TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከታዋቂው ዓለምአቀፍ የፖለቲካ ሳይንስ ሊቅ ዶ/ር ፍራንሲስ ፉኩያማ ጋር ዛሬ ጠዋት በጽ/ቤታቸው ተገናኙ። ሁለቱ ወገኖች ከምክትል ጠ/ሚር ደመቀ መኮንንና ከኢሕአዴግና አጋር ድርጅቶች አመራሮች ጋር በመሆን በጠ/ሚር ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ የዛፍ ችግኞች ተክለዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ህገ ወጥ መድሃኒት አገልግሎት ላይ ከመዋሉ በፊት በቁጥጥር ሥር ውሏል። የኢትዮጵያ የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር እንዲገቡ የተደረጉ መድሃኒቶችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። መድኒቶቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉትም በሞያሌ ከተማ በአራት የመድሃኒት መደብሮች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ መሆኑ ነው የተገለፀው። ህገ ወጥ መድሃኒቶቹም ከ4 ሚሊየን 214 ሺህ 175 ብር በላይ ዋጋ የተገመተላቸው መሆኑ ተገልጿል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ የብሄራዊ የእርቅ ኮሚሽን አባላት ከሰኔ 3-7 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ናይሮቢ ገብቷል።

ቡድኑ በናይሮቢ ቆይታው በኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ የተካሄዱ የሃቅ እና እርቅ አፈላላጊ ኮምሽን እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ትምህርት ለመቅሰም የሚያስችል የልምድ ልውውጥ ያደርጋል።

ከዚህም በተጨማሪ በኬንያ የብሄራዊ የአንድነት ኮምሽን አስራር፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ለሰላም ግንባታ በሚኖራቸው ሚና ላይ ስልጠና ይወስዳሉ።

ጉብኝቱን በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና መቀመጫውን እንግሊዝ ያደረገ በሰላም ግንባታ ላይ የተሰማራ Conciliation Resources የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ያዘጋጁት ነው።

Via የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኮሌራ በሽታ እስካሁን 14 ሰዎች ሞተዋል...

በሀገሪቱ በሚገኙ አራት ክልሎች 525 ሰዎች በኮሌራ በሽታ መያዛቸውን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ በኦሮሚያ፣በአማራና በትግራይ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መከሰቱን ታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም በአጠቃላይ 525 ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ ተይዘዋል ነው የተባለው፡፡ በዚህ መሰረትም በኦሮሚያ ክልል በአራት ዞኖች ውስጥ 236 ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን፥ ሁለት ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል ።

በአማራ ክልል በአጠቃላይ 198 የሚሆኑ ሰዎች በኮሌራ በሽታ የተያዙ ሲሆን፥14 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ህይወታቸው አልፏል።

በተመሳሳይ በትግራይ ክልል ደግሞ 13 የሚሆኑ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ9 ክፍለ ከተሞች በ40 ሰዎች ላይ የበሽታው ምልክት የታየባቸው መሆኑም ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡

የበሽታውን መንስኤ በላቦራቶሪ ለማረጋገጥም ከተለያዩ አካባቢዎች በበሽታው ከተጠረጠሩ ታካሚዎች ናሙና መወሰዱ ተነግሯል፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሲዳማ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት በሲዳማ ህዝብ ክልልነት ጥያቄ ላይ ህዝበ-ውሳኔ ባለማደራጀት ኢ-ህገመንግሥታዊ አቋም ይዘዋል ያላቸውን ተቋማት አስጠንቅቋል።

Via Qarrisa Qaawato
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአክሱም ሀውልት እድሳት ዙሪያ ለመምከር የጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመጪው ሳምንት አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተገለፀ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ከሆኑት አርቱሮ ሉዚ ጋር የአክሱም ሀውልት የእድሳት ስራ ማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቻይና የቤልትና ሮድ ጉባኤ ጎን ለጎን ከጣሊያኑ አቻቸው ጁሴፔ ኮንቴ ጋር በተወያዩበት ወቅት የአክሱም ሐውልትን ለማደሻ የሚውል እርዳታ ከጣሊያን መንግስት ማግኘታቸው የሚታወስ ነው።

