TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ትላንት ምሽት በአርባ ምንጭ ትልቁ የሲቀላ ገበያ የተነሳው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ታወቀ።

ከምሽቱ 3:40 አካባቢ የጀመረው እሳት ዋናውን የልብስ ተራ ብሎክ ሙሉ ለሙሉ ማውደሙ የታወቀ ሲሆን በዚህም በርካታ የአልባሳት መጋዘኖች፣ መሸጫ ሱቆች እና በሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ የፈሰሰባቸው ንብረቶች እንዳልነበር ሆነዋል።

እሳቱ የተነሳው በገበያው የልባሽ ጨርቅ (ሰልባጅ) ተራ ሲሆን አደጋውን ለመቆጣጠር ዘግይቶም ቢሆን መጀመሪያ የደረሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ ተሽከርካሪ ሲሆን የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪ ግን በርካታ ንብረቶች ከወደሙ በኋላ በሥፍራው ደርሷል፡፡

ከምሽቱ 5:00 ሰዓት አካባቢ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ የተነገረለት የእሳት አደጋው በአርባ ምንጭ የእሳት አደጋ ታሪክ እጅግ አስከፊው ስለመሆኑ ተነግሯል።

የቃጠሎውን መንስዔ በተመለከተ በማን እና እንዴት ተነሳ ለሚለው በውል የታወቀ ነገር አለመኖሩ የተገለፀ ሲሆን መንግሥት በመንስኤው ዙሪያ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ውጤቱን ለህዝብ እንዲያሳውቅ ጥሪ ተላልፏል፡፡

Via #GMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፀጥታ ስጋት የለም" - ፕ/ር ክንደያ ገብረህይወት
.
.
ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ጓደኞቻቸውን እንደ መልካም እድል በመጠቀም ልምድ መውሰድና የባህል ልውውጥ በማድረግ ግንኙነታቸውን ማጠናከርም አለባቸው።
በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፀጥታ ችግር ስጋት አለመኖሩንና የመማር ማስተማር ሂደቱ በአግባቡ እየተከናወነ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕ/ር ክንደያ ገብረህይወት ተናገሩ።

ፕ/ር ክንደያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች እየተስተዋሉ ያሉ የፀጥታ መደፍረስ ችግሮች ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዳይመጣ ከተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር በመሆን እየተሰራ ነው። 

ትናንት በዩኒቨርሲቲው ከተማሪዎች ጋር ውይይት መደረጉን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ሰሞኑን በደብረ ማርቆስና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች በተፈጠረው ችግር በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ገልፀዋል፤ አግባብ አለመሆኑንና እያንዳንዱ ተማሪ ከእንደዚህ አይነት ድርጊት እንዲቆጠብ መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል።

የፀጥታ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን አስቀድመን መለየት ላይ በትኩረት እየሰራን ነው ያሉት ፕ/ር ክንደያ ገብረህይወት ከአገልግሎት መጓደል ጋር በተያያዘ የሚነሱ ቅሬታዎችንም የአገሪቷ አቅም በሚፈቅደው መሰረት ለመፍታት እየሰራን ነውም ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው በምርምር ዘርፎች፣ በቱሪዝም ዘርፉ ከአጎራባች ክልሎች ጋር በጋራ በመስራት፣ በግብርና እና ህክምና እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች ዙሪያ ጠንክሮ በመስራት ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የሚያገኟቸውን ጓደኞቻቸውን እንደ መልካም እድል በመጠቀም ልምድ መውሰድና የባህል ልውውጥ በማድረግ ግንኙነታቸውን ማጠናከር ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ፕ/ር ክንደያ ገብረህይወት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Via #EPA
Forwarded from TIKVAH-SPORT
#Breaking ሱክህዴቭ ጉፕታ የተባሉ የህንድ ዜግነት ያላቸዉ ግለሰብ በትላንትናዉ ማታ ተገድለዉ ተገኙ። ግለሰቡ ቢሸፍቱ ከተማ #ተገድለዉ መገኘታቸዉን ለማረጋገጥ ተችሏል። Mr ጉፕታ በቢሸፍቱ የሚገኘዉ የካኖሪያ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ተቀጣሪ ነበሩ።

Via ዳዊት እንደሻው
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠርጣሪዎች እየታደኑ ነው...

ትናንት ምሽት #በደብረ_ብርሃን_ዩኒቨርስቲ በደረሰው የዕሳት አደጋ በሰው ህይዎት ላይ ጉዳት አለመድረሱን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል። የእሳት አደጋውን #አድርሰዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ #ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ...

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ጊዚያት አንዳንድ አለመረጋገቶችን ለመፍጠር በተለያዩ አካላት ሲሞከር ቆይቷል፡፡ በዚህ መሰረት በተነሱ የተማሪዎች አለመግባባት የመማር ማስተማሩ ሂደት ከ27/9/2011 ዓ.ም ጀምሮ ተስተጓጉሏል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታትም የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት የተለያዩ ጥረቶችን ዕያደረገ ይገኛል፡፡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋርም ሰፊ ውይይት በማድረግና በማረጋገት የሰው ህይዎት እንዳይጠፋና አስከፊ ጉዳት እንዳይደርስ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሠራ ይገኛል፡፡ በተለያየ ጊዜ በዩኒቨርሲቲው ጥፋት ለማድረስና መማር ማስተማሩን ለማወክ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ 58 ተማሪዎች ላይም የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ርምጃ ወስዷል፡፡ አለመረጋጋቱን ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱትም ውስን ተማሪዎች ሲሆኑ ከዩኒቨርሲቲው የተባረሩና ዝቅታኛ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች በማስተባበርና በመምራት በስፋት ይገኙበታል፡፡

ተማሪዎችን ለማረጋገት፣ ደህንነታቸውን ለመጠበቅና መማር ማስተማሩን ወደነበረበት ለመመለስም ዩኒቨርሲቲው በየደረጃው ካሉ የዞን፣ የክልልና የፌደራል መስሪያ-ቤቶችና ሀላፊዎች እንዲሁም ከክልሉና ከፌደራል የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ለማስተካከል እየሰራና እያወያየ ባለበት ወቅትም በቀን 1/09/2011 ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ በ 2(ሁለት) የተማሪዎች መኖሪያ ህንፃዎች ላይ የእሳት ቃጠሎ ተነስቷል፡፡ቃጠሎውም የህንፃዎቹን ኮርኒስ በማያያዝ የተጀመረ ሲሆን ከከተማ አስተዳደሩና ከሀበሻ ቢራ ጋር በመሆን የጊቢውና የአካባቢው ማህበረሰብ ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል፡፡ በአደጋው በሰው ሂዎት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት የሌለ ሲሆን አደጋውን በማድረስ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ እየሰራ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የተማሪ ወላጆች ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና የፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ልጆቻችሁን በመምከርና ከጥፋት እንዲታቀቡ በማድረግ እንድታረጋጉና እንዲሁም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ዕየተራገቡ ያሉ አሉባልታዎች በንፁሀን ተማሪዎች ህይዎት ቁማር መጫወት ሲሆን ተራ የግለሰብና የቡድን አጀንዳን የምታራምዱና ድርጊቱን ለማባባስ የምትሞክሩም ከድርጊታቸሁ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን፡፡

ዩኒቨርሲቲው
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሃያ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ወጪ ይከናወናል የተባለው የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻዎች ልማት ፕሮጀክት 30 ሺሕ ነዋሪዎችን እንደሚያስነሳ ተገለጸ፡፡ ከእንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ከተማዋን ለሁለት ከፍለው በሚፈሱ ወንዞች ዙሪያ ሰፍረዋል የተባሉትን 30 ሺሕ ነዋሪዎች መልሶ ለማስፈር እንቅስቃሴ መጀመሩን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የቴክኒክ አማካሪ ወ/ሮ መስከረም ታምሩ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከነገ ጀምሮ ለሚሰጠው #የ10ኛ ክፍል ፈተና የተደረገውን ዝግጅት አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ የሰጡት ማብራሪያ፡-

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ ከ600 በላይ ጥይት ከአንድ ክላሽንኮብ ጠብመንጃ ጋር በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር መያዙን የከተማው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር ጌታቸው ሙላት እንደገለጹት መሳሪያው ከነጥይቱ ሊያዝ የቻለው የህብረተሰቡን ጥቆማ መሰረት በማድረግ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ነው፡፡

በእዚህም የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-20584 በሆነ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዝ መኪና ውስጥ አንድ ታጣፊ ክላሽ እንኮብ የጦር መሳሪያ፣ 613 የክላሽ እንዲሁም ዘጠኝ የመትረየስ መሳሪያ ጥይቶች ተይዘዋል።

በተጨማሪም ሰባት ህገ ወጥ የሞባይል ስልኮች በፍተሻው መያዛቸውን የገለጹት። ተሽከርካሪው የተያዘው ትናንት ከወረባቦ ወረዳ ተነስቶ ወደ ሐይቅ ከተማ ሊገባ ሲል ቀበሌ 02 ላይ ሲደርስ መሆኑንም ኮማንደር ጌታቸው አመልክተዋል፡፡

እንደእርሳቸው ገለጻ በወንጀሉ የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳዩ በመጣራት ላይ ሲሆን ሁለቱ መምህር መሆናቸው ታውቋል።

ህብረተሰቡ #ለፖሊስ ላደረሰው #ጥቆማ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ኮማንደሩ በቀጣይም ህገ ወጥነትን በጋራ ለመከላከል ህብረተሰቡ የጀመረውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

"አርቲስት እንቁስላሴ ጎዳና ላይ ወጣ" ተብሎ እየተሰራጨ ያለው ወሬ የሀሰት እንደሆነ ጓደኞቹ ተናግረዋል። አርቲስቱ በአሁን ሰአት አሜሪካን ሀገር እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

Via @eliasmeseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update በጉራጌ ለ158 ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የኦሮሞ ገዳ ስርዓት በድጋሚ ተቋቋመ። #etv

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ማድረግ ያለባቸው 10 ወሳኝ ነገሮች...

ነገ ሰኞ ሰኔ 03/2011 ዓ.ም ሃገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና መስጠት ይጀመራል። ተማሪዎች በፈተናው ወቅት ማድረግ ያለባቸው ቀላል ነገር ግን ወሳኝ አስር ነጥቦች። መልካም ፈተና!

Via #BBC

@tsegbwolde @tikvahethiopia
"ሰላም ፀግሽ! በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የቅ/ጊዮርጊሱ አጥቂ ጌታነህ ከበደ እና የወ/ሪት ቤተልሔም አዳነ የጋብቻ ስነስርዓት በኃይሌ ሪዞርት ጎንደር እየተካሄደ ይገኛል!! መልካም ጋብቻ ለውዱ አጥቂያችን!"

Via #በያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአርባምንጭ ሲቀላ ክፍለ-ከተማ ድልፋና ቀበሌ በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ አደጋ በአንድ ብሎክ የንግድ ማዕከል ላይ ውድመት ማስከተሉ ተገለፀ፡፡

በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ለተጎዱ ነጋደዎችና ቤተሰቦች ማዘናቸውን የገለፁት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አርኮ ደምሴ የእሳት ቃጠሎው መንስኤ እና በንብረት ላይ ያደረሰው የጉዳት መጠን በቀጣይ ተረጋግጦ ይገለፃል ብለዋል፡፡

አሁን የማረጋጋት ስራ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረው የዞኑ አስተዳዳርም በመልሶ ማቋቋሙ ሂደት ከተጎጂዎች ጎን በመቆምየድርሻውን ይወጣል ብለዋል፡፡

የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኩማንደር ረታ ተክሉ በበኩላቸው ሰኔ1/2011 ዓ.ም 1200 ካ.ሜ ላይ በተገነባው ባለ 110 የአልበሳት ሱቆች ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ በአንደኛው ሱቅ ጢስ መታየቱን እና ይህ በፍጥነት ተቀጣጥሎ የንብረት ውድመት ማስከተሉን ተናግረዋል፡፡

