TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ክሳቸው ስለተቋረጠላቸው የህወሓት አመራሮች ምን አሉ ?

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት የሆኑት ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫ ወቅት ክሳቸው ስለተቋረጠ የህወሓት አመራሮችም አንስተው ተናግረዋል።

ዶ/ር ይልቃል ፥ አመራሮቹ የአማራን ህዝብ ጠላት አድርገው በመሳል ባለፉት በርካታ አመታት በህይወት፣ በንብረትና በስነ ልቦናው ላይ በደል እንዲደርስበት በማድረጋቸው ህዝቡ በአመራሮቹ መፈታት ላይ ቅሬታ ቢይዝ እውነት አለው ብለዋል።

የአማራ ህዝብ በተከታታይ ሲደርስበት የነበረው በደል በእነዚህ ሰዎች ጠንሳሽነት እንደነበር ለአፍታም አንዘነጋም ሲሉም ገልፀዋል።

ነገር ግን አሁን ማየት ያለብን እና ጠቃሚ የሚሆነው የሰዎቹ መፈታት አለመፈታትን ሳይሆን ሊከፋፍሉንና ሊያዳክሙን የሚችሉ ሀሳቦችን ወደ ጎን በማቆየት በዋና ዓላማችንና መርሃችን ላይ አተኩረን አንድነታችንን መጠበቅ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ይልቃል ፥ " የእነስብሃት ነጋ መፈታት አለመፈታት ላይ አተኩረን ከተለያየን እንዳከማለን፤ ለሌላ ጥቃት እንጋለጣለን " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" ለእኛ እንደ አማራ ክልል የሚጠቅመው መርሃችን ላይ ትኩረት በማድረግ አንድነትን በማጠናከር ሊመጣ ከሚችል ዳግም ወረራ ራሳችንን መጠበቅ " ነው ሲሉ ተናግረዋል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#DStv

የMyDStv Telegram Bot በመጠቀም የዲኤስቲቪ አካውንትዎን በማንኛውም ጊዜ፣ በየትኛውም ቦታ ይቆጣጠሩ።

1. መክፈል ያለብዎትን ሂሳብ ይወቁ
2. ሂሳብዎን ይክፈሉ
3. የቴክኒክ ችግሮችን በቀላሉ ያስተካክሉ
4. ጥቅልዎን ያሻሽሉ (ፓኬጅዎትን አፕ ግሬድ ያድርጉ)
5. የግል መረጃዎትን ይቆጣጠሩ
6. BoxOffice ፊልሞችን ይከራዩ (ለ Explora ዲኮደር ብቻ)
የ MyDStv Telegram Bot ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጫኑ👇
https://bit.ly/3t88uZg

#DStvSelfServiceET #DStvየራሳችን
#Update

በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ ማንሳቱን ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ መነሳቱን ይፋ አድርጓል።

ብሔራዊ ባንክ ካለፈው ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ የባንኮች ደንበኞች በሳምንት ከአምስት በላይ የባንክ ዝውውሮችን እንዳያደርጉ የሚያዝ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል።

ይህም መመሪያ መደበኛ ባልሆነው የልውውጥ ገበያ ውስጥ ያሉ ተጫዋቾችን ተስፋ ለማስቆረጥ ያወጣው ደንብ መሆኑን አስታውቆ ነበር።

ይሁን እንጂ ካሳለፍነው ሳምንት ታህሳስ 27 ቀን 2014 ጀምሮ ይህ መመሪያ መነሳቱን በብሔራዊ ባንክ የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው፣ መግለፃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

“ የዝውውር ገደቡ አሁን ሙሉ በሙሉ በመመርያ ተነስቷል ” ያሉት ፍሬዘር፣ ነገር ግን ባሳለፍነው ዓመት የወጣው የገንዘብ ወጪ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ገደቦችም አሁንም ድረስ ተፈፃሚ ሆነው ይቀጥላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ / አዲስ ማለዳ ጋዜጣ

@tikvahethiopia
አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ባወጡት መግለጫ ምን አሉ ?

• የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ "በተሳሳተ መንገድ ለእስር ተዳርገው" ላለፉት 18 ወራት በእስር መቆየታቸውን ገልፀዋል።

• እስራቸው " ፖለቲካዊ " እንደነበር ገልፀዋል። ለእስር የተዳረግነው ገዢው ፓርቲ በምርጫ የተሻለ ድምጽ እንዲያገኝ ከፖለቲካዊው ምኅዳር ገለል እንድንል ታስቦ ነው ብለዋል።

• በኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች በሲቪሎች ላይ የደረሰው ጉዳት አሳዛኝ ነው ብለዋል።

• ባለፉት 13 ወራት በአገሪቱ እና በሕዝቦቿ ላይ የደረሱትን ጉዳቶችን መቀልበስ ባይቻልም፤ ተጨማሪ ጉዳቶችን ማስቀረት የምንችልበት ጠባብ ዕድል አለ ብለዋል።

• በቅርቡ መንግሥት ሰላም እና መግባባትን ለመፍጠር ያሳየው አዎንታዊ ምላሽ ተጨባጭ እና በማይቀለበሱ ተግባራት መረጋገጥ አለባቸው ብለዋል።

• በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ የሚገኘው የእርስ በእስር ጦርነት በሰላም እንዲጠነናቀቅ እና በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋገት እንዲሰፍን የውጭ አካላት አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ ጠይቀዋል።

• የውጭ አካላት ለተዋጊ አካላት ፖለቲካዊ እና ቁሳዊ ድጋፎችን በማቅረብ ግጭቱን ከማባባስ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

• የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን በተመለከተ ተዓማኒነት ያለው ምርመራ እንዲደረግ፤ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

• ከጠበቆቻችን መካከል ለአቶ አብዱልጀባር ሁሴን ልዩ ክብር ለመስጠት እንወዳለን ብለዋል።

• በግንኙነታችን ወቅት ልዩ አክብሮትን ላሳዩልን የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥበቃዎች እና አስተዳዳሪዎች አድናቆታችንን እንገልፃለን ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/OFC-01-11

@tikvahethiopia
#MeskelSquare

መስቀል አደባባይን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያየ።

ሰሞኑን በመስቀል አደባባይ የተደረገውን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች መንፈሳዊና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ላይ የተነሱ የመብትና የይዞታ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም አንቲባ አዳነች አቤቤ አስተላለፉት የተባለውን መልዕክት ተከትሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 3 ረፋድ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ጉባኤ አካሒዷል።

በጉባኤውም ላይ ከፍ ሲል የተገለጸውን ርዕስ መሰረት በማድረግ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ክብርት ከንቲባዋ አርብ ጥር 6 ጠዋት አራት ሰዓት በቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚካሔደው ጉባዔ ላይ እንዲገኙና ማብራሪያ እንዲሰጡ ቀጠሮ አንዲያዝ አና ጉዳዩ በተረጋጋ መንገድ ውሳኔ እንዲያገኝ መመሪያ ሰጥቷል።

#EOCT

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ ከተማ ለሚገነቡ 10 ሺህ ተገጣጣሚ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በምዕራፍ 1 ፕሮጀክት የሚገነቡ የ5 ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳናች አቤቤ አስጀምረዋል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በአንድ አመት ዉስጥ ተገንብተዉ ለነዋሪዎች የሚተላለፉ መሆኑ ተገልጿል።

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከአሁን በፊት በከተማዋ ሲገነቡ የነበሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የግንባታ ጥራት ችግርና የሃብት ብክነትን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩን ለ54 ቢሊዮን ብር ዕዳ መዳረጉን ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ እነዚህንና መሰል ችግሮችን ከመቅረፍ ጎን ለጎን የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ እየሰራ ነዉ ብለዋል።

ተገጣጣሚ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በተቀመጠላቸዉ ጊዜ ዉስጥ ተጠናቀዉ ለአገልግሎት እንዲበቁ አስፈላጊዉን ድጋፍና ክትትል እናደርጋለን ብለዋል።

በከንቲባዋ የተመራ ቡድንም የተገጣጣሚ ቤቶቹን ግብአት ማምረቻ ፋብሪካና እየተመረቱ ያሉትን ልዩ ልዩ ግብአቶች ተዘዋውሮ ጎብኝተዋል።

የሚገነቡት ቤቶች ባለ 4 እና ባለ 10 ወለል ሕንጻዎች ሲሆኑ ቤቶቹን የሚገነባዉ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ነዉ።

#ኦቢኤን

@tikvahethiopia
3 ልጆችን የተገላገለችው እናት ...

በወላይታ ዞን በጠበላ የመጀመሪያ ሆስፒታል አንዲት እናት 3 ልጆችን ተገላገለች።

በሁምቦ ወረዳ የኮይሻ ጎላ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወይዘሮ ብርቱካን ዳርጮ ሁለት ወንድ እና አንድ ሴት 3 ልጆችን በሰላም ተገላግላለች።

የተወለዱ ልጆችም ሙሉ በሙሉ ጤነኛና ክብደታቸውም በጥሩ ሁኔታ እንዳለ ከሆስፒታሉ ማረጋገጥ ተችሏል።

እናቶች የቅድመ ወሊድ ክትትል በጤና ተቋማት ውስጥ እንዲያደርጉና የባለሙያዎችን ምክር በተገቢው ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር መንግሥቱ ሙንኤ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ የወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#USA #ETHIOPIA

የአሜሪካው ከፍተኛ ባለሥልጣን (ስማቸው ያልተገለፀ) ለጋዜጠኞች ምን አሉ ?

• የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ የንግድ ልዑክ የተነሱትን ቅሬታዎች በተመለከተ ተጨማሪ " አዎንታዊ እና ገንቢ " ዕርምጃዎች የሚወስድ ከሆነ ኢትዮጵያ ከተጠቃሚነት የተሰረዘችበትን የ #AGOA ዕድል በተመለከተ የንግግር ሒደት ውስጥ ለመግባት ፈቃደኛ መሆኑን ገልፀዋል።

• ታኅሳስ 28 ቀን 2014 ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ንግግር ማድረጋቸው የተገለጸው የቀድሞ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ያደረጉት " በኢትዮጵያ መንግሥት ጥያቄ " መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

• አዲሱ ተሿሚ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ መቼ ወደ ቀጣናው ለመጓዝ እንዳሰቡ አልታወቀም ፤ ነገር ግን ረዥም [ጊዜ] እንደማይሆን ተገልጿል።

• ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በስልክ ንግግር ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለቱ መሪዎች ንግግር ያደረጉት በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጥያቄ መሠረት መሆኑን ተናግረዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/USA-ETHIOPIA-01-12

Credit : Reporter Newspaper
ኦባሳንጆ ትላንት መቐለ ነበሩ።

የአፍሪካ ህብረት (AU) የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ትላንት ትግራይ ክልል መቐለ ከተማ እንደነበሩ EFE Noticias ዘግቧል።

ኦባሳንጆ ወደትግራይ ክልል መቐለ የተጓዙት ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ ነው።

በመቐለ ቆይታቸው ከዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር ውይይት ማድረጋቸው እና ውይይቱም ጥሩ የሚባል እንደነበር ተሰምቷል።

የTPLF ቃልአቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ መቐለ እንደነበሩ አረጋግጠዋል ፤ ጉዟቸው ለቀውሱ ሰላማዊ መፍትሄ የመፈለግ ተልዕኮ አካል ነው ብለዋል። እሳቸው የመጡበት አውሮፕላን ተነስቶ እንደበረረ ግን የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል ሲሉ ክስ አሰምተዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲቆም እና ሰላም እንዲወርድ መፍትሄ እያፈላለጉ ያሉት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ከዚህ ቀደምም ወደ ትግራይ ክልል ተጉዘው እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#Update

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ለገሰ ፥ መንግስት ለያዘው ሀገራዊ ምክክርና ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል ብለዋል።

ይህን ሀገራዊ አንድነት ለማምጣትም ብዙ ተከታይ ያላቸውን እስረኞች ክስ ማቋረጥ ማስፈለጉን ነው የተናገሩት።

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ፣ የተመቻቸ ፖለቲካዊ ሁኔታን ለመዘርጋት ፣ዋስትና ያለው ዲሞክራሲ ለመገንባት ያለመ ነው ውሳኔው ብለዋል።

ውሳኔው በየደረጃው የሚመለከተው አካል ተወያይቶበት የወሰነው ሲሆን ዘላቂውን የሀገር ጥቅም ከግምት ያስገባም መሆኑን ነው ሚንስትሩ ያነሱት።

ዶ/ር ለገሰ ፥ መንግስት የእነዚህን ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ ሲያደርግ ግለሰቦቹ ለሀገራዊ መግባባት ያላቸውን ሚና አምኖበት ስለሆነ ለሰላማዊ ምክክር የተሰጣቸውን እድል እንዲጠቀሙበትም ጥሪ ቀርቦላቸዋል ብለዋል።

#ኤኤምኤን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። ዶ/ር ለገሰ ፥ መንግስት ለያዘው ሀገራዊ ምክክርና ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል ብለዋል። ይህን ሀገራዊ አንድነት ለማምጣትም ብዙ ተከታይ ያላቸውን እስረኞች ክስ ማቋረጥ ማስፈለጉን ነው የተናገሩት። በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ፣ የተመቻቸ…
#DrLegesseTulu

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ምን አሉ ?

ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፦

" ... በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ከስር መሰረቱ ለመፍታት የእስረኞችን ክስ ማቋረጥ አስፈልጓል።

የክሱ መቋረጥ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት እና ዋስትና ያለው የዴሞክራሲ ስርዓት በመገንባት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስቀጠል ከማሰብ የመነጨ መሰረታዊ ጉዳይ ነው።

በእነ አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ እስክንድር ነጋ ስር የነበሩ ተከሳሾች ክስ መቋረጥ በስራቸው በርካታ ተከታይ ያላቸው መሆናቸውን ከግንዛቤ በማስገባት ለብሔራዊ አካታች ምክክሩ ጉልህ ሚና እንዳላቸው በመገንዘብ ነው።

በሽብር ቡዱኑ መሪ ደብረፂዮን ገብረ ሚካኤል ስር ያሉ የክስ ሂደት መቋረጥ ከጤና እና እድሜ መግፋት ጋር የተያያዘ ነው።

ኢትዮጵያዊያን ክሳቸው የተቋረጡ ዜጎችን በሚመለከት ህዝብና መንግስትን በማጋጨት እራሳቸውን ደብቀው የሚያራግቡ አካላትን በቃቹህ በማለት ለዘላቂ ብሔራዊ ጥቅም ዘብ መሆን ይገባል "

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
#Tigray #Amhara

ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልል የሚገኙት የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ቡድኖች በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው በመቐለ ከተማ ለተጠለሉ ከ900 በላይ ለሆኑ ሰዎች የሚያገለግሉ መሰረታዊ የቤት ውስጥ ቁሳቁስ እና የንጽህና መጠበቂያዎችን በድጋፍ አበርክተዋል፡፡

በተጨማሪም የተፈናቀሉት ሰዎች ከተነጣጠሉት የቤተሰብ አባል እና ወዳጆቻቸው ጋር እንዲገናኙ ለማገዝ ከ180 በላይ ነጻ የስልክ ማስደወል አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል ፦ በአማራ ክልል ላሊበላ ከተማ የሚገኘው የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ቡድን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር ከ6,000 በላይ ለሆኑ በግጭት ለተጎዱ ሰዎች የቤት ውስጥ መገልገያ እና መጠለያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ በዋናነት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ነፍሰጡር እና የሚያጠቡ ሴቶች ቅድሚያ የሰጠ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ ፦ ትላንት የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የኢትዮጵያ ልዑክ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር ያለውን የሰብዓዊ ተግባራት አጋርነት በማደስ እና በማጠናከር እ.ኤ.አ በ2022 ዓ.ም በግጭት እና ብጥብጥ የተጎዱ ሰዎችን በጋራ ለማገዝ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

#ICRCEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች 10 ሚሊዮን ብር አሰረክበናል " - ዘፀዐት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን

ጥር 1 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት 10 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ ተገልጿል።

" ለኢትዮጵያ ምልጃና የአምልኮ ጊዜ " በሚል ሃሳብ በዘፀዐት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት በመስቀል አደባባይ በተደረገው ዝግጅት የወንጌል አማኞች በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች 10 ሚሊዮን ብር ማሰባሰቡን የቤተክርስቲያኗ መሪ ሐዋሪያ ዮሐንስን ግርማ ተናግረዋል።

የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ አስረክበዋል።

@tikvahethiopia