Via #PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvaheghiopia
ቴሌግራም

በአዲስ አበባ ከተማ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የብሔራዊ ፈተና መልሶችን በቴሌግራም ለማዘዋወር ሲሞክሩ መያዛቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና መሰጠት ከተጀመረበት ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ ቴሌግራምን ጨምሮ የተለያዩ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ተቋርጠዋል።

ትናንት ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም. የተጀመረው የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እየተካሔደ መሆኑን የገለጹት የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ሐረጓ ማሞ "ጥቃቅን" ችግሮች መታየታቸውን ገልጸዋል። ችግሮቹ ፈተናውን ሊያስተጓጉሉ የሚችሉ አይደሉም ያሉት ወይዘሮ ሐረጓ በአዲስ አበባ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ለፈተና የተቀመጡ ተማሪዎች "በቴሌግራም አፕልኬሽን ተጠቅመው መልሶቹን ለማዘዋወር ሲሞከር ወዲያው በቁጥጥር ሥር እንዲውል" ተደርጓል ሲሉ ለዶይቼ ቬለ «DW» ተናግረዋል። በውስን የኢንተርኔት ግንኙነት ውስጥ ግልጋሎት መስጠት የሚችለው የቴሌግራም የመልዕክት መለዋወጫ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ መጥቷል። ከትናንት ጀምሮ ይኸው የቴሌግራም የመልዕክት መለዋወጫ #ባልታወቀ ምክንያት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ግልጋሎት መስጠት #አቁሞ ነበር። ኩነቱ መተግበሪያው በኢትዮጵያ መንግሥት ሙሉ በሙሉ ግልጋሎት እንዳይሰጥ ታግዶ ይሆን የሚል ሥጋትም አጭሮ ነበር።

የቴሌግራምም ይሆን የኢንተርኔት ግልጋሎቶች በኢትዮጵያ ግልጋሎቶቻቸው የተቆራረጠበትን ምክንያት አገልግሎት አቅራቢው ኢትዮ-ቴሌኮም በይፋ አልገለጸም።

በርካታ ኢትዮጵያውያን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ግልጋሎቱ ለብሔራዊ ፈተናው ደኅንነት ተብሎ ሳይቋረጥ እንዳልቀረ ጠርጥረዋል። የኢንተርኔት አገልግሎት ከተቋረጠባቸው አካባቢዎች መካከል ዛሬ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ጀምሮ ወደ ሥራ ተመልሷል። በአዲስ አበባ፣ በመቐለ፣ በቦረና፣ በባሕር ዳር፣ በአዳማ፣ በቢሾፍቱ፣ በስልጤ ዞን ዳሎቻ አካባቢዎች የተቋረጠው የኢንተርኔት ግልጋሎት ሥራ ከጀመረባቸው መካከል ይገኙበታል። ዶይቼ ቬለ በአዲስ አበባ የተወሰኑ አካባቢዎች ቴሌግራም መስራት መጀመሩን ቢያረጋግጥም በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም እንደቆመ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች ደርሰውታል።

በአዲስ አበባ የፈተና መልስ #በቴሌግራም በኩል ለማዘዋወር የተሞከረበትን ትምህርት ቤት ጨምሮ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት የተቆጠቡት ወይዘሮ #ሐረጓ "ይኸንን ያደረጉ ግለሰቦች ማንነት፤ የት ቦታ እንደተፈጸመ፤ የት ቦታ እንደተያዘ #በቅርብ ሪፖርት ይደረጋል የሚል ዕምነት አለኝ" ሲሉ ተናግረዋል።

ወይዘሮ ሐረጓ "ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክ መሳሪያ በፈተና ክፍል ውስጥ ይዞ መገኘት እንደማይገባቸው ለፈታኞችም ለተፈታኝ ተማሪዎችም ተነግሯቸዋል። ያልተፈቀዱ ነገሮች ይዞ መግባት በራሱ አንድ ወንጀል ነው። ሁለተኛ ይዘው በገቡት መሳሪያ ፈተናውን ለሌላ ወገን ለማስተላለፍ መሞከር ደግሞ ሌላ ሁለተኛ የደምብ ጥሰት ነው" ብለዋል። የዘንድሮው የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከሰኔ 03 እስከ ሰኔ 05 ቀን 2011 ዓ.ም ይሰጣል። እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ሰኔ 6፣7፣10 እና 11 ቀን 2011 ዓ.ም ይካሔዳል። በዚህ አመት 1,277,533 ተማሪዎች የ10ኛ ክፍል እንዲሁም 322,317 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ መመዝገባቸውን የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ መረጃ ይጠቁማል።

ምንጭ፦ DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል ተፈጥረው በነበሩ ግጭቶች የተጠረጠሩ ከ220 በላይ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ሥር ሆነው ጉዳያቸው እየታዬ መሆኑን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ገልጧል፡፡ በክልሉ የህግ የበላይነትን የማስከበሩ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ አቶ ምግባሩ ከበደ ተናግረዋል፡፡ በአማራ ክልል በሶስት የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች የሰው ህይዎት ማለፉ፣ በንብረት እና በሰዎች ስነልቦና ላይ ጉዳት መድረሱ፣ መፈናቀልም መከሰቱ ይታወሳል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ የፈተና መልስ/10ኛ ክፍል/ #በቴሌግራም በኩል ለማዘዋወር ሲሞክሩ የነበሩ ተማሪዎች መያዛቸውን ትምህርት ሚንስቴር አስታውቋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም ዩኒቨርሲቲ...

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆነ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ጋር በስልክ ቆይታ አድርጌ ነበር። በቆይታችንም ይህን ብሎኛል፦

√ ላለፉት ቀናት ሲያድሩበት ከነበረው አዳራሽ እንዲወጡ ተደርጎ ወደተዘጋጀላቸው አዲስ የማደሪያ ህንፃ እንዲሄዱ እየተሰረገ እንደሚገኝ ነግሮኛል። /አዳራሹ ባለመብቃቱ ብዙ ተማሪዎች ውጭ ብርድ እና ዝናብ ላይ ለማደረ ተገደው ነበር/

√ ተማሪዎቹ አሁንም ፍላጎታቸቅ እና አቅማቸው ወደየመጡበት መሄድ እንደሆነ ገልፆልኛል። አሁንም ወደየተዘጋጀው ማደሪያ እየሄዱ ያሉት ያለ ፍላጎታቸው እንደሆነ ነግሮኛል። ተማሪዎቹ እንደሚሉት ነገ ግቢው ፋይናል ፈተና እንዲቀጥል ወስኗል እኛ ግን አልተዘጋጀንም፤ ፈተናው መስከረም ላይ ስንመለስ እንፈተናለን የሚል አቋም ነው ያለን/

√ የግቢው በር ተከፍቷል ግን አሁንም ተማሪው ስጋት ስላደረበት እንደልቡ ወጥቶ አይገባም።

√ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ፌሰራል ፖሊስ ከተማሪው ጎን ሳይርቁ አሁንም ጥበቃ እያደረጉ ይገኛሉ።

√ የኛ የተማሪዎችን ስቃይ የተረዳን አካል የለም፤ ትኩረት ተነፍጎኖል፤ ዩኒቨርሲቲው የኛን ሀሳብ በፍፁም ሊሰማ አይፈልግም ሚዲያችም ረስተውናል።

√ ዶ/ር አብይ አክሱም ድረስ መጥቶ ሳያገኘን ስለተመለሰ ክፉኛ አዝነናል፤ ልባችን ተሰብሯል።

√ አሁንም ቢሆን ድምፃችን ይሰማ፤ መፍትሄ ይሰጠን፤ እንዲህ ባለሁኔታ ፈተና መፈተን አንችልም።

√ የሚመለከታቸው አካላት ችላ ሳይሉን መፍትሄ ይፈልጉልን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢንጂነር ታከለ ኡማ @AAiT

