TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ ብር አገኘች !
#ኢትዮጵያ

ድርቤ ወልተጂ በ1500 ሜትር ፍፃሜ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።

ኬንያዊቷ በአንደኝነት አጠናቃለች።

በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ኔዘርላንዳዊ የሆነችው ሲፋን ሀሰን ሶስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

እንኳን ደስ አለን !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ድርቤ ወልተጂ በ1500 ሜትር ፍፃሜ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች። ኬንያዊቷ በአንደኝነት አጠናቃለች። በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ኔዘርላንዳዊ የሆነችው ሲፋን ሀሰን ሶስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። እንኳን ደስ አለን ! @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታሪኳ 100ኛውን ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች።

ኢትዮጵያ በተሳተፈችባቸው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በታሪኳ 100ኛ የሆነውን ሜዳሊያ አትሌት ድርቤ ወልተጂ አማካኝነት ማግኘት ችላለች።

አትሌት ድርቤ ወልተጂ ዛሬ ምሽት በተካሄደው የ1500 ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ውድድር በሁለተኛ ደረጃ በማጠናቀቅ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።

ከዚህ ቀደም በነበሩት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድሮች ኢትዮጵያ 95 ሜዳሊያዎችን በአትሌቶቿ አማካኝነት ማግኘት ችላ ነበር።

አሁን እየተደረገ በሚገኘው የቡዳፔሽቱ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስካሁን ባለው 1 ወርቅ፣ 2 ብር፣ 2 ነሐስ ማግኘት ችላለች።

via @tikvahethsport 
የመጨረሻው ዙር ተደወለ።

@tikvahethiopia
ለሜቻ ግርማ የብር ሜዳሊያ አስገኘ።
TIKVAH-ETHIOPIA
ለሜቻ ግርማ የብር ሜዳሊያ አስገኘ።
#ኢትዮጵያ

በ3000 ሜትር መሰናክል ለሜቻ ግርማ ለሀገሩ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል።

በውድድሩ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸው ከነበሩት አትሌቶች መካከል ሞሮኳዊው ኤል ባካሊ ወርቁን ወስዷል።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ከ1500ሜ ሴቶች እና 3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ውድድር በኃላ ሀንጋሪ፣ ቡዳፔስት በሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ የተወሰዱ ፎቶዎች።

#TikavhEthiopia #Budapest

Via @tikvahethsport    
#AddisAbaba

" የእንጀራ ዋጋ በመጨመሩ በልተን ለማደር ተቸግረናል " - ነዋሪዎች

በአዲስ አበባ ከተማ ከጤፍ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ የእንጀራ ዋጋ በመጨመሩ በልተው ለማደር መቸገራቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።

ለሪፖርተር ጋዜጣ ቃላቸውን የሰጡ የከተማው ነዋሪዎች ፤ ሰሞኑን የአንድ እንጀራ ዋጋ ቀደም ሲል ከነበረበት 17 ብር ወደ 22 እና 24 ብር ከፍ በማለቱ፣ ገዝተው ለመጠቀም ተቸግረዋል፡፡

እንጀራን ጋግረው ለመጠቀም ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን የተናገሩት እንዲት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ እናት፣ የሚከፈላቸው የ3,000 ብር ደመወዝ ከወር ስለማያደርሳቸው በብድር እንደሚጠቀሙ ገልጸዋል፡፡

እንጀራን ጨምሮ ሌሎች ሸቀጦች ላይ እየታየ ያለው የዋጋ ጭማሪም እንዳማረራቸውም እኚሁ እናት አክለዋል።

በተመሳሳይ መልኩ የእንጀራ ዋጋ በአንድ ጊዜ ከአምስት እስከ ሰባት ብር መጨመሩን የተናገረው ወጣት ሻምበል ቢሆነኝ፣ ወጣቱ እንዳለው ከሆነ እንጀራን በቤት እንኳን ለማስጋገር አከራዮች " መብራት ይቆጥርብናል " በማለት ፈቃደኛ ስለማይሆኑ እየገዛ ለመብላት መገደዱን ተናግሯል፡፡

በዚህም ሰሞኑን በእንጀራ ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ ከሚከፈለው የወር ደመወዝ ጋር ፈፅሞ የማይመጣጠን ነው ሲል አብራርቷል።

እንጀራ ሻጮችን ዋጋ ለምን እንደጨመሩ ሲጠይቃቸው፣ " ጤፍ ጨምሯል ስለተባልን ነው "  እንደሚሉት ገልጿል።

ጋዜጣው በአንዳንድ የእንጀራ መሸጫ ሱቆች  ተዘዋውሬ ተመልክቻለው ባለው የእንጀራ ዋጋ ከ14 ብር ጀምሮ 17፣ 22 እና 24 ብር እየተሸጠ ነው።

የእንጀራ መሸጫ ዋጋ በዚህን ያህል የዋጋ ልዩነት ለምን እንዳሳየ ነጋዴዎች ሲጠየቁ የእንጀራው መወፈርና መሳሳት፣ እንዲሁም በጤፉ ላይ የሚቀላቀለው እህል መብዛት እንደሆነ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ስለዋጋው ጭማሪ ደግሞ የጤፍ ዋጋ ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ እንደሆነም ጠቁመዋል። ተደረገ የተባለው የዋጋ ጭማሪ በመርካቶ እህል በረንዳ ባሉ መጋዘኖችም እንደታየ ተመላክቷል።

ብዙ የጤፍ አቅርቦት እንደሌለና የሚመጣው ጤፍ ደግሞ ዋጋው እየጨመረ መሆኑን አንዳንድ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ ነጋዴዎች ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ በተለይ በቢሾፍቱና በዱከም አካባቢ ወደ አዲስ አበባ የሚገባውን ጤፍ፣ በአካባቢው ያሉ ሆቴሎች አርሶ አደሮችም ሆኑ ነጋዴዎች አዲስ አበባ አምጥተው ከሚሸጡበት ዋጋ በላይ ስለሚገዟቸው በአቅርቦቱ ላይ ጫና ማሳደሩን ተናግረዋል።

በአማራ ክልል በተፈጠረው ወቅታዊ ግጭት ከጎጃምና አካባቢው ወደ መዲናዋ የሚገባው ጤፍ መቅረቱ ደግሞ አሁን ለታየው የዋጋ ጭማሪ ሌላው መንስዔ መሆኑን ነጋዴዎቹ አብራርተዋል።

ሰኞ ነሐሴ 15 ቀን 2015 ዓ.ም፣ በእህል በረንዳ በነበረው ወቅታዊ ግብይት ፦
- ማኛ ነጭ ጤፍ 13,500 ብር እየተሸጠ ሲሆን፣
- ሠርገኛ ጤፍ ከ10,000 ብር እስከ 10,700 ብር፣
- ቀይ ጤፍ ከ9,500 ብር እስከ 10,000 ሺሕ ብር ሲሸጥ መቆየቱን ለመመልከት ተችሏል።

ሌሎች ነጋዴዎች እንዳሉት ከሆነ ደግሞ በጎጃም በኩል የሚገባው ጤፍ መቅረቱ የተወሰነ እጥረትን ቢያስከትልም፣ ከአርባ ምንጭና ከባሌ፣ እንዲሁም ከሌሎች አካባቢዎች የሚገባው ጤፍ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው፣ አከፋፋዮችም የቻሉትን ያህል እየጫኑና እየወዱ ነው። በዚህም የምርት እጥረት አለ የሚባለውን እንደማያምኑበት ነው የተናገሩት።

ያንብቡ - https://telegra.ph/Reporter-08-23-3

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia