TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥቃት አድራሹ ታወቀ‼️

ትናንት ረቡዕ ማታ በአንድ የካሊፎርኒያ መጠጥና ዳንስ ቤት ውስጥ 12 ሰዎችን የገደለው ግለሰብ፣ የ28 ዓመቱ #ኢያን_ሎንግ መሆኑን፣ ባለሥልጣናት አስታወቁ። ለግድያው ምክንያቱ አልታወቀም። ሎንግ፣ ራሱንም ጭምር #ያጠፋበትን የጅምላ ግድያ የፈፀመው በእጅ ቦምብና ሽጉጥ በመጠቀም ሲሆን፣ ምሽቱ የኮሌጅ ተማሪዎች የሆነ ሥርዓት የሚያከናውኑበት እንደነበርም ታውቋል። የቬንቱራ ቀበሌ ፖሊስ አዛዥ ገኦፍ ዲን ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል፣ ሁኔታውን በማረጋጋት ላይ የነበረ አንዱ አባላቸው ከሰለባዎቹ መካከል እንደነበርም ገልፀዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውይይቱ በተለያዩ ቦታዎች ቀጥሏል‼️
ያዳመጣችሁት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ5 ኪሎ ግቢ ተማሪዎች በሰላም ዙሪያ ውይይት እያደረጉ እንደሆነ የገለፁበት ድምፅ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሰው ልጆች ፍቅር
ለሰው ልጆች ሰላም
ለሰው ልጆች በዓለም ዙሪያ ሁሉ
ሰላም ይሁን ምድሩ ሁሉ።

ፈጣሪ እስከዘላለሙ አፋቅሮ ያኑረን።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በርማ‼️

ባለፈው ዓመት ሚያንማር(በርማ) ውስጥ በወታደራዊው ገዢ መደብ የደረሰውን ግድያ ሽሽት ከሀገር የተሰደዱ ሮሒንግያ ሙስሊሞች፣ ከ2ሺህ 2መቶ በላይ ሰዎች በዚህ ወር ካገሪቱ #እንደሚባረሩ በመስማታቸው፣ ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ እንደሚገኙ ተገለፀ።

አንዳንዶቹ እንዲያውም፣ «ወደ ራከሂኒ ከመመለስ፣ ራሳችንን በራሳችን ብናጠፋ ይሻለናል» ማለታቸው ተሰምቷል። በራከሂኒ የሚያንማር ወታደራዊ ገዢ መደብ፣ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በማወጁ ይወነጀላል።

“ያለንን ሁሉ አጥተናል፣ አሁን ብንመለስ የሚጠብቀን ግድያና ወከባ ነው” ሲል ማንነቱ እንዳይታወቀ የፈለገ ስደተኛ በሰጠው ቃል፣ “ይገደላሉ” ተብሎ ስም ዝርዝራቸው ከተሰጠው መካከል እንደሆነም ተናግሯል።

በዚህ በኅዳር ወር አጋማሽ፣ የሮሒንግያ ስደተኞችን ለመመለስ፣ ሚያንማር እና ባንግላዴሽ ሥምምነት አድርገው እንደነበር ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቪኦኤ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update በአዳማ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች የፈሳሽ ማጠራቀሚያው በጤናችን ላይ ችግር እያስከተለ ነው አሉ፡፡

ምንጭ፦ ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውይይቱ ቀጥሏል‼️በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ የTIKVAH-ETH አባላት ከቤተሰቦቻቸው ጋር እየተወያዩ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀለ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎችም ሰብሰብ ብለው ስለ ሰላም ተነጋግረዋል፤ ተወያይተዋል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጋር ወደ ጦርነትና የእርስ በርስ #ግጭት የሚሄድ ነገር ይኖራል ብለው እንደማያስቡ የጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም #ብርሃኑ_ጁላ ተናገሩ፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ክቡር ጠ/ሚ ዶክተር #አብይ_አህመድ ሁለት የተለያዩ ውይይቶች ከወልቃይት ፀገዴና ከቅማንት የአገር ሽማግሌዎች ጋር የተቀሰቀሱ ግጭቶችን #በሰላም በመፍታት ዙሪያ ተወያይተዋል። #ጎንደር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ ጉባኤ‼️

የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 4ኛ የሥራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በመጪው #ቅዳሜ እንደሚካሄድ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አስታወቁ።

አፈ ጉባኤው አቶ #ላክደር_ላክባክ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት አስቸኳይ ጉባኤው የሚካሄደው የክልሉን መንግስት የሚመራው ጋህዴን በቅርቡ ባካሄደው ግምገማ የክልሉ ዋናና ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ነው።

ለአንድ ቀን በሚካሄደው ጉባኤ የክልሉ ዋናና ምክትል ርዕሳነ መስተዳድሮች ያቀረቡት የስልጣን መልቀቅ ጥያቄ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አፈ ጉባኤው ገልጸዋል።

በምትካቸውም አዲስ ዋናና ምክትል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንደሚሾሙ ይጠበቃል ።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በ14 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁን የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ #ኢብራሂም_ኡስማን ተናግረዋል። የኢንዱስትሪ ፓርኩ ከአንድ ወር በኋላ ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነቀምት‼️

በነቀምቴ ከተማ አስተዳደር ተቋርጦ የቆየው  የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ  #መደበኛ ስራ  መጀመሩን የከተማው አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የከተማው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን  ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈይሣ ብርሃኑ እንዳሉት ተቋማቱ አገልግሎት ያቆሙት በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ምስራቅ ወለጋ አዋሳኝ ወረዳዎች በተፈጠረ ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች ዘላቂ #መፍትሔ እንዲሰጥ ለመጠየቅ ነው።

በዚህም ከጥቅምት 26/2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለሶስት ቀናት ስራቸውን አቋርጠው ቆይተዋል፡፡

እነዚህ በከተማዋ የሚገኙ  የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች፣ የትራንስፖርት ፣ የትምህርትና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዛሬ ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውን ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

የከተማዋ  ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ግርማ አብዲሣ በበኩላቸው በአሁኑ ጊዜ በከተማው አስተማማኝ ሠላም ሰፍኖ ሁሉም ነገር  ወደ ነበረበት መመለሱን ገልጸዋል፡፡

ከነዋሪዎቹ  መካከል ወይዘሮ የሺ ሐረግ ፋንታሁን በሰጡት አስተያየት የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስራ ማቆማቸው በተለይ በቀን ሠራተኛውና  በሌሎችም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንና የመንግሥት ስራም መበደሉን ጠቁመዋል፡፡፡

በመንገድ መዘጋጋት ምክንያት አምቡላንሶች ወላድ እናቶችንና ድንገተኛ ህሙማንን ወደ ጤና ተቋማት ለማድረስ ችግር ሆኖባቸው መቆየቱን የተናገሩት ደግሞ የከተማዋ ቀበሌ ሰባት ነዋሪ ወይዘሮ ድንቅነሽ ምትኩ  ናቸው ፡፡

ሌላው የከተማዋ ቀበሌ ሶስት ነዋሪ አቶ ጌታሁን ወዳጆ እንዳሉት ማንም እንደፈለገው መንገድ የሚዘጋና  የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን የሚያቋርጥ ከሆነ በነዋሪው ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው፡፡

መንግሥት የሕግ የበላይነትን ማስከበርና  የሕዝቡ ቅሬታ መስማት እንዳለበት አመልክተዋል፡፡

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች‼️

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ፣ የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝደንት ከስራ #መታገዳቸው ለተጀመረው የእርቅና #የሰላም ጉዞ የማይበጅ መሆኑን ተናገረ፡፡

ኮሚቴው ዛሬ አጠቃላይ የስራ አፈፃፀሙን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫውም ልዩ ልዩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ማቋቋሙንና ሀላፊነት መስጠቱን ተናግሯል፡፡

ወቅታዊ ችግሮችንና ቀውሶችን ለመፍታት በቂ ጥረት አድርጌያለሁ ብሏል፡፡ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ከሚገኙ የአለም ሙስሊም ማህበረሰቦች ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረጉን ተናግሯል፡፡

ኮሚቴው በአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንት በሼህ #መሀመድ_ሸሪፍ ላይ የተደረገው የስራ እገዳ ከወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ያልተዛመደና አንድን ግለሰብ ነጥሎ ተጠያቂ ያደረገ ነው፤ ስለሆነም ለጀመርነው የእርቅና የሰላም ጉዞ የማይበጅ መሆኑን ተገንዝበው የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትና የፌዴራል እስልምና ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ሂደቱን በጥሞና እንዲያስቡበት መክሯል፡፡

የጋራ ኮሚቴው የኢትዮጵያን ሙስሊሞችን ሁሉ ያለ ልዩነት የሚያሳትፍና የጋራ የሆነ መጅሊስን ለማዋቀር ውጥን መያዙን ተናግሯል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህፃን በፀሎት ብርሃኑ‼️

አሰቃቂ ወንጀል በሚፈጽሙ ግለሰቦች ላይ ቀደም ሲል የሚሰጠው የፍርድ ውሳኔ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ በርካቶች ሌላ የወንጀል ድርጊት እንዲፈጽሙ እያደረገ ነው  ሲሉ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጹ፡፡

በርካታ ቁጥር ያላቸው የደሴ ከተማዋ ነዋሪዎች የሰባት ዓመት ህጻን በአሰቃቂ ሁኔታ #የገደለው ግለሰብ የማያዳግምና ሌላውን ሊያስተምር የሚችል #እርምጃ እንዲወሰድበትም ትላንት በአደባባይ ጠይቀዋል፡፡

የሟች ህጻን በጸሎት ብርሃኑ እናት ወይዘሮ አበባ ሙህዬ ልጃቸው ባለፈው ጥቅምት 24 ቀን 2011 ዓ.ም ለጨዋታ እንደወጣች ሳትመለስ መቅረቷን ይናገራሉ፡፡

በልጃቸው ያልተለመደ መዘግየትና ወጥቶ መቀረት የተደናገጡት እናት ከአካባቢው ሰዎች ጋር በመሆን ፍለጋ ቢያካሂዱም ህጻኗ ሳትገኝ ቀርታለች፡፡

ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ህጻኗ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ አስክሬኗ መገኘቱን የገለጹት ወይዘሮ አበባ በጥርጣሬ ከተያዙት ግለሰቦች ከአንዱ ጋር በትዳር አብረው የቆዩ መሆናቸውንና አንድ ልጅ ከወለዱለት በኋላ መፋታታቸውን ተናግረዋል።

ፍቺውን ተከትሎ ግለሰቡ ለመግደል በተደጋጋሚ ሲዝትባቸው መቆየቱን ነው የጠቆሙት፡፡

ህጻኗ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ አስክሬኗ መገኘቱ እንደተሰማ ትላንት በደሴ ከተማ #አለመረጋጋት ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ወንጀሉን በፈጸመው ሰው ላይ የማያዳግምና ሌላውን ሊያስተምር የሚችል ርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል፡፡

የደሴ ከተማ አስተዳደርና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንደሰን ጸጋዬ በበኩላቸው ድርጊቱ አሳዛኝ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የህጻኗ አስከሬን ከትናንት በስቲያ በምትኖርበት አካባቢ ከሚገኝ ጫካ በጆንያ ውስጥ #ተጠቅልሎ መገኘቱን ተከትሎ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ከጉዳዩ ጋር ግንኙት ይኖራቸዋል የተባሉ ሦስት ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጸዋል፡፡

🔹ዛሬ በደሴ ከተማ ተፈጥሮ የነበረው ውጥረት መረጋጋቱን ለመስማት ተችሏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወገን! ሰከን ማለት ዋጋ አለው! #ሰላምን እስክታጣት ድረስ ምንም ላይስመስልህ ይችላል። ነገር ግን ሰላም አንዴ ከእጅህ ከወጣች የልጅ ልጅህን #ብትገብር እንኳን መልሰህ ላታገኛት ትችላለህ።

#ሶሪያ የቀደመው ገፅታዋን እና #አሁን ያለውን ገፅታዋን ከላይ ባለው ፎቶው ተመልከት። ያኔ በትንሽ በትልቁ አትባላም።

ሰላም ለኢትዮጵያ!
ተወያይተን ችግራችንን እንፍታ!
#ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ረድኤት ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ‼️ትላንት በሰላም ጉዳይ ላይ ሰብሰብ ብለው ውይይት ሲያደርጉ ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia