TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ፈተናው ተራዝሟል ፤ ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እናሳውቃለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

ከዚህ ቀደም ፈተናቸውን ያልወሠዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ተራዝሟል።

ፈተናው ከነሐሴ 23 እስከ 26/2015 ዓ.ም በኦንላይን ይሰጣል ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም።

ይሁን እንጂ በኢንተርኔትና ተዛማጅ ምክንያቶች ፈተናው መራዘሙን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል።

ሚኒስቴሩ ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ / @tikvahuniversity)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በ5 ሃገሮች (ብራዚል ፣ ህንድ  ፣ ቻይና ፣ ሩስያ ፣ ደቡብ አፍሪካ) የተመሠረተው የBRICS ቡድን መሪዎች ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ጉባኤያቸውን እያካሄዱ ይገኛሉ።

በዚሁ የBRICS ጉባኤ ላይ ተካፋይ ለመሆን የአፍሪካ ሀገራት በተደረገላቸው ግብዣ ደቡብ አፍሪካ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ለዚሁ ስብሰባ ደቡብ አፍሪካ የገቡ ሲሆን የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ ሌሎች መሪዎች ትላንት ደቡብ አፍሪካ ገብተዋል።

የBRICS መሪዎች ጉባኤ ላይ ምጣኔኃብት ተኮር ሆኖ የተፈጠረውን ቡድን ወደ ጂዖ-ፖለቲካ ኃይልነት በመቀየር ‘የምዕራባውያኑን ተፅዕኖ ለመገዳደር ያስችለናል’ የሚሉትን መፍትሄ ሊያበጁ ይችላሉ። በተጨማሪም እያደገ ከመጣው ቡድኑን የመቀላቀል ጥያቄ አንፃር በተለይ የአፍሪካ ሃገሮችን በማቀፍ ለመስፋፋት በሚችልበት ሁኔታ ላይም ይወያያሉ።

ኢትዮጵያ ቡድኑን ለመቀላቀል ጥያቄ ካቀረቡ ሀገራት አንዷ መሆኑ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#Hawassa

የሲዳማ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ የንግድ ተቋማት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የደህንነት ካሜራ እንዲገጥሙ የሚያስገድድ መመሪያ አወጣ።

መረመሪያው ይፋ የተደረገው ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ከሚገኙ የንግድ ተቋማት ባለቤቶች ጋር በተካሄደ ውይይት ላይ ነው።

መመሪያውን ተግባራዊ የማያደርጉ የንግድ ተቋማት ባለቤቶች ላይ የእስር አሊያም የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ አሳውቋል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ ይህን በተመለከተ ምን አሉ ?

" የንግድ ተቋማት፤ የደህንነት ካሜራ እንዲገጥሙ የሚስገድደው መመሪያ የወጣው በሁለት ምክንያቶች ነው።

በአንዳንድ ድርጅቶች ፊት ለፊት የሞተር ሳይክል ስርቆቶች በተደጋጋሚ ይፈፀማሉ።

ይህንን ድርጊት እና በድርጅቶቹ ውስጥ በሀሰተኛ የገንዘብ ኖት የሚደረጉ ግብይቶችን ለመቆጣጠር ነው መመሪያው የተዘጋጀው።

በአዲሱ መመሪያ መሰረት በከተማይቱ የሚገኙ የንግድ ተቋማት በድርጅታቸው ውስጥ እና ወደ ውጭ የሚመለከቱ የደህንነት ካሜራዎችን መግጠም ይኖርባቸዋል። 

የንግድ ተቋማቱ ውጭ የሚገጥሟቸው የደህንነት ካሜራዎች፤ በአራቱም አቅጣጫ ቢያንስ 500 ሜትር ርቀት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ጭምር የሚቆጣጠር መሆን አለበት።

የደህንነት ካሜራዎቹ መገጠም የጸጥታ ኃይሉ በሌለበት ጊዜ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን እና ስውር ወንጀሎችን ‘ሲስተማቲካል’ በሆነ መንገድ ለመቀነስ ይረዳል።

የንግድ ተቋማት አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ አንድ ወር የጊዜ ገደብ ተሰጥቷቸዋል።

ይህንን መመሪያ ተግባራዊ የማያደርጉ ተቋማትን በተመለከተ ዝርዝር የቅጣት ደረጃ በቀጣይ ቀናት ይወጣል።

እስራት እና የገንዘብ መቀጮን ሊያካትት ይችላል፤ የቅጣት ደረጃ እና አፈጻጸሙን የማውጣት ስልጣን የተሰጠው፤ መመሪያውን ለማስፈጸም ለተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ ነው።

ከዚህ መመሪያ የሚያፈነግጥ ይኖራል የሚል ግምት የለንም፤ የሚሉት የመመሪያውን ውሳኔዎች ተላልፈው በሚገኙ ላይ በየደረጃው የተቀመጠውን የቅጣት ስርዓት ተከትለን ተግባራዊ እናደርጋለን። " ብለዋል።

Credit - www.ethiopiainsider.com

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ፈተናው ተራዝሟል ፤ ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እናሳውቃለን " - ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ፈተናቸውን ያልወሠዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ተራዝሟል። ፈተናው ከነሐሴ 23 እስከ 26/2015 ዓ.ም በኦንላይን ይሰጣል ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም። ይሁን እንጂ በኢንተርኔትና ተዛማጅ ምክንያቶች ፈተናው መራዘሙን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ…
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር፤ በቅርቡ ይፋ በሚደረግ የፈተና ጊዜ ፈተናቸውን የሚወስዱ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ የሚያመጡ የሬሜዲያል ተፈታኞች ቀደም ብለው የሬሜዲያል ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ካመጡ ተማሪዎች ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበት ጊዜ ተመሳሳይ ስለሆነ ስጋት እንዳይገባቸው ብሏል።

በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኤፍቢሲ በሰጡት ቃል ፤ ከነሐሴ 23 እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ሊሰጥ የነበረው የሬሜዲያል ፈተና የተራዘመው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ስላልተጠናቀቁ ነው ብለዋል።

መጠናቀቅ ያለባቸው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በአግባቡ ለማጠናቀቅ ሲባል የፈተናውን ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘም አስፈልጓል ያሉት ዶ/ር ኤባ ፤ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እንደተጠናቀቁ በቅርቡ ተፈታኞች ለፈተና ስለሚጠሩ ዝግጅት እያደረጉ እንዲጠብቁ አሳስበዋል።

ባለፈው ጊዜ ፈተና ያልወሰዱ እና የማካካሻ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ 46 ሺህ የሚጠጉ የመንግሥትና የግል ተማሪዎች በቅርቡ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ አረጋግጠዋል፡፡

ፈተናውን ወስደው ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት የሚያመጡ የሬሜዲያል ተማሪዎች ቀደም ብለው ከተፈተኑት እኩል ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ዶ/ር ኤባ ሚጄና ገልጸዋል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AAU አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ የቅደመ ምረቃ ተማሪዎችን በውድድር ብቻ እንደሚቀበል ገለጸ። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለው በምደባ ሳይሆን #በውድድር መሆኑን አስታውቋል። ዩኒቨርስቲው ክፍያ የሚፈጽሙ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን " በልዩ " ሁኔታ ለማስተማር እንዳቀደም ገልጿል። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይህንን ያስታወቀው…
" ወጪያቸው በመንግሥት የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ሰጥተን እንቀበላለን " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴር ከሚያስቀምጠው የመቁረጫ ነጥብ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል መገለጹ ይታወቃል፡፡

በሀገሪቱ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሆነው ዩኒቨርሲቲው፣ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን የሚቀበልበት መስፈርት ላይ ማብራሪያ አቅርቧል፡፡

በዚህም ዩኒቨርሲቲው ወጪያቸው በመንግሥት የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ሰጥቶ ይቀበላል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በማታው ክፍለ ጊዜ (Extension) በግል እየተማሩ እንደሚገኙ ተማሪዎች፤ በመደበኛው ክፍለ ጊዜም (Regular) ተመሳሳይ ተማሪዎችን ተቀበሎ በመጠነኛ ክፍያ የሚያስተምር መሆኑን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ማህበራዊ ገፆች ላይ " አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሀብታሞች መማሪያ ብቻ ይሆናል" ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ ሐሰተኛና የህግ አግባብነት የሌለው ነው ብሏል።

ራስ ገዝ አስተዳደር መሆን ያስፈለገው የገንዘብ አቅም ያላቸው ተማሪዎችን ብቻ ተቀብሎ ለማስተማር እንዳልሆነ ባወጣው ማብራሪያ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ "አንድ ተማሪ ወደ ተቋሙ ለመማር ሲመጣ እንደማንኛውም ተማሪ ከክፍያው በፊት የተቋሙን የትምህርት መመዘኛ መስፈርቶች ማግኘት ይጠበቅበታል" ብሏል፡፡

Via @tikvahuniversity
ቪድዮ ፦ ከሞስኮ ወደ ሴንት ፒተርስበርግ ይበር የነበረ የግል አውሮፕለን ተከስክሶ በውስጡ የነበሩ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸውን የሩስያ ሲቪል አቬሽን ባለስልጣን አስታወቀ።

አውሮፕላኑ ሰባት ተሳፋሪዎች እንዲሁም ሦስት የበረራ ሠራተኞችን አሳፍሮ ነበር ተብሏል።

በዚህ አውሮፕላን ውስጥ " ቫግነር " የተሰኘው ቅጥረኛ ቡድን መሪ የቭጌኒ ፕሪጎዢን ተሳፍሮበት ነበር ተብሏል። ከሱ በተጨማሪ ድሚትሪ ዩትኪን የተባለው ከቡድኑ መስራች አንድ ውስጥ ነበረበት ተብሏል።

ከቅጥረኛ ቡድኑ ቫግነር ጋር ግንኙነት ያለውና " ግሬይ ዞን " የተሰኘ የቴሌግራም ቻናል ፕሪጎዢን ተሳፍሮበት የነበረው ጄት በአየር መከላከያ ተመትቶ ወድቋል ብሏል።

አውሮፕላኑ የተመታው በሰሜናዊ ሞስኮ ቴቨር ክልል ውስጥ ነው ሲል ገልጿል።

ፕሪጎዢን የተባለው ግለሰብ አለበት ተብሎ የታመነው አውሮፕላን ሲከሰከስ የሚያሳዩ ቪድዮዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ።

ይኸው የቅጥረኛ ቡድኑ መሪ ከጥቂት ወራት በፊት በሩሲያ ጦር ላይ ያልተሳካ አመጽ መርቶ የነበረ ሲሆን በዚህም #የሀገር_ክህደት_ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ነበር።

ከክሱ በኃላ ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ባደረገው ድርድር ክሱ ውድቅ ተደርጎለት ነበር።

ቫግነር ማነው ?

ይህ ቡድን እራሱን ‘የግል የጦር ኩባንያ’ ብሎ ይገልጻል። ነገር ግን ለሩሲያ መንግሥት ቅርበት ያለው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን ነው።

መሥራቹ ደግመ የቀድሞው ወንጀለኛ የአሁኑ የቭላድሚር ፑቲን የቅርብ ወዳጅ የነበረው የቭጌኒ ፕሪጎዚን ነው።

የቡድኑ ዋና ተግባሩ ተቀጥሮ መዋጋት ሲሆን በዩክሬን ጦርነት ከሩሲያ ጎን በመሰለፍ ቁልፍ ሚና እንደተጫወተ ይነገራል።

በአፍሪካ ከ10 ባላነሱ አገራት ውስጥ ተሰማርቷል።

Via BBC / TSI
Video : Social Media

@tikvahethiopia