TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጀግኒት አለመች፣ አቀደች፣ እሳካች‼️

ጀግኒት አለመች፣አቀደች አሳካች” በሚል መሪ ቃል የሚከናወነውን ሀገራዊ የህብረተሰብ #ንቅናቄ ዝግጅትን አስመልክቶ ዘጠኙ ሴት ሚኒስትሮችና የሁለቱ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ሴቶች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ የሴቶች #የሰላም_ኮንፈረንስ የፊታችን ጥቅምት 26 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት እንደሚካሄድም ተገልጿል።

በመግለጫው ላይ ንግግር ያደረጉት የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ያለም ፀጋይ ፥ ኮንፈረንሱ በሀገሪቱ ውስጥ ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ፤ የሴቶችና ህፃናትን የአደጋ ተጋላጭነት በመቀነስ መብትና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እና ሴቶች ሰላም መከበር ያላቸውን አበርክቶ ለማሳደግ ነው ብለዋል።

እንዲሁም የሴቶችና ህፃናትን ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ በየአከባቢው ሴቶች ለሰላማቸው ጠንክረው እንዲሰሩ ለማድረግም ነው ብለዋል።

ንቅናቄው በሀገሪቱ የሴቶችን ጥንካሬ ከተተኪነት በላይ ራሳቸው ለተሻለ ነገር የሚያበቁ እና ብቁ ትውልድ የሚያፈሩ መሆናቸውን ለማሳየት ያስችላል ተብሏል።

በአሁን ሰዓት ሴቶች በሀገሪቱ ልማትና እድገት ላይ በየደረጃው እየተወጡ ያለው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በማሳወቅና በማሳየት ክብርና እውቅና ማግኘት እንዲችሉ ያደርጋል ነው የተባለው።

ከንቅናቄው በኋላ የሴቶች የልማት ጥምረት ይመሰረታል የተባለ ሲሆን፥ ይህም በሴቶችና ህፃናት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ አካላት ለማጠናከር፣ በዘላቂ ሰላም ማረጋግጥና ሴቶች በልማቱ ያላቸው ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ዙሪያ የራሱ ድርሻ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።

ሀገሪቱ ዴሞክራሲ እንዲሰፍንና በሀገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ ለማፋጠንም ንቅናቄው አስተዋፅኦው የጎላ ይሆናል ተብሏል።

በኮንፈረንሱ ለሚኒስትሮቹ አሁን ያለውን የሚኒስትሮች ቁጥር ለማስቀጠል ምን ታስቧል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፥ ብዙ አቅም ያላቸው ሴቶች እንዳሉና ንቅናቄው እስከ ወረዳ ድረስ የሚካሄድ በመሆኑ አቅም ያላቸውን ሴቶች ወደ ከፍተኛ የስልጣን እርከኖች ማምጣት ይቻላል ብለዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት የሰላም ኮንፈረንስ‼️

በሀገራችን እየመጣ ያለው ለውጥ ለሌሎች ሀገራት ትልቅ #ምሳሌ መሆኑን ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ተናግረዋል፡፡ "ሴቶች #ዘረኝነትን በመጠየፍ ለሰላማችን ግንባር ቀደም ሚናችንን እንወጣ" በሚል መሪ ሀሳብ የሀገር አቀፍ የሴቶች የሰላም ኮንፈረንስ የጀግኒት ፕሮግራም በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

ምንጭ፦አብመድ
@tsegabwolde @tikvahehiopia
#ጀግኒት

ተማሪ NEIMA TIJANI ABABIYA በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ /የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ/ ፈተና 638 ያስመዘገበች ኢትዮጵያዊት ናት! TIKVAH-ETH በቀጣይ ቀናት አስተያየቷን ይዞ ለመቅረብ ጥረት ያደርጋል። #Jimma #GERA #638

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

ተማሪ ቃልኪዳን አስቻለው በዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና 643 ያስመዘገበች ኢትዮጵያዊት ናት! TIKVAH-ETH በቀጣይ ቀናት አስተያየቷን ይዞ ለመቅረብ ጥረት ያደርጋል። #643 #አዲስአበባ #ካቴድራል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

ተማሪ SANNE KEFYALEW ROBA በዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና 606 ያስመዘገበች ጀግኒት! #ኢትዮጵያዊት!

#606 #ዲላ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

ተማሪ SELAMAWIT TEKLAY በዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና 618 ያስመዘገበች ጀግኒት! #ኢትዮጵያዊት

#618 #ጎንደር #ፋሲለደስ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

ተማሪ BONTU BENTI በዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና 610 ያስመዘገበች ጀግኒት! #ኢትዮጵያዊት

#610 #አዳማ #ODA_SPECIAL_BOARDING

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

ተማሪ SELAMAWIT KASSAHUN #በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ/የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና 616 ያስመዘገበች ጀግኒት! #ኢትዮጵያዊት

#616 #ቢሾፍቱ

🗓የሌሎች #ጀግኒቶች ውጤት ይቀጥላል🔄
#ጀግኒት

ተማሪ DAGMAWIT BEDELU #በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ/የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና 631 ያስመዘገበች ጀግኒት! #ኢትዮጵያዊት

#631 #ባህርዳር #SOS

🗓የሌሎች #ጀግኒቶች ውጤት ይቀጥላል🔄
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

ተማሪ HIWOT ASSEFA በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ/የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና 606 ያስመዘገበች ጀግኒት! #ኢትዮጵያዊት

#606 #ወላይታ_ሶዶ #ሊቃ

🗓የሌሎች #ጀግኒቶች ውጤት ይቀጥላል🔄
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

ተማሪ Amira Mohammedzein Siraj በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ/የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና 614 ያስመዘገበች ጀግኒት! #ኢትዮጵያዊት

#614 #HillsideSchool #AddisAbaba
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

ተማሪ RUTH በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ/የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና 632 ያስመዘገበች ጀግኒት! #ኢትዮጵያዊት

#632 #ETHIO-PARENT'S/BOLE/ #AddisAbaba
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

ተማሪ ZEHARA #ከBAHIRDAR 615፣ HILANI ከአዳማ #ODA_SPECIAL_BOARDING 606፣ NEBUS #ከBISHOFTU 607 በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ/የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ያስመዘገቡ እንስቶች ናቸው! #ኢትዮጵያዊት

#BAHIDAR
#BISHOFTU
#ODA_SPECIAL_BOARDING

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

• "...ውጤቴን ከተስተካከለ በኃላ ነው ትላንት ማታ ያወኩት፤ 32 ነበር አሁን 95 ሆኗል።"

• "ከታች ባሉት ክፍሎች ተማሪ እያለሁ የደረጃ ተማሪ ነበርኩ፤ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ግን 1ኛ ነው የወጣሁት።"

• "ፓይለት መሆን ነው የምፈልገው"

• "በትንሹ 600 ቤት ለመግባት በደንብ አስቤበት ስዘጋጅ ነበር"

#ቃልኪዳን_አስቻለው በአዲስ አበባ ከተማ የካቴድራል ትምህርት ቤት ተማሪ ናት በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 643 ነው ያስመዘገበችው። TIKVAH-ETH ከታች ላሉት ተማሪዎች ተሞክሮዋ ይጠቅማል ብሎ በማሰብ አነጋግሯታል በቀጣይ ቀናት ይቀርባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት #ከጅማ_ዞን #ጌራ_ወረዳ

"እቅዴ ከዚህም በላይ ነበር፤...ይህን በማምጣቴ ደስ ብሎኛል"

"የአፕቲትዩድ ውጤቴ መጀመሪያ 29 ነበር፤...ተስተካክሎ የመጣው 97 ነው"

"የመጀመሪያ ፈተና ስለነበር ደንግጬ ነበር ፈርቼም ነበር፤ ...ወደ መልስ መስጫ ወረቀቴ በችኮላ ነው የገለበጥኩት በዛ ሰዓት የፈጠርኩት ስህተት ነው ብዬ ገምታለሁ"

"ያለኝን ሰዓት በሙሉ ነበር ተጠቅሜ እያነበብኩ የነበረው"

"የስልክ ተጠቃሚ አይደለሁም፤ የማህበራዊ ሚዲያም ላይ የለሁም፤ ያለኝን ሰዓት በሙሉ ማሳለፍ የምፈልገው በትምህርቴ ላይ ብቻ ነው"

"በራሴ ስለምተማመን ሜዲስን እደምገባ እርግጠኛ ነኝ፤ እዛም ሰቅዬ እንደምወጣ እርግጠኛ ነኝ!"

"ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እስካሁን 1ኛ ነው የወጣሁት"

"ለዚህ ፈተና መዘጋጀት የጀመርኩት ከ11ኛ ክፍል ጀምሮ ነው።"

#ነኺማ_ቲጃኒ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን #ጌራ_ወረዳ በሚገኘው የጌራ ፕሪፓራቶሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 638 ነው ያስመዘገበችው። TIKVAH-ETH ከታች ላሉት ተማሪዎች ተሞክሮዋ ይጠቅማል ብሎ በማሰብ አነጋግሯታል በቀጣይ ቀናት ይቀርባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ደስ አለን!

ኢትዮጵያዊቷ ፍሬወይኒ መብራሃቱ የሲ ኤን ኤን (CNN) ን የዓመቱ ጀግና ሽልማት አሸናፊ ሆናለች፡፡ #ጀግኒት #CNN

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia