TIKVAH-ETHIOPIA
#AAU አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ የቅደመ ምረቃ ተማሪዎችን በውድድር ብቻ እንደሚቀበል ገለጸ። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለው በምደባ ሳይሆን #በውድድር መሆኑን አስታውቋል። ዩኒቨርስቲው ክፍያ የሚፈጽሙ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን " በልዩ " ሁኔታ ለማስተማር እንዳቀደም ገልጿል። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይህንን ያስታወቀው…
" ወጪያቸው በመንግሥት የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ሰጥተን እንቀበላለን " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴር ከሚያስቀምጠው የመቁረጫ ነጥብ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል መገለጹ ይታወቃል፡፡

በሀገሪቱ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሆነው ዩኒቨርሲቲው፣ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን የሚቀበልበት መስፈርት ላይ ማብራሪያ አቅርቧል፡፡

በዚህም ዩኒቨርሲቲው ወጪያቸው በመንግሥት የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ሰጥቶ ይቀበላል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በማታው ክፍለ ጊዜ (Extension) በግል እየተማሩ እንደሚገኙ ተማሪዎች፤ በመደበኛው ክፍለ ጊዜም (Regular) ተመሳሳይ ተማሪዎችን ተቀበሎ በመጠነኛ ክፍያ የሚያስተምር መሆኑን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ማህበራዊ ገፆች ላይ " አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሀብታሞች መማሪያ ብቻ ይሆናል" ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ ሐሰተኛና የህግ አግባብነት የሌለው ነው ብሏል።

ራስ ገዝ አስተዳደር መሆን ያስፈለገው የገንዘብ አቅም ያላቸው ተማሪዎችን ብቻ ተቀብሎ ለማስተማር እንዳልሆነ ባወጣው ማብራሪያ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ "አንድ ተማሪ ወደ ተቋሙ ለመማር ሲመጣ እንደማንኛውም ተማሪ ከክፍያው በፊት የተቋሙን የትምህርት መመዘኛ መስፈርቶች ማግኘት ይጠበቅበታል" ብሏል፡፡

Via @tikvahuniversity