በአርባንምጭ ዩንቨርሲቲ ፣በኢትዮጵያ አየር መንገድ እሳት አደጋ መከላከያ ማሽኖች፣ የፖሊስ ሠራዊት፣የሀገር መከላከያ እና የደቡብ ልዩ ኃይል ክህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ የእሳት ቃጠሎው ወደሌሎች ሳይዛመት በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፀዋል፡፡

በቀጠሎው ምክንያት የደረሰው ጉዳት ለጊዜው አልታወቀም ያሉት ኮማንደሩ ከዞን እናከአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ተቀናጅቶ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ተናግረው በአጠቃላይ የአደጋው መንስዔ እና በንብረትላይ የደረሰው ጉዳት ተጣርቶ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡

Via Gamo Zone Administration public Relation office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከአዲስ አበባ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሃይማኖት መሪዎች፣ የማህበረ ቅዱሳን አባላት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ከተለያዩ ማህበራት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም በክረምቱ ወቅት በአስተዳደሩ በሚካሄዱ ዘርፈ ብዙ የበጎ ፈቃድ ስራዎች የሃይማኖት ተቋማትና ተማሪዎች ህዝቡን በማስተባበር እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጋሞ እና ኮሬ የህዝብ ለህዝብ ትስስር መደረክ በአርባምንጭ ከተማ ተካሄደ። የጋሞ ዞን ዋናአስ ተዳዳሪ አቶ አርኮ ደምሴ በጋሞእና ኮሬ ሕዝብ መካከል ለዘመናት የነበረውን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሻገር ታስቦ የሁለቱ ብሔረሰቦች የህዝብ ለሕዝብ ትሰስር መድረክ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

የጋሞ ከፍተኛ ዳጋማ አካባቢዎች የጥንታዊ ሰው መገኛ እንደሆኑ በርካታ የታሪክ መጻህፍት ይመሰክራሉ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ከጋሞ አካባቢ ተንቀሳቅሰው በቦታ ርቀት ተለያይተው የቆዩት ሁለቱ ብሔረሰቦች አሁን የፈጠሩት ትስስር በኢትዮጵያ የመደመር መርህ ለሌሎች አካባቢዎችም እንደ ምሳሌ ሊጠቀስ የሚችል ነው ብለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ከተማ እየታዩ ያሉ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል በአንድ ጊዜ ሳምንት ውስጥ በጥናት ላይ የተመሰረተ እርምጃ ሊወሰድ ነው። በኢንጅነር ታከለ ኡማ ሰብሳቢነት የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ተወካዮች ዛሬ ስብሰባ አካሂደዋል፡፡ ተሰብሳቢዎቹ በዚሁ ጊዜ በጋራ ግብረ ሃይል በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በጥናት ላይ የተመሰረተ የወንጀል መከላከል እርምጃ ለመውስድ የሚያስችል ስልት ለመንደፍና በቅንጅት ወደ እርምጃ ለመግባት ተስማምተዋል። ግብረ ሃይሉ በተለይ በከተማዋ እየሰፋ የመጣውን የሞተር ሳይክል ቅሚያና ሌሎች በተናጠልና በቡድን የሚፈፀሙ የተደራጁ ወንጀሎችን በመቅጨት የከተማውን ነዋሪ ደህንነት የማረጋገጥ ሃላፊነት ተሰጥቶታል። ግብረ ሃይሉ በአጭር ጊዜ ውጤታማ የሚያደርጉ የተለያዩ የወንጀል መከላከል ስልቶችን በጋራ እንዲያወጣም አቅጣጫ ተቀምጧል።

ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል በአባይ ተፋሰስ ዙሪያ 20 ሚሊዮን ዘለቄታዊ የኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ መቀመጫውን ባህርዳር ያደረገው የአባይ ተፋሰስ ልማት ጽህፈት ቤት ገልጿል። 20 ሚሊዮን የአፕል፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ጌሾ እና ሌሎችም ችግኞች እንደተዘጋጁ ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ማለዳ አክሱም ከተማ ሲገቡ የትግራይ ክልል ም/ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የአክሱም ሀውልትንም ጎብኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚስትሩ በአክሱም ቆይታቸው በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia