ መቸገራቸውን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡ ችሎቱም ገንዘቡ በሌላ መዝገብ ከታገደ በዚህ መዝገብ ጉዳዩ በቀጥታ ባለመኖሩ የሚሰጥ ትዕዛዝ እንደማይኖር ገልጿል፡፡ ስለጉዳዩም ተከሳሾቹ ጠበቆቻቸውን ቢያማክሩ የተሻለ እንደሚሆን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡

Via waltainfo
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በህንድ በህንፃ መደርመስ የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ፍርስራሽ ተጭኗቸዋል። ምክንያቱ በውል እንዳልታወቀ የተነገረለት ይኸው አደጋ የተከሰተው በደቡባዊ ሙምባይ አካባቢ መሆኑን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ህንፃው የመቶ ዓመት እድሜ እንዳለውና በቅርቡ በአካባቢው ተከስቶ በነበረው ጎርፍ ጋር ሳይያያዝ አይቀርም የሚል ግምት እንዳለም ተነግሯል፡፡

በሀገሪቱ የህንጻ መደርመስ ስጋት እየሆነ መምጣቱንና በርካታ ሰዎች ሰለባ እንደሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በየዓመቱ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ህይወት ላይ አደጋ እያስከተለ ያለው የህንጻ መደርመስ የግንባታ ጥራት ጉድለትና ረጅም እድሜ ማስቆጠር በምክንያትነት ተጠቃሽ ሆነዋል፡፡

በህንፃው ፍርስራሽ ስር ሌሎች ተጎጂዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ የሀገሪቱ እሳት አደጋና ነብስ አድን ቡድን የነፍስ አድን ስራ እያከናወነ እንደሚገኝም የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ/ENA/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀያት ጣፎ ኮንዶሚኒየም #ከተሰረቁት 7 ትራንስፎርመሮች ዉስጥ 2ቱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ #አዲስአበባ

ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሞ አባ ገዳ ምክር ቤት ከኦሮሚያ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የዘንድሮውን ኢሬቻ በዓል ለማክበር እየተሰናዳ ነው፡፡ በዓሉ በአዲስ አበባና ቢሾፍቱ እንደሚከበር አዲስ ስታንዳርድ የአዲሱ አረጋን ትዊተር ገጽ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

Via አዲስ ስታንዳርድ/wzema/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሩዋንዳ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ!

ሩዋንዳ በድንበር አከባቢ የኢቦላ በሽታ መከሰቱ እንዳሳሰባት ገለጸች። በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና በሩዋንዳ መካከል ባለው የጎማ ወሰን አካባቢ የድንበር ተሻጋሪ ሰዎች ምርመራን ለማገዝ ተጨማሪ የሰው ሀይል እየላከች እንደሆነ የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ተናግረዋል።

ቢቢሲ እንደዘገበው የመጀመሪያው የኢቦላ ተህዋስ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ህዝቦች በሚኖሩባት ጎማ ከተማ በምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን በይፋ ከሚታወቁ ቦታዎች ውጭ በሩዋንዳ ጊስኒ መካከል ያለው ቦታ በጣም አስቸጋር ነው ተብሏል።

በቀን ሁለት እና ከዚያ በላይ ሰዎች በስራም ሆነ በትምህርት ምክንያት ድንበር እንደሚያቋርጡም በዘገባው ተጠቅሷል።

ሩዋንዳ ድንበሯን ሳትዘጋ ዜጎች #ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ትሰጣለች ሲሉ የጤና ሚኒስተሩ ጋሹምባ መግለፃቸውን በመረጃው ተጠቅሷል።

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባለፈው ነሐሴ ወር በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ 2 ሺ500 ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከነዚህ መካከል የ1 ሺ 600 በላይ ሰዎችን ህይወት እንደቀጠፈ እና በሀገሪቱ ታሪክ ሁለተኛው ገዳይ በሽታ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል ሲል ነው ቢቢሲ የዘገበው።

Via #BBC/ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሶከር ኢትዮጵያ፦

ማስተካከያ/ይቅርታ
soccerethiopia.net

"በትላንትናው ዕለት የአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜን ኢትዮጵያዊው አርቢትር በዓምላክ ተሰማ እንደሚመራው ገልፀን ነበር። ሆኖም አሁን ባገኘነው መረጃ መሠረት ፍልሚያውን የሚመሩት ዳኞች ምደባ ይፋ እንዳልተደረገ ሲገለፅ በሌላ በኩል ደቡብ አፍሪካዊው ዳኛ ቪክቶር ጎሜዝ ዋና ዳኛ ሆነው መመደባቸው እየተነገረ ይገኛል። ለተፈጠረው የዜና ስህተት/መደነጋገር አንባቢዎቻችን እና ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማን ከፍተኛ ይቅርታ እንጠይቃለን።" /ሶከር ኢትዮጵያ/
_______________________________

TIKVAH-ETHም ሶከር ኢትዮጵያን እንደ ምንጭነት ተጠቅሞ መረጃውን ለእናተ ማድረሱ ይታወቃል!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አሜሪካ ለታይዋን ከምታደርገው የጦር መሳርያ ሽያጭ ጋር ተያይዞ ቻይና ግንኙነታቸው እንደምታቋርጥ ተናገረች። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር እንደገለፀው አሜሪካ ለታይዋን ልታደርገው ያሰበችው የጦር መሳርያ ሽያጭ ካላቆመች የቻይና መንግስትና ኩባንያዎች የንግድ ግንኙነታቸው ያቋርጣሉ ብለዋል፡፡

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዙማ የሞት ማስፈራሪያ ደረሳቸው...

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት #ጃኮብ_ዙማ በርሳቸው አመራር ወቅት የተፈፀመውን የሙስና ጉዳዮች ለሚያጣራው ቡድን የምስክርነት ቃል መስጠታቸውን ተከትሎ የሞት ማስፈራሪያ ለሳቸውም ሆነ ለቤተሰባቸው እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።

ዛሬ ሐምሌ 9፣2011ዓ.ም የማጣራት ስራውን ለሚመሩት ዳኛ እንደተናገሩት ማስፈራሪያው የደረሳቸው ሐምሌ 8፣2011 ዓ.ም የሰጡትን የምስክርነት ቃል ተከትሎ ነው ብለዋል። በዚሁም ቀን በሰጡት የምስክርነት ቃል #የመግደል ሙከራ እንደተሞከረባቸው አሳውቀው ነበር።

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/SA-07-16-5
#update በኦሮሚያ ክልል ውስጥ #በሚገኝ አንድ የኢንዱስትሪ መንደር በሰባት የቻይና ዜጎች ላይ በተፈፀመ የዘራፊዎች ጥቃት አንድ ቻይናዊ መገደሉንና ሌላ አንድ መቁሰሉን የቻይና ኤምባሲን ጠቅሶ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

በጉዳዩ ላይ የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ #አሰግድ_ጌታቸው እሁድ ቻይናውያን ላይ ደረሰ ስለተባለው አደጋ ለጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ይህን ብለዋል፦ "ድርጊቱ የተፈፀመው አዳማ ኢንደስትሪ ፓርክ አቅራቢያ እሁድ አንድ ሰአት ገደማ ነው። እራት ከበሉ በሁዋላ በግሩፕ ወጡ። የሄዱበት ቦታ ከፓርኩ ሶስት ኪ.ሜ ርቀት ላይ ያለ ሲሆን ጭለማ እና ገደላማ ስፍራ ነው። የአካባቢው ሰው እንኳን አይሄድበትም። ለምን ወደዛ እንደሄዱ ገና እየተጣራ ነው። ከዛም ቻይናዎቹ እርስ በርስ እንደተወጋጉ ሟቹ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ተናግሮ ነበር። ከዛ በሁዋላ ግን ሌሎች ሰዎች እንዳረጉት ለማስመሰል ተሞክሯል። በጥርጣሬ የተወሰኑ ቻይናውያንም፣ የአካባቢ ሰዎችም ተይዘዋል። ዝርፊያ ስለተባለው ግን አላውቅም እነሱም ተዘረፍን ብለው ሪፖርት አላደረጉም።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጉምሩክ ኮሚሽን በ2011 በጀት ዓመት ወደ ሀገር ሊገቡና ከሀገር ሊወጡ የነበሩ 1 ቢሊዮን 633 ሚሊዮን 598 ሺህ 338 ብር የሚገመት የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች በቁጥጥር ስር አውያለሁ ብሏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking #ሰበር_ዜና

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄን ህዝበ ውሳኔ አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፦

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የሲዳማ ዞን መስተዳደር ምክር ቤት ውሳኔን መሰረት በማድረግ በህዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን ለመወሰን ህዝበ ውሳኔ እንዲደራጅለት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን እንደ አዲስ የማደራጀት፣ የምርጫ ቦርድ ስልጣንና ተግባር የሚወስነውን ህግ የማርቀቅ እና በተወካዮች ምክር ቤት የማጸደቅ፣ የምርጫ ህጎችን የማሻሻል፣ ተቋማዊ ለውጦችን የማከናወን እንቅስቃቄ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ከነዚህ ተቋማዊ ለውጦች መካከል የቦርዱን ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት አድርጎ የተከናወነው የምርጫ ቦርድ አባላት መረጣ ዋነኛው ነው፡፡

በዚህም መሰረት ከዚህ የቦርድ አባለት መረጣ ሰፊ ምክክርና ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጐበት ከተለየ በኋላ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 06 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ተጨማሪ አራት የቦርድ አባላት ሹመት ተከናውኖ ቦርዱ አባላት ተሟልተውለት ስራውን ጀምሯል፡፡

ቦርዱ ተሟልቶ ስራ በጀመረበት ባለፈው አንድ ወር በእንጥልጥል የሚገኙ እና አስቸኳይ ናቸው ያላቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በቦርዱ አለመሟላት ምክንያት በእንጥልጥል ከቆዮት ጉዳዮች አንዱ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ለቦርዱ የቀረበው የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን ህዝበ ውሳኔ ማደራጀት ነው፡፡

ቦርዱ ስራ ከጀመረ አንስቶ የሲዳማ ዞን ክልልነትን የሚመለከቱ በተለያዩ ጊዚያት የቀረቡትን ጥያቄዎች ከመመልከቱም በላይ ከክልሉና የዞን መስተዳድር አመራሮች ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

እንደሚታወቀው የሲዳማ ዞን የክልልነት ህዝበ ውሳኔ የማደራጀት ጥያቄ ከክልሉ ምክር ቤት ለቦርዱ የደረሰው ህዳር 12/2011 ዓ.ም ሲሆን በህገ መንግስቱ አንቀጽ 47/3/ለ/ ለክልሉ የተሰጠው “ጥያቄው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በአንድ አመት” የሚለው የማደራጀት ጊዜ ገደብ ለቦርዱም ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡

በመሆኑ በህግ መንግስቱ የተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ በቀሩት 5 ወራት ውስጥ ህዝበ ውሳኔውን ለማከናወን የመጀመሪያ ደረጃ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡

ህዝበ ውሳኔ የሚከናወነው የህዝብን ፍላጐትና ውሳኔ ህጋዊ እና ነፃ በሆነ አግባብ መሰጠቱን ለማረጋገጥ ነው፡፡ በመሆኑም ቦርዱ ተገቢና በቂ ዝግጅት አድርጐ ህዝበ ውሳኔውን ማካሄድ ይችል ዘንድ የሚያደርጋቸው ዝግጅቶች
- የህዝበ ውሳኔ አካሄድ የሚመራበት የስነስርአት መመሪያ ማዘጋጀት
- የህዝበ ውሳኔ አጠቃላይ ጊዜ ሰሌዳና በጀት ማዘጋጀት
- በህዝበ ውሳኔ ዝግጅትና ድምፅ መስጠት ሂደት ስለሚኖረው የፀጥታ አጠባበቅ ሁኔታ ግብረ ሃይል ማደራጀትና ዕቅድ ማፅደቅ
- ገለልተኛ የምርጫ አስፈፃሚዎች መመልመል፣ ማሰልጠንና ማሰማራት
- ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መድረክ ማዘጋጀት፣ የድርጊት መርሃ ግብር ማውጣት
- በህዝበ ውሳኔ አፈፃፄም ሂደቱ ላይ የጋራ ምክክር መርሃ ግብሮችን አውጥቶ መተግበር
- የሰነድና ቁሳቁስ ዝግጅትና ህትመት ስራዎች ማከናወን
- ድምፅ መስጫ ወረቀቶችና ፖስተሮች ማዘጋጀት፣ ማሳተም፣ ማሰራጨት
- ህዝበ ውሳኔ ድምጽ ማሰጠት
- ቆጠራና ውጤት ማሳወቅ
ሲሆኑ በሌላ በኩል ሂደቱ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም የሚጠበቅባቸውን ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

በዚህም መሰረት፦

1. የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ከክልሉ መንግስትና ከዞኑ መስተዳደር ጋር በመመካከር በአሁኑ ወቅት የክልሉም የዞኑም አስተዳደር ዋና ከተማ ሆና የምታገለግለው የሀዋሳ ከተማ የህዝበ ውሳኔው ውጤት የሲዳማን ክልል መሆን የሚያረጋግጥ ቢሆን በከተማዋ ላይ ሁለቱ አካላት የሚኖራቸውን መብትና ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚነሱ የሃብት ክፍፍል ጥያቄዎችን የሚያስተናግዱበትን አሰራር አዘጋጅተው ለቦርዱ እንዲያሳውቁ

2. በአዋጅ 532/1999 አንቀጽ 107 በተጠቀሰው የትብብር ድንጋጌ መሰረት የህዝበ ውሳኔው ጸጥታና ደህንነትን ( electoral security) ማስጠበቅን አስመልክቶ የፌደራል ፓሊስ፣ የክልሉ ፓሊስና የዞኑ ፓሊስ በትብብር የሚሰሩበትን ዝርዝር እቅድ እንዲያወጡና ከቦርድ ጋር ተባብረው እንዲሰሩ

3. የደቡብ ክልል ምክር ቤት በሲዳማ ዞን የሚኖሩ የተለያዩ የሌሎች ብሄር ብሔረሰብ አባላት ከህዝበ ውሳኔው በኋላ የሚኖራቸውን ህጋዊ የመብቶች ጥበቃ አስመልክቶ ግልጽ አስተዳደራዊና ህጋዊ ማእቀፍ እንዲያዘጋጅና ለቦርዱ እንዲያሳውቅ ምርጫ ቦርድ የወሰነ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የሚመለከታቸው አካላት ከላይ የተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ምላሽ እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ.ም በጽሁፍ እንዲያሳውቁ ወስኗል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህገ መንግስቱና በምርጫ አዋጁ የተሰጠውን ሃላፊነት አለም አቀፍ የምርጫ መሰረታዊ መርሆዎች ጋር በማጣመር ሃላፊነቱን ለመወጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ለመግለጽ ይወዳል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሐምሌ 10/2011 ዓ.ም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም...

ኔልሰን ማንዴላ ፕሬዝደንት ከሆኑ በኋላ አንድ እለት ከቅርብ ጠባቂዎቻቸው ጋር ለምን በእግራችን ወጣ ብለን አንንሸራሸርም በዛው ምሳ እንበላለን ብለዋቸው ተያይዘው ወጡ።

አንድ ሞቅ ያለ ሰፈር ሲደርሱ ምግብ ቤት አግኝተው ከጠባቂዎቻቸው ጋር ገብተው እንዳዘዙ ከፊት ለፊታቸው ያዘዘው ምግብ የዘገየበት አንድ ሰው ስላዩ "ጥሩትና ከእኛ ጋር ይብላ"ብለው አንዱን ወታደር ላኩ። ሰውየው መጥቶ አብሯቸው ተመገበ።

እየተመገበ ሳለ እጁ ይንቀጠቀጣል ጨርሶ ሲሄድ ከጠባቂ ወታደሮቹ መሃል አንዱ "ማዴባ የቅድሙ ሰውዬ ህመምተኛ ነበርኮ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር" ይላቸዋል "አይደለም! ድሮ የታሰርኩበት እስር ቤት ጠባቂ ዘበኛ ነበር። ብዙ ግዜ ተደብድቤ ከቶርች ስመለስ ውሃ ስለሚጠማኝ ውሃ እንዲሰጡኝ በጩኽት ስጠይቅ ይሄ ሰው በምላሹ ይመጣና ፊቴ ላይ ሽንቱን ይሸናል።አሁን የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት ሆኜ ሲያየኝ የምበቀለው መስሎት ፈርቶ ነው" ሀገር 'በመቻቻል እና #በፍቅር እንጂ በቂም በቀል አትገነባም። ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ባህርይ ናትና-

Via Book For All

ሰላም ህልውናችን ነው!
ሰላም እደሩ!

🗞ሃምሌ 09/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤትና ተቃዋሚዎች በዛሬው ዕለት ስልጣን ለመጋራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ሁለቱ የሱዳን የፓለቲካ ሀይሎች በኢትዮጵያና የአፍሪካ ህብረት በቀረበው ረቀቅ የሽግግር እቅድ በቅርቡ ስምምነት ላይ መድረሳቸው የሚታወስ ነው፡፡

ስምምነቱን ተከተሎ የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር መሀመድ ሃምዳን ዶጋሊ ባደረጉት ንግግር የፓለቲካ ስምምነቱ ለሀገሪቱ ታሪካዊ ክስተት ነው ብለዋል፡፡
በሀገሪቱ ህገ መንግስት ላይ የተደረሰው ስምምነት ደግሞ በመጪው አርብ እንደሚፈርም ነው ተቃዋሚዎች ለአናዶሉ የተናገሩት፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ አዳማ በተገነባው የክፍያ መንገድ በተሰጡ አገልግሎቶች በ2011 በጀት አመት ከ2 መቶ ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተነግሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞዋ የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ዩርሱላ ቮን ደ ለየን የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል። የ60 ዓመቷ ዩርሱላ ቮን ደ ለየን የኮሚሽንን ፕሬዚዳንት ሆነው ሲሰሩ የቆዩተን ዣን ክላውድ ዠንከርን ተክተው ይሰራሉ። ባደረጉት ንግግርም “በእኔ ላይ ያሳያችሁት መተማመን በጠንካራዋና በተባበረችው አውሮፓ ላይ ያላችሁን መተማመን ያሳያል” ብለዋል። አዲሷ ፕሬዚዳንት በሚስጥር በተከናወነ የድምፅ አሰጣጥ አሸንፈው ነው ስልጣን የተቀዳጁት።

Via አልጄዚራና ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርቢትር በአምላክ ተሰማ የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን የማይመራው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ስለመራ ነው ተብሏል። አሁን የደቡብ አፍሪካው አርቢትር ቪክቶር ጎሜዝ ጨዋታውን እንደሚመሩት የታወቀ ሲሆን ለውጡ የተደረገውም በካፍ አካሄድ የግማሽ ፍፃሜን የመራ ዳኛ ፍፃሜ ስለማይመራ ነው። ከዚህ በፊትም በካፍ ጨዋታዎች ታሪክ ግማሽ ፍፃሜ እና ፍፃሜ የመራ አርቢትር የለም ተብሏል። ይሁንና ኢትዮጵያዊው አርቢትር በዘንድሮው አህጉራዊ ውድድር ትልቅ አክብሮት እና ምስጋናን ለራሱ እና ለሀገሩ አትርፏል።

Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ ወደ ሀረር...

ቆቦ አካባቢ መንገድ ተዘግቶ #መቆማቸውን መንገደኞች ገልፀዋል። ምክንያቱ ምን እንደሆነ እንደማያውቁ የተናገሩት መንገደኞቹ ለረጅም ደቂቃ መቆማቸውን ጠቁመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመጪው ሀምሌ 22/2011 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ቀን ለመትከል እቅድ ተይዞ ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ነው፡፡
በእለቱም:-
* በትግራይ ክልል 12 ሚሊዮን
* በአማራ ክልል 108 ሚሊዮን
* በኦሮሚያ ክልል 126 ሚሊዮን እንዲሁም
* በደቡብ ክልል 48 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

@tsegabwolde @tikcahethiopia
#update ሳውዲ በየመን ድሮኖች ላይ ጥቃት መፈፀሟን ገለጸች፡፡ የየመን 3 የስለላ ድሮኖች ጅዛን እና አብሃ በተባሉ የየመን አዋሳኝ ወደ ሳውዲ ከተሞች ከመንቀሳቀሳቸው በፊት በሳውዲ አየር ሀይል መደምሰሳቸውን ወታደራዊ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

በመንግስት የሚመራው ሳውዲ ፕረስ ኤጀንሲ እንደዘገበው ቦምብ ተሸካሚ ድሮኖቹ በየመን በሚንቀሳቀሱት የሀውቲ አማፅያን የሚመሩ ቢሆንም ድርጊቱን በዋናነት የምታቀነባብረው ኢራን መሆኗን ነው የገለፀው። ሳውዲ በየመን ላይ በምትወስዳቸው ጥቃቶች የተነሳ ንፁሀን ዜጎች ምን ያህል እየተሰቃዩ መሆኑን አንድ የየመን ሰብዓዊ መብት ቡድን ገልጿል፡፡

ቡድኑ እንዳለው የሳውዲ የአየር ጥቃት ትምህርት ቤቶችንና ሆስፒታሎችን ኢላሚ ያደረገ በመሆኑ ብዙ ጥፋቶችን በየመን አስከትለዋል ብሏል፡፡ እስካሁን በተደረጉ የአየር ላይ ጥቃቶች ቢያንስ ወደ 175 ንፁሀን እንዲሁም 165 ህፃናትን ጨምሮ መገደላቸው ተገልጿል፡፡

በአደጋው ከ427 በላይ የቆሰሉ ንፁሀን ሲኖሩ ይህም 172 ህፃናትን ያካትታል ነው ያለው፡፡ ይህም ቁጥር ለ 150 ጊዜ በተደረጉት የአየር ላይ ትቃት ብቻ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
የየመኑ የሰብዓዊ መብት ቡድኑ ይህንን ሪፖርት ያወጣው ከ2 ሺህ በላይ የመናውያንን በማነጋገር መሆኑን የአሜሪካው ዜና አውታር ኤፒ ዘግቧል፡፡

Via AP/ኢትዮኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የዓባይ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ሠራተኞች ከ16 እስከ 25 ሚሊዮን ብር ይሆናል የተባለ ገንዘብ ወደ አዲስ አበባ ይዘው ሲገቡ፣ በቁጥጥር ሥር ውለው መታሰራቸውን ሪፖርተር ዘገበ።

የባንኩ ሠራተኞች ናቸው የተባሉት ግለሰቦች ገንዘቡን ከመሃል ሜዳ፣ ደብረ ብርሃንና በዚያው አካባቢ ካሉ የዓባይ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ቢሮዎች ሰብስበው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ እያሉ፣ ወደ አዲስ አበባ መዳረሻ አካባቢ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተነግሯል፡፡

ግለሰቦቹ እንዴት? ለምን? በማን ፈቃድ? ገንዘቡን ሰብስበው ይጓዙ እንደነበር፣ እንዲሁም የገንዘቡን ትክክለኛ መጠን እንዲያብራሩ የባንኩን ፕሬዚዳንት አቶ የኋላ ገሠሠን በግል ስልካቸው ሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2011 ዓ.ም. ሪፖርተር ጋዜጣ አነጋግሯቸው ነበር፡፡

አቶ የኋላ፣ ‹‹ገና እያጣራሁ ነው፡፡ ልጨርስና እንነግራችኋለን፡፡ ነገ ደውሉልኝ፤›› ያሉ ቢሆንም፣ በቀጠረው መሠረት ማክሰኞ ሐምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ቢደውልላቸውም ሆነ አጭር መልዕክት ቢላክላቸውም ምላሽ አልሰጡም፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የባንኩ ሠራተኞችም ሆኑ ገንዘቡ እስከ ማክሰኞ ምሽት ድረስ እንዳልተለቀቁ የሪፖርተር ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

Via #ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር ፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ሐምሌ 15 ይጀምራል፡፡

ምክር ቤቱ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት በእጩነት የቀረቡትን የአቶ ተመስገን ጥሩነህ ሹመት እና የ2012 ረቂቅ በጀትን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

የምክር ቤቱ ስብሰባ ከሐምሌ 15 እስከ 18/ 2011 ዓ.ም ባሉት ቀናት በባሕር ዳር እንደሚካሄድ መርሀ ግብሩ ያሳያል፡፡

ምንጭ ፡- አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia