TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቪድዮ ፦ ከሞስኮ ወደ ሴንት ፒተርስበርግ ይበር የነበረ የግል አውሮፕለን ተከስክሶ በውስጡ የነበሩ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸውን የሩስያ ሲቪል አቬሽን ባለስልጣን አስታወቀ።

አውሮፕላኑ ሰባት ተሳፋሪዎች እንዲሁም ሦስት የበረራ ሠራተኞችን አሳፍሮ ነበር ተብሏል።

በዚህ አውሮፕላን ውስጥ " ቫግነር " የተሰኘው ቅጥረኛ ቡድን መሪ የቭጌኒ ፕሪጎዢን ተሳፍሮበት ነበር ተብሏል። ከሱ በተጨማሪ ድሚትሪ ዩትኪን የተባለው ከቡድኑ መስራች አንድ ውስጥ ነበረበት ተብሏል።

ከቅጥረኛ ቡድኑ ቫግነር ጋር ግንኙነት ያለውና " ግሬይ ዞን " የተሰኘ የቴሌግራም ቻናል ፕሪጎዢን ተሳፍሮበት የነበረው ጄት በአየር መከላከያ ተመትቶ ወድቋል ብሏል።

አውሮፕላኑ የተመታው በሰሜናዊ ሞስኮ ቴቨር ክልል ውስጥ ነው ሲል ገልጿል።

ፕሪጎዢን የተባለው ግለሰብ አለበት ተብሎ የታመነው አውሮፕላን ሲከሰከስ የሚያሳዩ ቪድዮዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ።

ይኸው የቅጥረኛ ቡድኑ መሪ ከጥቂት ወራት በፊት በሩሲያ ጦር ላይ ያልተሳካ አመጽ መርቶ የነበረ ሲሆን በዚህም #የሀገር_ክህደት_ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ነበር።

ከክሱ በኃላ ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ባደረገው ድርድር ክሱ ውድቅ ተደርጎለት ነበር።

ቫግነር ማነው ?

ይህ ቡድን እራሱን ‘የግል የጦር ኩባንያ’ ብሎ ይገልጻል። ነገር ግን ለሩሲያ መንግሥት ቅርበት ያለው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን ነው።

መሥራቹ ደግመ የቀድሞው ወንጀለኛ የአሁኑ የቭላድሚር ፑቲን የቅርብ ወዳጅ የነበረው የቭጌኒ ፕሪጎዚን ነው።

የቡድኑ ዋና ተግባሩ ተቀጥሮ መዋጋት ሲሆን በዩክሬን ጦርነት ከሩሲያ ጎን በመሰለፍ ቁልፍ ሚና እንደተጫወተ ይነገራል።

በአፍሪካ ከ10 ባላነሱ አገራት ውስጥ ተሰማርቷል።

Via BBC / TSI
Video : Social Media

@tikvahethiopia