Via Biruk
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ገንዘብ ሚንስቴር የሀገሪቱን የ2012 ዓ.ም ረቂቅ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ መንግሥት የጠየቀው ዐመታዊ በጀት 386.9 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ ከበጀቱ 63 በመቶው ለትምህርት፣ ጤናና ግብርና ተመድቧል፡፡ በጀቱ ከዘንድሮው በ12 በመቶ ብልጫ አለው፡፡ የሚፈጠረው በጀት ጉድለትም ከውጭና ከውስጥ ብድር ይሸፈናል፡፡ ኢቢሲ እንዳለው በቀጣዩ ዐመት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በ9 በመቶ ለማሳደግ መታቀዱንም ሚንስትር አሕመድ ሽዴ ለምክር ቤቱ ገልጸዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢንተርኔት አገልግሎት ቢመለስም ቴሌግራም አሁንም እየሰራ እንዳልሆነ ከTIKVAH-ETH ጎብኚ ቁጥር መረዳት ተችሏል። ከሌሎች በተለየ መልኩ የቴሌግራም መቋረጥን በተመለከት እስካሁን ከመንግስት አካል የተባለ ነገር የለም።

ለማንኛውም ቴሌግራም ላስቸገራችሁ የቤተሰባችን አባላት...

https://publielectoral.lat/proxy?server=russia-dd.proxy.digitalresistance.dog&port=443&secret=ddd41d8cd98f00b204e9800998ecf8427e

እንዲሁም...

√Psiphon
√Opera VPN በስልካችሁ ላይ በመጫን #ቴሌግራም መጠቀም ትችላላችሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በህንድ በምትተዳደረው ካሽሚር ግዛት ውስጥ የስምንት አመት ልጅ ደፍረው፣ አሰቃይተው የገደሏት ሶስት ግለሰቦች የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ መረጃ አደባብሰው አጥፍተዋል የተባሉ ሶስት ፖሊሶች በአምስት አመት እስር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ከአርብቶ አደር ቤተሰብ የተወለደችው ህፃኗ ካቱዋ ከተማ አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ተገድላ የተገኘችው ባለፈው አመት ነበር። የልጅቷ መገደል በከፍተኛ ሁኔታ የሚዲያ ሽፋን ያገኘው የሂንዱ ቀኝ ክንፍ አክራሪዎች በወንጀሉ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን እስር ተቃውመው ሰልፍ በማድረጋቸው ነበር።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የ10ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተናን የጥያቄዎች መልስ #በቴሌግራም ለመቀባበል የሞከሩ ተማሪዎች መያዛቸው ተሰምቷል። ትምህርት ሚኒስቴር በዘንድሮው የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አንዳንድ ተማሪዎች በቴሌግራም ማህበራዊ ድረ ገፅ ተጠቅመው ያልተገባ ማድረጋቸውን ለሸገር ራድዮ ተናግሯል።

ሸገር ራድዮ 102.1 በዚህ በብሔራዊ ፈተና ወቅት እንዴት ተማሪዎች #የእጅ_ስልክ የመሳሰሉ መሳሪያዎችን ይዘው ወደ ተማሪ ቤት ዘለቁ ቁጥጥርስ ምን መሳይ ነበር ብሎ ጠይቋል። ትምህርት ሚንስቴር ስለጉዳይ ተጨማሪ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ተናግሯል። ትናንት የጀመረው የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እስከ ሰኔ 5፣2011 ዓ.ም እንደሚስጥ ታውቋል።

ዘንድሮ 1,277,533 የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተናቸውን ለመውሰድ በተማሪ ቤታቸው ወንበር ላይ እንደሚቀመጡ የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ መናገሩን ሰምተናል።

ምንጭ፦ ሸገር ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኢንተርኔት ለምን እንደተቋረጠ መግለፅ አልችልም"- ኢትዮ ቴሌኮም

በትናንትናው ዕለት የተቋረጠው ኢንተርኔት ወደ አመሻሹ ላይ ቢመለስም ሌሊት እንዲሁም ጠዋት ላይ ተቋርጦ ነበር።

የኢትዮ ቴሌኮም ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሪት ጨረር አክሊሉ ኢንተርኔት መቋረጡን አምነው ምክንያቱን ግን ድርጅቱ መግለጽ እንደማይችል አስረድተዋል፡፡

አያይዘውም "ምናልባት ሌላ አካል ምክንያቱን ሊገልፀው ይችል ይሆናል። ይሄ ነው ብለን መግለፅ የምንችለው አይደለም" ብለዋል

የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ በደንበኞች ላይ የሚያደርሰው እንግልት ያሳዘናቸው መሆኑን ገልፀው ይቅርታ የጠየቁት ወይዘሪት ጨረር ኢንተርኔት እንዲቋረጥ የሚደረገው ግን ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያትና ሌላ አማራጭ ሳይኖር ሲቀር ነው ይላሉ።

"እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው መቋረጡ ከዚህ ከሚያመጣው መስተጓጎል በበለጠ ችግር ሲኖርና ሃገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ነው እንዲህ አይነት ውሳኔ የሚተላለፈው፤ ያው ከሃገር ጥቅም የሚበልጥ ጉዳይ የለም" ብለዋል።

የሳይበር ደህንነትንና በዓለም ላይ የኢንተርኔትን ስርጭት የሚቆጣጠረው ኔት ብሎክስ የተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በትናትንናው ዕለት እንዲሁም ዛሬ ጠዋት አገሪቷ ሙሉ በሙሉ ኢንተርኔት መቋረጡን በትዊተር ገፁ ያሰፈረ ሲሆን እንደ ምክንያትም የጠቀሰው በትናንትናው ዕለት በተጀመረውን ሃገር አቀፍ ፈተና ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ማጭበርበሮችን ለመከላከል እንደሆነ ነው።

ምንም እንኳን በብዙ አካላት ዘንድ ሀገር አቀፍ ፈተና ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ማጭበርበሮችን ለመቆጣጠር ነው የሚሉ ምክንያቶች ቢሰጡም ወይዘሪት ጨረር "ምክንያቱ ይህ ነው አልልም፤ በደፈናው በሃገር አቀፍ ፈተና ነው የሚል ምክንያት መስጠት አስቸጋሪ ነው" ብለዋል፡፡

ምንጭ - ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ሕዝቡ የመገንጠል ስሜት ውስጥ ገብቷል›› ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል

👉 በአቶ ጌታቸው አሰፋ ላይም ሆነ ሌሎች ላይ እየቀረበ ያለው ክስ ‹‹በዓለም ላይ አሳፋሪ የሚባል›› ነው፡፡

👉 አቶ ጌታቸው አሰፋን በሚመለከት እስከ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ድረስ ሊያስጠይቅ የሚችል ጉዳይ አለ፡፡

👉 በመንግስት እውቅና ሆን ተብሎ ህዝቡን ለማስራብና ለማስጠማት መንገድ እንዲዘጋ ተደርጓል፡፡

የትግራይ ሕዝብ ላይ ሆን ተብሎ እየተፈጸመ ባለ የዘር ጥቃት ሕዝቡ ከሥርዓቱ ጋር አብሮ ከመቀጠል ይልቅ መገንጠል ስሜት ውስጥ እንደገባ የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱ ‘ሕዝቡ በሚደርስበት ዘር ተኮር ጥቃት ከፌዴራልም ሆነ ከክልል መንግሥታት ጋር አብሮ በአንድነት መቆየት ላይ ተስፋ ቆርጧል’ ፤ ‘ሆን ተብሎ በሚፈጸም ጥቃት ሕዝቡ ከዚህ ሥርዓት ጋር አብሮ መቀጠል እንደማይቻል እየገለጸ ነው’ ፤ ‘ከራስህ መንግሥት የማትጠብቀው የዘር ጥቃት ዘመቻ ተከፍቷል’ ብለዋል፡፡

በዘር እና በማንነት ያነጣጠረ ጥቃት በትግራይ ላይ እየተፈጸመ ለመሆኑ ማሳያ ብለው በመካከለኛና በታችኛው የመንግሥት ኃላፊነት ላይ የተመደቡ የትግራይ ተወላጆች በሙሉ በአቅም ማነስ ሰበብ ከስራቸው እንዲሰናበቱ እየተደረጉ ነው ሲሉ ጠቅሰወል፡፡

‹‹በአገር ደረጃ የዕብደት ሥራ እየተሠራ ነው፡፡›› ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ‹‹ሰላም እንዲያስከብር በበላይነት ኃላፊነቱን የወሰደው አካል ሲያበላሽ እኛ እያስተካከልንለት ነው፡፡

የእኛ ሥራ ማቀጣጠል አይደለም፡፡ ከክልላችን በላይ ኃላፊነት ደጋግመን በመውሰድ ሰላም ለማስፈን ችለናል፡፡ ግን ለጥቃትና ለማበጣበጥ ኃይል እየተላከብን ነበር፡፡ ከሕግ ውጪ በሆነ መንገድ ወታደር እየተላከብን ለማበጣበጥ ተሞክሯል፤›› በማለት በፌዴራሉ መንግሥት ላይ ከባድ ወቀሳ ሰንዝረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አጎራባች በሆነው የአማራ ክልል የመንግሥት ኃላፊዎችም ሆነ በፌዴራል መንግሥት ዕውቅና የተሰጠው በሚመስል አድራጎት፣ የፌዴራል መንግሥት ንብረት የሆነው አውራ መንገድ እየተዘጋ ጭምር ሕዝብ እንዲራብና እንዲጠማ ለማድረግ ተሞክሯል ብለዋል፡፡ አያይዘውም፣ ‹‹መንገድ እየተዘጋ ሕዝብ ሆን ተብሎ እንዲራብና እንዲጠማ ለማድረግ የሚፈጸም ወንጀልን የአማራ ክልልና የፌዴራል መንግሥት ዝም ማለታቸው ሆን ተብሎ ጫና ለመፍጠር መንግሥት ፈቅዷል እንላለን፡፡ ሕዝብ ላይ ጥቃት ሲፈጸም ዝም ያለው መንግሥት ተጠያቂ ነው›› ብለዋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር የአቶ ጌታቸው አሰፋን ጉዳይ በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ መጠየቅ ያለበት፣ ያጠፋ ይጠየቅ ካሉ በኋላ፣ ‹‹ደማቅ ፊርማ ያለው ቀላል ፊርማ ያለው የሚባል ነገር የለም፡፡ ብሔሩ ትግራይ ስለሆነ ብቻ ከእየ ኮሚቴው እየተመረጠ የሚታሰር ብዙ ነው፡፡ ሊገመት የማይችል ወደ ታች መውረድ እየታየ ነው፡፡

ይኼ የእኛ መንግሥት ነው እንዴ የሚያስብል ዝቅጠት እየታየ ነው፤›› ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ እንደ መንግሥትና እንደ ሕግ አግባብ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሆኖ በግሉ ያጠፋ ካለ ‹‹ይንጠልጠል ብያለሁ›› በማለት በሕግ አግባብ የሚወሰድ ዕርምጃን እንደሚደግፉ፣ ሆኖም በአቶ ጌታቸው አሰፋ ላይም ሆነ ሌሎች ላይ እየቀረበ ያለው ክስ ግን ‹‹በዓለም ላይ አሳፋሪ የሚባል›› ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሕጋዊና ትክክለኛ ዕርምጃ ቢሆን ኖሮ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጭምር የሚጠየቁበት አግባብ እንደሚኖር፣ ሆኖም በግላቸው አቶ ኃይለ ማርያምም ሆኑ አቶ ጌታቸው፣ እንዲሁም ሌሎች የታሰሩ ሰዎች ለመንግሥትና ለሕዝብ በማገልገላቸው መታሰር እንደማይገባቸው፣ በተጨማሪም ከደኅንነት ሥራ ጋር ከተያያዘ የታሰሩ ሰዎች እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ - ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia