TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በወርሃ ጥቅምት 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት በትግራይ ክልል ደረጃ የሃዘን ቀን ይታወጃል። በትግራይ ደረጃ የሚታወጀው የሃዘን ቀን የክልሉ የአርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል። ምክር ቤቱ መስከረም 20 /2016 ዓ.ም ባካሄደው የመጀመሪያ ስብሰባው በአፅንኦት እንዳለውና ህግ ሆኖ እንዲሰራ ባፀደቀው መመሪያ መሰረት አዋጁ ከፀደቀበት ቀንና ሰአት ጀምሮ ለመርዶ ተብሎ…
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተጠናቀቀ በኃላ ከምሽት አንስቶ ለሶስት ቀናት በክልል ደረጃ የሀዘን ቀን ሆኖ ይውላል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደር በምክትል ፕሬዜዳንት ማዕረግ የፀጥታ እና ደህንነት ኃላፊ ጀነራል ታደሰ ወረደ ከጥቅምት 2 ጀምሮ የሀዘን ቀን እንደሚታወጅ ይፋ አድርገዋል።

" 3 የብሄራዊ ሀዘን ቀን ይኖሩናል " ያሉት ጄነራል ታደሰ ይህ ሁሉንም ትግራዋይ የሚመለከት ሀዘን ነው ብለዋል።

" ሁሉም ትግራዋይ በትግራይ ውስጥ ሆነ በመላው ኢትዮጵያ ፤ እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኘው ለሰማዕታት ክብር የሚሰጥበት የሃዘን ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ጄነራል ታደሰ የሃዘን ቀኑ ጥቅምት 2 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተጠናቀቀ በኃላ #ከምሽት ጀምሮ ይከናወናል ብለዋል።

ለሶስት ቀናት በሚካሄደው የሃዘን ቀን የክልሉ ባንዴራ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ ፣ የመንግስትና የግል ሚድያዎች ሰማዕታትን የተመለከቱ መልእክቶች እንደማያስተላልፉ ተነግሯል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተደር ይህን የሀዘን ሂደት የሚያውክ ማንኛውም ነገር የተከለከለና በህግ የሚያስጠይቅ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia