TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrTedrosAdhanom

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክትር ዶክትር ቴድሮስ አድኃኖም በፖለቲካዊ አለመግባባት ሳቢያ የሰውን ህይወት ለማዳን የሚደረገው ጥረት ሊደናቅፍ እንደሚችልም አስጠነቀቁ።

ከአሜሪካ ጋር አለምግባባት ውስጥ ስለገባው ድርጅታቸው በተመለከተ ዶክተር ቴድሮስ በስሜት ተሞልተው በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት "በዓለም የጤና ድርጅት ውስጥ ምንም ምስጢር የለንም፤ የህይወት ጉዳይ በመሆኑ መረጃን ባገኘን ጊዜ ሁሉ እናጋራለን" ሲሉ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረውም "ከየት እንደመጣሁ ታውቃላችሁ፤ ስለጦርነት አውቃለሁ። ድህነትንም አውቃለሁ። ሰዎችን ለስቃይ ስለሚዳርጉ ነገሮች አውቃለሁ። ሰዎች እንዴት በድህነት ምክንያት ለሞት እንደሚዳረጉ አውቃለሁ" ሲሉ በስሜት ተናግረዋል።

"ይህን ሁሉ የማያውቁ ይኖራሉ. . . በቀላል የህይወት ጎዳና ላይ አልፈው ይሆናል። ምናልባትም ጦርነት ማለት፤ ድህነት ማለት ምን እንደሆኑ ላያውቁ ይችላሉ። ለዚህም ነው ስሜታዊ የሆንኩት" ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ድርጅታቸው የኮሮናቫይረስን የተመለከተ ምንም አይነት መረጃ ከየትኛውም አገር አለመደበቁን በዘርዝር አብራርተዋል።

ዶክትር ቴድሮስ በቴሌቪዥን በተላለፈው መግለጫቸው ላይ እንዳሉት ከአሜሪካ የበሽታ መቆጠጠሪያና መከላከያ ማዕከል የተወከሉ 15 ባለሙያዎች ከጥር ወር ጀምሮ ስለበሽታው ያሉ መረጃዎችን በሙሉ እንዲያውቁ ሲደረጉ ቆይተዋል ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በአፍሪካ ፣ በማእከላዊ እና በደቡብ አሜሪካ እና በምስራቅ አውሮፓ እየጨመረ የመጣው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አዝማሚያዎች አሳሰቢ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በጄኔቫ በቪዲዮ ኮንፈረንስ እንደገለጹት፣ በምዕራብ አውሮፓ ወረርሽኙ እየተረጋጋ ወይም እየቀነሰ ቢታይም፣ ለብዙ አገሮች በሽታው ገና እየጀመረ መሆኑንና በወረርሽኙ የመጀመሪያ ደረጃዎች ላይ ጥሩ ሆነው የተገኙት አንዳንድ አገራት በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ እየተስፋፋባቸው መምጣቱን ዶ/ር ቴድሮስ ተናግረዋል፡፡

“ብዙ አገራት አሁንም በወረርሽኙ የመጀመሪያ ደረጃዎች ላይ ናቸው፤ በወረርሽኙ መጀመሪያ ላይ የተጎዱት የተወሰኑ አገራት አሁን መልሶ መቋቋም ጀምረዋል” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም "ምንም ስህተት መስራት የለብንም፣ የምንጓዘው ረዥም መንገድ አለ፣ ይህ ቫይረስ ለረጅም ጊዜ ከእኛ ጋር ይቆያል" ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ፣ ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WHA73 የዓለም የጤና ድርጅት አመታዊ ጉባኤ በቪዲዮ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። ጉባዔው በዋናነት አባል ሀገራቱ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚያተኩር ነው ተብሏል። በጉባዔው መክፈቻ ላይ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ሃገራቸው ቫይረሱን ለመቆጣጠር አበረታች ስራ መስራቷን ጠቅሰው፥ አስፈላጊው ግምገማ ቫይረሱን መቆጣጠር ከተቻለ በኋላ ይደረጋል ብለዋል። አያይዘውም ሃገራቸው ቫይረሱን…
#WHA73 #DrTedrosAdhanom

በትንሹ 320 ነርሶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ሞተዋል!

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የሚሞቱ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር ከፍተኛ አደጋን ደቅኗል ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናገረዋል።

ዓለም አቀፉ የነርሶች ምክርቤት በስሩ ካሉት ማህበራት ባሰባሰበድ መረጃ መሰረት በአንዳንድ ሃገራት የሚስተዋለው የነርሶቹ የተጠቂነት ቁጥር በ20 በመቶ አሻቅቧል፤ በዓለም አቀፍ ደረጃም በትንሹ 320 ነርሶች ሞተዋል፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ መረጃዎች በወጉ ሊሰበሰቡ ቢችሉ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የድርጅቱ አባል ሃገራት የጤና ባለሙያዎቻቸውን ከወረርሽኙ #ሊጠብቁ ፣ አስፈላጊውን የህክምና ግብዓቶች ሊያሟሉላቸው እና መረጃዎችን ስርዓት ባለው መልኩ ሊሰበስቡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መድሃኒት ለማግኘት ሲጠቀምበት የነበረውን የፀረ ወባ መድሃኒት ፣ ሃይድሮክሲክሎሮክዊን ለጊዜው #አቋረጠ

የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ቦርድ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከአምስት ቀን በፊት በታተመው ላንሰት የሕክምና መጽሔት ላይ የወጣውን የጥናት ሪፖርት መሰረት አድርጎ ነው። በዚህ ጥናት መሰረት መድሃኒቱ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎችን ሞት #ያፋጥናል ይላል።

የዓለም ጤና ድርጅት [WHO] ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "የከፍተኛ አመራሮቹ ቡድን አባላቱ #የሃይድሮክሲክሎሮክዊን ሙከራ ደህንነቱ ዳግም በደህንነት ቁጥጥር ቦርዱ እስኪመረመር ድረስ ለጊዜው እንዲቋረጥ ወስነዋል" ብለዋል። ሌሎቹ የምርምር ስራዎች ግን መቀጠላቸውን ገልፀዋል።

'ሃይድሮክሲክሎሮክዊን' (የፀረ ወባ መድሃኒት) በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ሌሎች መሪዎች ለኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ቢሰጥ በፍጥነት እንዲያገግሙ ያደርጋል በሚል ሲወደስ ቆይቶ ነበር።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

"የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተባባሰ ነው " - WHO

ምንም እንኳን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥርጭት በአውሮፓ እየቀነሰ ቢሆንም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግን እየተባባሰ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም አስታወቁ።

ዳይሬክተሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፤ ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ገልፀዋል።

ትናንት ከተመዘገበው ከ136,000 በላይ ኬዝ 75 በመቶ የሚሆነው የተገኘው በአስር (10) አገራት ሲሆን አብዛኞቹ አሜሪካ እና ደቡብ እስያ ውስጥ የተገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በበርካታ አገራት የታየው አዎንታዊ ለውጥ አበረታች እንደሆነ ዳይሬክተሩ ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም አክለዋል።

"አሁን ላይ የእነዚህ አገራት ትልቁ ችግር #ግድየለሽነት ነው። ምን ያህል ሕዝብ ለቫይረሱ እንደተጋለጠ የሚያሳዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አሁንም በዓለም ላይ ያለ አብዛኛው ሰው ለበሽታው ተጋላጭ እንደሆነ ያሳያል" ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

#BBC #GoaChronicle
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Dexamethasone 'ዴክሳሜታሰን' የተባለው መድሃኒት በኮሮና ቫይረስ በሽታ በፅኑ የታመሙትን ሰዎች ህይወት ለመታገድ እንደሚረዳ የብሪታንያ ተመራማሪዎች ገለፁ። ሳይንቲስቶቹ በህክምና ላይ ያሉና በቬንትሌተር የሚተነፍሱት ታማሚዎችን የመሞት እድል በአንድ ሶስተኛ እንደሚቀንስ የገለጹ ሲሆን በኦክስጅን ውስጥ ያሉትን የመሞት ዕድላቸውን በአንድ አምስተኛ እንደሚቀንስ ተናግረዋል፡፡ ይህ መድሃኒት የኮቪድ…
#DrTedrosAdhanom

በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 'ዴክሳሜታሶን' በተባለው መድኃኒት ላይ የተደረገው ሙከራና ያስገኘውን ውጤት በበጎ እንደሚመለከተው የዓለም ጤና ድርጅት ማስታወቁን #ቢቢሲ ዘግቧል።

በሙከራው ይህ መድኃኒት በኮቪድ-19 በጽኑ ከታመሙ ሰዎች የአንድ ሦስተኛውን ሕይወት መታደግ እንደሚችል እና በወረርሽኙ ሰበብ ኦክስጂን በሚያስፈልጋቸው ሰዎች ላይ የሚያጋጥምን ሞት በአንድ አምስተኛ ሊቀንስ እንደሚችል ለድርጅቱ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ግኝት አመልክቷል።

ድርጅቱ እንዳለው የዴክሳሜታሶን ጠቀሜታ በኮቪድ-19 በጸና በታመሙ ሰዎች ላይ እንጂ ቀለል ያለ ህመም ባለቸው ላይ እንዳልሆነ አመልክቷል https://telegra.ph/T-06-18-2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ “ወደ አዲስና አደገኛ” ደረጃ እየተሸጋገረ ነው ሲል አስጠነቀቀ።

ድርጅቱ ይህንን ያለው ሐሙስ ዕለት በዓለም ዙሪያ ከዚህ ቀደም ከታየው በበለጠ በአንድ ቀን ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በበሽታው መያዙን በተመለከተ ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም እንዳሉት በአንድ ቀን 150 ሺህ አዲስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ተመዝግበዋል።

ከዚህም ውስጥ ግማሽ ያህሉ ከሰሜንና ደቡብ አሜሪካ አህጉራት የተገኙ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ደግሞ ከመካከለኛው ምሥራቅና ደቡብ እስያ አገራት የተገኙ ናቸው ብለዋል።

ዶክተር ቴድሮስ ጨምረውም ኮሮናቫይረስ አሁንም በፍጥነት ከመዛመቱ በተጨማሪ ወረርሽኙ እየተስፋፋ ይገኛል ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት "ሰዎች እራሳቸውን ለይተው በመቆየት ተሰላችተው ይሆናል። አገራትም ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴዎችን መክፈት ይፈልጋሉ። ነገር ግን አሁን ከሌላው ጊዜ በበለጠ ጠንቃቃ መሆን የሚያስፈልግበት ነው" ሲሉ መክረዋል - #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በሰጡት መረጃ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 ከተያዙት ከ9 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መካከል የመጀመሪያው 1 ሚሊዮን የተመዘገበው በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ሲሆን የኃለኛው 1 ሚሊዮን ግን በ8 ቀን ጊዜ ውስጥ ነው የተመዘገበው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ቀጥ አድርጎ የሚያቆም ተዓምረኛ መፍትሄ ላይገኝ ይችላል ሲሉ አስጠንቀቅዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ፥ ወረርሽኙን ለመግታት የሚበጀው ሀገራትና ግለሰቦች በሙሉ ቫይረሱን ለመከላከል የሚጠቅሙ መንገዶችን ሁሉ ስራ ላይ ማዋል እንደሆነ አሳስበዋል።

የመጨረሻ ደረጃ ሙከራ ላይ ያሉ ክትባቶች አሉ ነገር ግን ምርመራ ፣ ንክኪ ያላቸው ሰዎች ፈልጎ መለየት ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም እና መሰል መንገዶችን መጠቀሙ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

ዓለም የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ወደማግኘት እየተቃረበ ቢሆንም የኮቪድ-19 መከላከያዎችን ማላላት የለበትም ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አሳሰቡ።

ዶ/ር ቴድሮስ ፥ "የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) አሁንም የዛሬ 8 ወር እንደነበረው አስጊ ወረርሽኝ መሆኑን እንደቀጠለ ነው" ብለዋል።

በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኝ የሰላም ጉባዔ ላይ "በኮቪድ-19 ታክቶን ይሆናል ነገር ግን እርሱ ገና አልሰለቸንም" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም።

የአውሮፓ አገራት እየታገሉ ነው ነገር ግን ስርጭቱን ለማቆም የተወሰዱት እርምጃዎች እንዲሁም ቫይረሱ ምንም ለውጥ አላሳየም" ሲሉ ተናገረዋል።

ከሰሞኑን የተለያዩ ሀገራት ተመራማሪዎች "ውጤታማ" የሆነ ክትባት ማግኘታቸውን እየገለፁ ነው።

ዶ/ር ቴድሮስ ገና ደህንነቱ እና ውጤታማነቱ መፈተሽ ባለበት ክትባት ላይ መተማመን አደገኛ መሆኑን ገልፀዋል።

"ክትባት በፍጥነት ያስፈልጋል ፣ ነገር ግን እጃችንን አጣጥፈን ቁጭ አንልም" ብለዋል። (BBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#FDREDefenseForce የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ የWHO ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የ 'ህወሓትን ቡድን' በመደገፍ ከሰዋል። የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራትን ጭምር ጦርነቱን እንዲያወግዙ ሰርተዋል፤ የጦር መሳሪያዎችንም እንዲያገኙ ሰርተዋል ሲሉ ተናገረዋል። ዶ/ር ቴድሮስ እስካሁን ለቀረበባቸው ክስ ምላሽ አልሰጡም። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

ዶ/ር ቴድሮስ ኣድሃኖም ዛሬ በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው ሁኔታ 'ለየትኛውም ወገን አልወገንኩም' ሲሉ አሳውቀዋል።

ከሰሞኑን እሳቸውን በሚመለከት እየወጡ ያሉ ዘገባዎችንም 'እውነት አይደሉም' ብለዋቸዋል።

እኔ የምወግነው ከአንድ ወገን ጋር ብቻ ነው እሱም ከ'ሰላም' ጋር ነው ብለዋል።

ዶክተር ቴድሮስ ኣድሃኖም በመግለጫቸው ፥ ሁሉም ወገኖች "ለሰላም እና ለሲቪሎች ደህንነት መጠበቅ" እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

* ዶ/ር ቴድሮስ የሰጡት መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#WHO #DrTedrosAdhanom

የአስትራዜኔካ ክትባት የደም መርጋትን ስለማስከተሉ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባለመኖሩ በዚህ ስጋት አገሮች ክትባቱን ከመስጠት መቆጠብ የለባቸውም ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

በትንሹ 5 የአውሮፓ ሀገራት አይስላንድ፣ ቡልጋሪያ፣ ዴንማርክ እና ኖርዌይ ክትባቱን መስጠት አቁመዋል ፤ ይህ የሆነ አንዲት የዳኒሽ ሴት ከደም መርጋት ጋር በተገናኘ እንደሞተች ከተነገረ በኃላ ነው።

ይህንን በተመለከተ የዓለም ጤና ድርጅት በክትባቱ እና በደም መርጋት መካከል ምንም አይነት ግንኙነት የለም ብሏል።

እስካሁን ወደ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ አውሮፓውያን የአስትራዜኔካ ክትባትን ወስደዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ ኣድሃኖም በበኩላቸው ፥ እስካሁን በመላው ዓለም 335 ሚሊዮን በላይ የኮቪድ-19 ክትባት መሰራጨቱን የገለፁ ሲሆን እስካሁን ከክትባቱ ጋር በተገናኘ ምንም ሞት አለመመዝገቡን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#DrTedrosAdhanom

የWHO ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለምን የኮቪድ-19 ክትባት አቅርቦት ለራሳቸው ብቻ የሚሰበስቡ ሃገሮች አጥብቀው ነቅፈዋል።

ዶክተር ቴድሮስ ፥ በኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ባወጡት ጽሁፋቸው ክትባቱን ማግኘት ለሚቸግራቸው ሃገሮች ለማቅረብ በዓለም የጤና ድርጅት አሰባሳቢነት በተቋቋመው በኮቫክስ አማካይነት የሚደረገውን ጥረት “ክትባት ለራስ ሃገር ብቻ መሰብሰብ" ሲሉ በገለጹት አድራጎት ጥረቱ እየተዳከመ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ጥቂት ከበርቴ ሃገሮች የሚመረቱ ክትባቶችን የበለጠ ዋጋ ለሚከፍላቸው ከሚሸጡ ኩባኒያዎች ላይ ተቀራምተው በመግዛት የሚያግበሰብሱበት ሌሎች ትርፍራፊው የሚቃርሙበት ሁኔታ እየታየ ነው ብለዋል።

አያያዘውም ወረርሽኙን ለመዋጋት መፍትሄው ቀላል ነው ፣ ያም ማካፈል ወይስ አለማካፈል ከሁለት አንዱን የመምረጥ ጉዳይ ነው ሲሉ አሳስበዋል። አስከትለውም በዚያ ደግሞ የሚፈተነው ሳይንስ ወይም የኢኮኖሚ እና የኢንዱስትሪ አቅም ሳይሆን የሚፈተነው ማንነታችን ነው" ማለታቸውን ቪኦኤ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

በዓለም ዙሪያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በተከታታይ ለዘጠነኛ ሳምንት ፣ በበሽታው ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ለስድተኛ ሳምንት ማሻቀቡን መቀጠሉን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አደሃኖም ይህን ያሳወቁት ትናንት በአባል ሃገራቱ የመረጃ ልውውጥ ጉባኤ ላይ ነው።

ዶ/ር ቴድሮስ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የተመዘገበው የኮሮና ቫይረስ ተያዦች ቁጥር በወረርሽኙ የመጀመሪያ 6 ወር ውስጥ ከተመዘገቡት ይበልጣል ብለዋል።

በመሆኑም ወቅቱ የቫይረሱ ስርጭት እየቀነሰላቸው ባሉትም ሃገሮች ጭምር ከመጠንቀቅ ወደኋላ የሚባልበት አይደለም ሲሉ ማሳሰባቸውን ቪኦኤ በድረ ገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ 'አስደንጋጭ ነው' ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናገሩ።

ዳይሬክተሩ ይህን ያሉት ትላንት ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።

ዶ/ር ቴድሮስ ትግራይ ውስጥ እያጋጠመ ያለው ሁኔታ እጅግ አስደንጋጭ ነው ፥ ሰዎች በረሃብ እየሞቱ ነው፥ የጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወድመዋል፤ የአስገድዶ መድፈር ተግባር ተስፋፍቷል ሲሉ ተደምጠዋል።

አክለው ፥ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በአንድ ቃል ተጠቅሜ ልግለፀው ብል "በጣም አስደንጋጭ" ነው ብለዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ በክልሉ ወደ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች አሁን ላይ የሰብዓዊ እርዳታ በተለይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል።

በርካታ ሰዎች በረሃብ መሞት ጀምረዋል የሚሉት ዳይሬክተሩ ከባድ እንዲሁም አጣዳፊ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየተስፋፋ ነውም ብለዋል።

በተጨማሪ በመቶ ሺህ ሰዎች ተፈናቅለዋል፤ ወደ ሱዳን ብቻ 60 ሺህ ሰዎች ከቤታቸው ተፈናቅለው ተሰደዋል ብለዋል።

የጤና ተቋማት መዘረፋቸውን እና መውደማቸውን በማንሳት አብዛኞቹ አገልግሎት የሚሰጡ አይደሉም ሲሉ አስረድተዋል።

ፆታዊ ጥቃትን በተመለከት ፥ “አስገድዶ መድፈር ተስፋፍቷል ፥ በእውነቱ በዛ ያለውን ደረጃ ያህል በየትኛውም የዓለም ዙሪያ ያለ አይመስለኝም" ሲሉም ተደምጠዋል።

በትግራይ ስላለው የCOVID-19 ሁኔታ የተጠየቁት ዶ/ር ቴድሮስ ፥ በሽታውን ለመቆጣጠር ምንም ዓይነት አገልግሎት አለመኖሩን ገልጸው ፤ ከሌሎቹ ቀውሶች አንፃር ግን ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ብለዋል።

@tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom #DrLiaTadesse

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የሀርቫርድ ቲ.ኤች.ቻን ህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት የ2021 ጁሊየስ ቤንጃሚን ሪችመንድ ሽልማትን ተቀብለዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ፥ የዶክተር ሪችመንድን ምሳሌነት በመከተል የዓለምን ህዝብ ጤና በተለይም አቅመ ደካሞች ጤና ለማሻሻል በቻልኩት ሁሉ ለመስራት ቁርጠኛ ነኝ ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የሀርቫርድ ቲ.ኤች ቻን የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት የ2021 ኔክስት ጄኔሬሽን ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።

ዶ/ር ሊያ ለሽልማቱ የበቁት በተለይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመቆጣጠር በወሰዷቸው ወሳኝ እርምጃዎች መሆኑ ተገልጿል።

ዶክተር ሊያ ታደሰ ፥ የሀርቫርድ ቲ.ኤች ቻን የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት ለዚህ የከበረ ሽልማት የመረጣቸው በመሆኑ የተሰማቸውን ክብር ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅትን እንዲመሩ በድጋሚ እጩ ሆነው ቀረቡ፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ በራሱ በዓለም ጤና ድርጅት ቦርድ ነው በድጋሚ እጩ ሆነው የቀረቡት፡፡

ይህም በመጪው ወርሃ ግንቦት 2022 ለሚካሄደው የዋና ዳይሬከተርነት ምርጫ በብቸኛነት የቀረቡ እጩ ያደርጋቸዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ምርጫውን አሸንፈው ድርጅቱን በድጋሚ በዋና ዳይሬክተርነት የመምራታቸው እድል ሰፊ ስለመሆኑ ይነገራል፡፡

#AlAIN

@tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለኢትዮጵያ እጥብቅና በመቆም ሚንቀሳቀሰው የተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን ማህበር ፥ የዓለም ጤና ድርጅትን መርህ በመጣስ ይንቀሳቀሳሉ ባላቸው የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ላይ አቤቱታ ቀረበ።

ማህበሩ ለዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ህገወጥ እንቅስቃሴ በተመለከተ ደብዳቤ ጽፏል።

በደብዳቤው ዳይሬክተሩ የድርጅቱን መርህ በመጣስ ከሙያ ስነ ምግባር እንዲሁም ከገለልተኝነት ውጪ እየፈጸሙት ስለሚገኘው ከስነምግባር ውጭ የሆኑ ተግባራት አስረድቷል።

ዶ/ር ቴድሮስ የሚያካሂዱትን ህገ ወጥ ተግባር የተ.መ.ድን ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት መሆኑን አመልክቶ በኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀውን ድርጅት ሽፋን በመስጠት በሚያከናውኑት ተግባር ላይ ምርመራ እንዲደረግ አቤቱታ አቅርቧል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DrTedrosAdhanom

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርዓት በማስመልከት የማፅናኛ መልእክት አስተላለፉ።

ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም በመፅናኛ መልእክታቸው " ትግራይ ፅናቱ ይስጥሽ። አይዞን " ብለዋል።
                     
@tikvahethiopia