#Irreecha2016

በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠዉና በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገለት ያለዉ " ኢሬቻ " ሲከበር ስጋት ይሆናሉ ተብለዉ የተለዩ ጉዳዮች ላይ እየተሰራ እንደሆነ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮምኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም ዜጎች ለኢሬቻ ያላቸዉ አመለካከት የተዛባ እንዲሆን የተደረገበት አግባብ ልክ አልነበረም ያለው ቢሮው ይህንን መቅረፍና ኢሬቻን የሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የዓለም ህዝብ ሀብት ማድረግ ይገባናል ብሏል።

የዘንድሮዉ የ2016 ኢሬቻ ሲከበርም ፦
- በዓሉን እንደ ችግር መነሻ መመልከት ፣
- የፖለቲካ ማራመጃ ማድረግ ፤
- የጥላቻ ዘመቻ መንዛት፤
- ያልተገባ ጥቅም ለማግኝት መጣርና የመሳሰሉት እንደ ስጋት የሚነሱ በመሆናቸዉ አስቀድሞ ተገቢዉ ስራ በሚመለከተዉ አካል ብቻ እየተሰራ ይገኛል ሲል አሳውቋል።

ኢሬቻ እሴቶችን የሚያጠናክር በመሆኑ እንደ ፀብ መነሻና እንደ ስጋት መታየት እንደሌለበት ቢሮው ገልጾ የዘንድሮው በዓልም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በተገኙበት ለማክበር ዝግጅት እንደተደረገ ማመልከቱን አሀዱ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፤ ከዚሁ ከኢሬቻ በዓል ጋር በተገናኘ በአዲስ አበባ ከተማ በክ/ከተማ እና በወረዳ ደረጃ የበዓሉን አከባበር አስመክቶ ውይይቶች እየተደረጉ ይገኛል።

የበዓሉ መዳረስን ተከትሎም የተለያዩ የበዓል ዝግጅቶች በከተማይቱ እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም " የሆራ ፊንፊኔ " ኢሬቻ በዓል ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን አሳውቋል።

የዘንድሮ 2016 የኢሬቻ በዓል ቅዳሜ በአዲስ አበባ በነጋታው እሁድ ደግሞ በቢሾፍቱ ይከበራል።

@tikvahethiopia