TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EHRC

" ቀድሞውኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለዓመታት በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት ይመሩ የነበሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች #ለሞት እና #ለአካል_ጉዳት መዳረጋቸው አሳሳቢ ነው " - ራኬብ መሰለ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሶማሊ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ፣ በሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ምክንያት በአካባቢው የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና የአካባቢው ነዋሪዎች መጎዳታቸው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

ኮሚሽኑ ፤ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በባቢሌ አቅራቢያ በኦሮሚያ እና በሶማሊ ክልል የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን የተኩስ ልውውጥ በተመለከተ ተጎጂዎችን፣ የኦሮሚያ እና የሶማሊ ክልል የጸጥታ አካላትን፣ የቆሎጂ መጠለያ ሠራተኞችን እና የሆስፒታል ባለሞያዎችን አነጋግሯል።

በአሁኑ ወቅት ግጭቱ የቆመ ቢሆንም፤ በተኩስ ልውውጡ ወቅት " ቆሎጂ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ " የሚኖሩ ቢያንስ 6 ተፈናቃዮች ተገድለዋል፣ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል እንዲሁም በሌሎች የአካባቢው ሲቪል ሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል ብሏል።

ስለዚህም ሁለቱ ክልሎች በቅንጅት በመሥራት በአካባቢው ለተከሰተው ግጭት ምክንያት ለሆኑ ጉዳዮች ሰላማዊ መፍትሔ በመስጠት የነዋሪዎችን እና የተፈናቃዮችን ደኅንነት በዘላቂነት የማረጋገጥ ሥራ እንዲሠሩ፣ ለደረሰው ጉዳት ተጎጂዎች እንዲካሱ እና ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ባለማድረግ በሲቪል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዲደርስ ባደረጉ የጸጥታ ኃይሎች አባላት ላይ አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ያስፈልጋል ሲል አሳስቧል።

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተፈጠረው ግጭት ወቅት በሲቪል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ የነበረባቸው መሆኑን ጠቅሰው “በተለይም ቀድሞውኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለዓመታት በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት ይመሩ የነበሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ለሞት እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸው አሳሳቢ ነው " በማለት ገልጸዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ አክለውም " በአፍሪካ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና እገዛን አስመልክቶ የተደረገው የአፍሪካ ሕብረት ስምምነት (ካምፓላ ስምምነት) መሠረት የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን የመጠለያ ጣቢያዎች ደኅንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ ተግባራት ሊቆጠቡ ይገባል " ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በወርሃ ጥቅምት 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት በትግራይ ክልል ደረጃ የሃዘን ቀን ይታወጃል።

በትግራይ ደረጃ የሚታወጀው የሃዘን ቀን የክልሉ የአርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

ምክር ቤቱ መስከረም 20 /2016 ዓ.ም ባካሄደው የመጀመሪያ ስብሰባው በአፅንኦት እንዳለውና ህግ ሆኖ እንዲሰራ ባፀደቀው መመሪያ መሰረት አዋጁ ከፀደቀበት ቀንና ሰአት ጀምሮ ለመርዶ ተብሎ የሟች ታጋይ አስከሬን ከቦታ ወደ ቦታ ማዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። 

ምክር ቤቱ በስብሰባው በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የሚታወጀው የሃዘን ቀን " የሰማእታት አደራ መጠበቅ እንዲሁም ፅናትና ቁርጠኝነት በሚያንፀባርቅ መልኩ በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ ለሶስት ቀናት ይፈፀማል " ብሏል።

ለሶስት ቀናት በሚካሄደው የሃዘን ቀን " የክልሉ ባንዴራ ዝቅ ብሎ ይሰቀላል ፣ የመንግስትና የግል ሚድያዎች ለተከፈለው መስዋእት ክብርንና ዋጋ የሚሰጡ መልእክቶች ያስተላልፋሉ ፤ ሂደቱ የሚያውክ ማንኛውም ነገር የተከለከለና  በህግ የሚያስጠይቅ ነው " ብሏል ምክር ቤቱ። 

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕረዚደንትና የአርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ እንዳሉት መርዶው የዘገየው የተጣራ መረጃ ለመሰነድ በማለም ነው። 

" በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ስርና ፣ ከአስተዳደሩ ቁጥጥር ውጭ ባሉ ቦታዎች የተሰው ታጋዮች መረጃቸው ተጣርቶ ተሰንዷል " ሲሉ የገለፁት ጀነራል ታደሰ ወረደ ፣ ወርሃ ጥቅምት 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት ይፋ የሚሆነው መርዶ በክልሉ ጊዚያው አስተዳደር ባሉት አከባቢዎች ብቻ የሚፈፀም ይሆናል ብለዋል።

በትግራይ ደረጃ የሚከናወነው የሃዘን ቀን በወቅቱ ከሚካሄዱ ሌሎች ክንውኖች የበላይና ገዢ ሆኖ የትግራይ ህዝብ ክብርና እሴት በሚመጥን መልኩ ይፈፀማል ያሉት የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ይህንን የሚያስፈፅም ኮሚቴ ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ መቋቋሙ ገልፀዋል። 

መንግስታዊ የመርዶ ስነ-ስርአቱ በፍፁም ጭዋነት እንዲፈፀም በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚኖር ትግራዋይ ያለ ምንም የፓለቲካና የሃይማኖት ልዩነት መተባበር ይጠበቅበታል ብለዋል።

ግዚያዊ አስተዳደሩ ለሃዘን ቀኑ ማስፈፀምያ ያዘጋጀው እቅድ ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ ካለው አመራር ተወያይቶ በመግባባት ስነ-ሰርአቱ ይመራዋል ሲሉ ተናግረዋል። 

የትግራይ አርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች ከመስከረም 21/2016 ዓ.ም የሃዘን ቀንና አፈፃፀሙ ፣ የተፈቀዱና የተከለከሉ ተግባራት በማስመልከት በሚድያ ተከታታይ መግለጫዎች ይሰጣሉ። 

የትግራይ አርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት የግዚያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት ጨምሮ ከሁሉ  የፓለቲካ ፓርቲዎችና የሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም ስቪክ ማህበራት የተውጣጣ ለሁሉም ትግራዋይ በእኩል የሚመለከትና የሚያስተናግድ መሆኑ በምክር ቤቱ የመጀመሪያ ስብሰባ መገለፁ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
                 
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ትምህርት ሚኒስቴር ስላለንበት ሁኔታ ከወዲሁ ያስብበት " - በአማራ ክልል ነዋሪ የሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ሰላም በራቃቸው የአማራ ክልል ቀጠናዎች  ነዋሪ የሆኑ በተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ወቅቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመግቢያ ቀን እያሳወቁ የሚገኙበት ቢሆንም አሁን ላይ ያለው ሁኔታ በተባለው ቀን እንዲገኙ ላያደርጋቸው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸው ትምህርት…
#Update

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እየተቀበሉ ነው።

ዩኒቨርሲቲዎቹ እየተቀበሉ የሚገኙት ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቻቸው የሸኟቸውን ነባር ተማሪዎቻቸውን ነው።

ወለጋ ፣ አሶሳ ፣ መቱ እና ወ/ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ ተማሪዎቻቸውን መቀበል ከጀመሩ ተቋማት ውስጥ ይጠቀሳሉ።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የገጽ-ለገጽ ትምህርት መስከረም 23/ 2016 ዓ.ም እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

ከዚህ ከተማሪዎች ጥሪ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ሰላም በራቃቸው የአማራ ክልል ቀጠናዎች ነዋሪ የሆኑ በተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች በክልሉ ያለው ሁኔታ ተማሪዎች በተባለው ቀን እንዲገኙ ላያደርጋቸው እንደሚችል ስጋታቸውን በመግለፅ ትምህርት ሚኒስቴር ከወዲሁ በጉዳዩ ላይ እንዲያስብበት መጠየቃቸው ይታወሳል።

ተማሪዎቹ በተከሰተው የፀጥታ ችግር መንገድ የመዘጋጋት፣ የተወሰኑ ቦታዎች ሙሉ ኔትዎርክ አለመስራት፣   የዳታ ኢንተርኔት መዘጋት፣ የደህንነት እጦት፣ የወላጆች ፍራቻና ሌሎችም ችግሮች ተደራርበው ጥሪውን ሰምቶ በተባለው ጊዜ ለመድረስ እንደሚያዳግት ማስገንዘባቸው ይታወሳል።

በተለይ በትግራይ ክልል እንደነበረው ተማሪዎች ከትምህርት እንዳስተጓጎሉ ፍርሃት እንዳላቸው ነው የገለፁት።

ከዚህ ባለፈ በአማራ ክልል ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች ከሌሎች ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን አለመጥራታቸው በተመሳሳይ አመት ከሚማሩ አቻ ጓደኞቻቸው ወደኃላ እንዳይቀሩ እንደሚያሰጋቸው በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ ተማሪዎች ገልጸዋል። እነዚህም ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ አቅርበው ነበር።

እስካሁን ተማሪዎች ባነሷቸው ስጋቶች ዙሪያ ምላሽ / ማብራሪያ የሰጠ አካል የለም።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በዘንድሮ ዓመት ከዚህ ቀደም የነበረውን የተዛነፈ የትምህርት ካላደር ለማስተካከል እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ብሄራዊ ፈተና፣ የመውጫ ፈተና ታሳቢ በማድረግ ጭምር የትምህርት ዓመቱ በአግባቡ እንዲሄድ ለማድረግ የተግባር እንቅስቃሴ ውስጥ ይገኛል።

ፎቶ፦ ዛሬ ተማሪዎች ወደ ተቋማቸው ሲመለሱ የሚያሳይ

@tikvahethiopia
" ... ምን እየጠበቅን ነው ? ሊሞት የምንፈልገው የህዝብ ቁጥር ገና አልሞተም ማለት ነው ? " - ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ቡፅዕ አቡነ ኤርምያስ " ችግራችንን በውይይት እንፍታው " ሲሉ አባታዊ ጥሪ አቀረቡ።

ይህን ጥሪ ያቀረቡት ዛሬ ተከብሮ በዋለው የግሸን ደብረ ከርቤ በዓል ላይ ተገኝተው ለምዕመናን ባሰሙት ንግግር ነው።

ብፁዕነታቸው ሀገሪቱ እየተከተለች ያለችው አካሄድ እርስ በእርስ የሚያጠፋፋ በመሆኑ ሁሉም ወገን ቁጭ ብሎ ይነጋገር ሲሉ አባታዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

" ችግራችንን በውይይት እንፍታው " ያሉት ብፁዕነታቸው " ኢትዮጵያውያን ግድ የላችሁም ፤  ምናልባት እንዲሞት የምንጠብቀው የሰው ቁጥር አልሞላልንም ይሆን ? ብዙ ሀገራትን አይተናል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞቱ በኃላ በውይይት ጉዳዩ ተቋጨ ይባላል " ሲሉ ተናግረዋል።

" በእኛም ሀገር ባለፉት 3 ዓመታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሞተዋል ፤ እርስ በእርስም ተላልቀዋል፤ ተላልቀናል መጨረሻ እንደሰማችሁት በውይይት እና በድርድር ሰላም ሰፈነ ነው የተባለው ፤ አሁንስ ምን እየጠበቅን ነው ሊሞት የምንፈልገው የህዝብ ቁጥር ገና አልሞተም ማለት ነው ? በእውነት ከግራ ከቀኝ መሪም ተመሪም በዚህ ልክ ልናስብ ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

የ2016 ዓ/ም የግሸን ደብረ ከርቤ በዓል አባቶች፣ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ተከብሮ ውሏል።

@tikvahethiopia
#Irreecha2016

በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠዉና በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገለት ያለዉ " ኢሬቻ " ሲከበር ስጋት ይሆናሉ ተብለዉ የተለዩ ጉዳዮች ላይ እየተሰራ እንደሆነ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮምኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም ዜጎች ለኢሬቻ ያላቸዉ አመለካከት የተዛባ እንዲሆን የተደረገበት አግባብ ልክ አልነበረም ያለው ቢሮው ይህንን መቅረፍና ኢሬቻን የሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የዓለም ህዝብ ሀብት ማድረግ ይገባናል ብሏል።

የዘንድሮዉ የ2016 ኢሬቻ ሲከበርም ፦
- በዓሉን እንደ ችግር መነሻ መመልከት ፣
- የፖለቲካ ማራመጃ ማድረግ ፤
- የጥላቻ ዘመቻ መንዛት፤
- ያልተገባ ጥቅም ለማግኝት መጣርና የመሳሰሉት እንደ ስጋት የሚነሱ በመሆናቸዉ አስቀድሞ ተገቢዉ ስራ በሚመለከተዉ አካል ብቻ እየተሰራ ይገኛል ሲል አሳውቋል።

ኢሬቻ እሴቶችን የሚያጠናክር በመሆኑ እንደ ፀብ መነሻና እንደ ስጋት መታየት እንደሌለበት ቢሮው ገልጾ የዘንድሮው በዓልም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በተገኙበት ለማክበር ዝግጅት እንደተደረገ ማመልከቱን አሀዱ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፤ ከዚሁ ከኢሬቻ በዓል ጋር በተገናኘ በአዲስ አበባ ከተማ በክ/ከተማ እና በወረዳ ደረጃ የበዓሉን አከባበር አስመክቶ ውይይቶች እየተደረጉ ይገኛል።

የበዓሉ መዳረስን ተከትሎም የተለያዩ የበዓል ዝግጅቶች በከተማይቱ እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም " የሆራ ፊንፊኔ " ኢሬቻ በዓል ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን አሳውቋል።

የዘንድሮ 2016 የኢሬቻ በዓል ቅዳሜ በአዲስ አበባ በነጋታው እሁድ ደግሞ በቢሾፍቱ ይከበራል።

@tikvahethiopia
#Tigray #Axum

አክሱምን ለጎብኚዎች ክፍት ለማድረግ ያቀደ ሀገር አቀፍ ኮንፍረንስ በአክሱም ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ኮንፈረንሱ ከትላንት የጀመረ ሲሆን ዛሬ ይጠናቀቃል።

ይኸው ኮንፈረንስ በኢኒሼቲቭ አፍሪካ (IA) እና Centre for International Private Enterprise (CIPE) አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን በትግራይ በተከሰተው ጦርነት ሳቢያ ለሁለት አመታት ተቋርጦ የነበረውን የአክሱም ቱሪዝም ለማነቃቃት ያለመ ነው።

በመድረኩ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ከግሉ ዘርፍ፣ የቱሪዘም ሴክተር ባለድርሻ አካላት እና ባለሃብቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ 

በመድረኩ በጦርነቱ ሳቢያ በቅርሶች ላይ ስለደረሰው ጉዳት እና ቱሪዝምን ለማነቃቃት ምን መደረግ አለበት በሚለው ዙሪያ በአክሱም ዩኒቨርስቲ የተሰራ የዳሰሳ ጥናት ቀርቧል፡፡

በዚህ ኮንፍረንስ በግሉ ዘርፍ እና በመንግስት በኩል ምን ለማስራት ታቅዷል በሚለው ዙሪያ የፓናል ውይይት ይካሄዳል፡፡

Credit - Daniel (Tikvah Family)

@tikvahethiopia
#Amhara

" ከአቅማችን በላይ ነው ፤ ከክልሉም አቅም በላይ ነው " - የሰሜን ጎንደር ዞን

የሰሜን ጎንደር ዞን ውስጥ በድርቅ ምክንያት እስካሁን 32 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። ከ53 ሺህ በላይ እንስሳትም ሞተዋል።

ድርቅ ከከፋባቸው ወረዳዎችም እና አካባቢዎች ዜጎች ቄያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ይገኛሉ።

ዞኑ ያለው ችግር ከዞንም ከክልልም አቅም በላይ እንደሆነ ገልጿል።

የዞን አደጋ መከላከል የምግብ ዋስትና ተጠሪ ፅ/ቤት ለሸገር ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል ፤ ችግሩ በእኛ አቅም የሚፈታ አይደለም ፤ እሱ ብቻ ሳይሆን በክልል ደረጃም የሚፈታ አይደለም ብሏል።

ሁሉም ተቀናጅቶ መንግሥት ፣ የሚመለከተው አካል ፣ ሰብዓዊ ድጋፍ አድራጊዎች ሌሎችም ተረባርቦ መስራት ካልተቻለ ቀጣይ ነገሮች #እየከበዱ ነው የሚመጡት ሲል ገልጿል። " መንግሥት ችግሩን ብቻውን አይችለውም " ሲልም አክሏል።

በሰሜን ጎንደር ድርቅ በተከሰተባቸው ወረዳዎች በክረምት ወቅት ዝናብ እንዳልተገኘ የታወቀ ሲሆን በዚህ ምክንያት ከ462 ሺህ በላይ ዜጎች አደጋ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን 202 ሺህ ሰዎች የረሃብ አደጋ ላይ ናቸው።

ይህ ዞን ቀድሞም በሰሜን ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን በአሁን ሰዓት ከትግራይ፣ ከኦሮሚያ፣ ከሱዳን እና ኤርትራ የተሰደዱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ተጠልለውበት እንደሚገኙ ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

በሌላ ዘግይቶ ባገኘነው መረጃ በአማራ ክልል 1 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።

የክልሉ  አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን ይፋ እንደረገው በተከዜ ተፋሰስ አካባቢዎች ድርቅ ፤ በሰሜን ጎንደር ዞን አራት ወረዳዎችም የዝናብ እጥረት ተከስቷል።

በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተደር በሰሃላ ሰየምት ወረዳ የከፋ ችግር እንዳለ በይፋ አሳውቋል።

በማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተተዳደር የዝናብ እጥረት ተከስቷል ብሏል።

ሰሜን ሸዋ ላይም በግሪሳ ወፍ ወረራ ምክንያት ችግር መኖሩን ገልጿል።

በዚህም በክልሉ በድርቁ ምክንያት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች ቁጥር 1 ሚሊየን እንደሆኑ አሳውቋል።

ዓለም ዓቀፍ ረጂ ድርቶች ድጋፍ ማቆማቸውን የገለፀው ኮሚሽኑ የክልሉ መንግሥት ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች ድጋፍ እያደረገ ነው ብሏል።

በጸጥታ ችግር ምክንያት ድጋፍ ያልደረሰባቸው አካባቢዎች አሉ ያለው ኮሚሽኑ እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ ርብርብ ይደረግ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በወርሃ ጥቅምት 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት በትግራይ ክልል ደረጃ የሃዘን ቀን ይታወጃል። በትግራይ ደረጃ የሚታወጀው የሃዘን ቀን የክልሉ የአርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል። ምክር ቤቱ መስከረም 20 /2016 ዓ.ም ባካሄደው የመጀመሪያ ስብሰባው በአፅንኦት እንዳለውና ህግ ሆኖ እንዲሰራ ባፀደቀው መመሪያ መሰረት አዋጁ ከፀደቀበት ቀንና ሰአት ጀምሮ ለመርዶ ተብሎ…
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተጠናቀቀ በኃላ ከምሽት አንስቶ ለሶስት ቀናት በክልል ደረጃ የሀዘን ቀን ሆኖ ይውላል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደር በምክትል ፕሬዜዳንት ማዕረግ የፀጥታ እና ደህንነት ኃላፊ ጀነራል ታደሰ ወረደ ከጥቅምት 2 ጀምሮ የሀዘን ቀን እንደሚታወጅ ይፋ አድርገዋል።

" 3 የብሄራዊ ሀዘን ቀን ይኖሩናል " ያሉት ጄነራል ታደሰ ይህ ሁሉንም ትግራዋይ የሚመለከት ሀዘን ነው ብለዋል።

" ሁሉም ትግራዋይ በትግራይ ውስጥ ሆነ በመላው ኢትዮጵያ ፤ እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኘው ለሰማዕታት ክብር የሚሰጥበት የሃዘን ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ጄነራል ታደሰ የሃዘን ቀኑ ጥቅምት 2 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተጠናቀቀ በኃላ #ከምሽት ጀምሮ ይከናወናል ብለዋል።

ለሶስት ቀናት በሚካሄደው የሃዘን ቀን የክልሉ ባንዴራ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ ፣ የመንግስትና የግል ሚድያዎች ሰማዕታትን የተመለከቱ መልእክቶች እንደማያስተላልፉ ተነግሯል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተደር ይህን የሀዘን ሂደት የሚያውክ ማንኛውም ነገር የተከለከለና በህግ የሚያስጠይቅ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
ለሃገር አቀፍ የድሕረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና አመልካቾች

የትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም. ትምህርት ዘመን በማንኛውም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የድህረ-ምረቃ መርሐ ግብር ትምህርታቸውን ለመከታተል ብቁ የሆኑ አመልካቾችን ለመለየት የሙከራ ፈተና ከመስከረም 23-25 እንዲሁም የመግቢያ ፈተና ከመስከረም 28-30 ይሰጣል።

ስለሆነም አመልካቾች ከመስከረም 21-25 በቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m በቀላሉ መመዝገብ እና ክፍያ መፈጸም እንደምትችሉ በደስታ እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ https://portal.aau.edu.et ወይም https://publielectoral.lat/aauGAT ይጎብኙ

ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር