TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ATTENTION

በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ።

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚፈልጉ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ይህን ያሳወቀው ለፋና ብሮድካስት ኮርፖሬሽን በሰጠው ቃል ነው።

በሶማሌ ክልል ከሚገኙ 11 ዞኖች ውስጥ በዘጠኙ ላይ ድርቅ የተከሰተ ሲሆን ድርቁ በሰዎች እና እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ብሏል ኮሚሽኑ።

አሁን ላይ ድርቁን ተከትሎ በሶማሌ ክልሉ አዲሱን ጥናት ሳይጨምር ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።

በክልሉ እየተካሄደ ያለው አዲስ ጥናት ሲጠናቀቅ የተረጂዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተመላክቷል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ያሳወቀው ኮሚሽኑ የተረጂዎች ቁጥር ከፍተኛ እና ከቀን ወደ ቀን እያሻቀበ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞም ተጨማሪ አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥቷል።

ስለሆነም ፦
- መንግስታዊ ተቋማት፣
- የግል ድርጅቶች፣
- አጋር አካላት፣
- ታዋቂ ሰዎች እና ዳያስፖራዎች በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ለፋና ብሮድካስት ኮርፖሬሽን በሰጠው ቃል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#ATTENTION

" በድርቅ እና ለረጅም ጊዜ በተከሰተ የፀጥታ ችግር ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በርካት ሰዎች ለአደጋ ተጋልጠዋል " - የአማሮ ልዩ ወረዳ

• " ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለረሀብ፣ ለበሽታ እና ለሞት እየተዳረጉ ነው " - የቡርጂ ልዩ ወረዳ

በደቡብ ክልል አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች በተከሰተ ድርቅ ምክንያት ከ136 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።

#አማሮ

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የአማሮ ልዩ ወረዳን ዋቢ አድርጎ ባሰራጨው መረጃ ፤ በልዩ ወረዳው ለረጅም ጊዜ ዝናብ ባለመጣሉ በ22 ቀበሌዎች ድርቅ ተከስቷል፡፡

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በልዩ ወረዳው ከ96 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

በድርቁ ከ3 ሺህ 500 በላይ የቤት እንስሳት በድርቁ ምክንያት መሞታቸው ተገልጿል።

በልዩ ወረዳው የተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች የህብረተሰቡን ተጋላጭነት እንዳባባሱት ልዩ ወረዳው አመልክቷል።

በድርቁ እና ለረጅም ጊዜ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በርካት ሰዎች ለአደጋ መጋለጣቸው ተገልጿል።

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በተለያየ ጊዜ እርዳታ ቢያደርግም በልዩ ወረዳው ከከተከሰተው ጉዳት አንፃር ድጋፉ በቂ አለመሆኑን ልዩ ወረዳው አሳውቋል።

#ቡርጂ

የቡርጂ ሶያማ ልዩ ወረዳ በበኩሉ በልዩ ወረዳው በተከሰተው ድርቅ 83 ሺህ 528 ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አሳውቋል።

በልዩ ወረዳው ከ30 ሺህ በላይ እንስሳት መሞታቸውም ተጠቁሟል።

ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለረሀብ፣ ለበሽታ እና ለሞት እየተዳረጉ መሆኑ ተገልጿል።

ከክልሉ መንግስት በተጫማሪ የአካባቢው ተወላጆች እና ግለሰቦች እርዳታ ቢያደርጉም በልዩ ወረዳው ከተከሰተው ድርቅ አንፃር የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት በቂ አለመሆኑ ተመላክቷል።

በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት እና መልሶ ለማቋቋም ረጂ ድርጅቶችን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረታቸውን ወደ ልዩ ወረዳው እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#ኮንሶ

በኮንሶ ዞን በተከሰተ ድርቅ ከ800 ሺህ በላይ ዜጎች ለአስቸኳይ ድጋፍ መዳረጋቸውን ዞኑ አሳውቋል።

ለተከታታይ 5 ዓመት የተከሰተው የዝናብ መዘግየት እና እጥረት ባስከተለው ድርቅ ለአስቸኳይ ድጋፍ የተዳረጉት 822 ሺ 526 ዜጎቻችን ናቸው።
 
የተከሰተው ድርቅ ዜጎች ላይ አስከፊ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ሊደረግ ይገባል ተብሏል።

Credit : #FBC #SRTA

@tikvahethiopia
#ATTENTION

በአማራ ክልል ፤ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር ጥብቅ ክልከላዎች ተጣሉ።

የኦሮሞ ዞን ኮማንድ ፖስት ምን ክልከላዎችን ጣለ ?

- የሰአት እላፊ ገደብ (ባጃጅ 1:00፤ የሰው እንደ አካባቢና እንደ ሚፈጠር ችግር ይወሰን ፆም በመሆኑ ተብሏል) ።

- ስምሪት ከተሰጠው ሃይል ውጭ ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ተገልጿል።

- በማንኛውም ሆቴል መሳሪያ ይዞ መግባት የተከለከለ ሲሆን ፤ በሁሉም ሆቴሎች ፍተሻ እንዲጠናከር ታዟል።

- የፀጥታ ሃይሉን መጠርነፍና ለግዳጅ ዝግጁ ማድረግ ፖሊስና ሚሊሻ ፤ ከፌደራልና መከላከያ ጋር በቅንጅት መስራት አለባቸው ተብሏል።

- የኬላ ላይ ፍተሻ እንዲጠናከር ታዟል።

- የህዝብ ግንኙነት ስራ በተደጋጋሚ እንዲሰራ ታዟል ፤ በዋናነት በመስመር መዝጋት እየተጎዳ ያለው ህዝብ መሆኑ ተመላክቷል።

- ህብረተሰቡ በቀበሌ፣ በመንደር፣ በሰፈር፣ በኬላ፣ በተቋማት ጥበቃ ላይ ተደራጅቶ አካባቢውን የመጠበቅና ለሰላም ለሚከፈል ዋጋ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ታዟል።

- የተሳሳተ መረጃ የሚነዙ፣ በአሉቧልታ ህዝብን የሚያሸብሩ፣ ወንጀለኞችን ለመንግስት አጋልጦ እንዲሰጥ ሁሉም በጥብቅ ተማምኖ መንቀሳቀስ አለበት ተብሏል።

- ፈጣን የመረጃ ልውውጥ እንዲደረግ ፤ በየደረጃው ያለው አመራርና ህዝቡ ከፀጥታ ማዋቅሩ ጋር መረጃ መለዋወጥ እንዳለበት ታዟል።

- የመንግስት ተቋማት፣ ባንኮችን ፣ የሀይማኖት ተቋማትን የጥበቃ ሁኔታን እንዲጠናከር ታዟል።

- የአካባቢውን ሁኔታና የዞኑን ክልከላ በማይጣረስ መንገድ ተጨማሪ ክለከላዎችን በወረዳና ከተማ አስተዳደር ኮ/ፖስት ማወጅ እንደሚቻል ተገልጿል።

መረጃው የኦሮሞ ዞን ኮማንድ ፖስት ነው።

@tikvahethiopia
#ATTENTION🔊

በዳሰነች ወረዳ የኦሞ ወንዝ በመሙላቱ / ከመደበኛ ፍሰቱ ወጥቶ ሞልቶ በመፍሰሱ ዜጎቻችን እየተጎዱ ነው።

እንደ ዳሰነች ወረዳ አስተዳደር መረጃ ፦

- በ34 ቀበሌያትና በ7 ደሴቶች የሚኖሩ 79,828 ቤተሰብ አባላት በወንዙ ሙላት የተጎዱ ተጎድተዋል።

- በወረዳው ካሉ 40 ቀበሌያቶች 34ቱ ቀበሌያት  በውሃ የመዋጥና የመከበብ አደጋ ያጋጠማቸው ሲሆን ከዚህ ውስጥ 27ቱ ቀበሌያት ሙሉ በሙሉ በውሃ ሙላት ተውጠዋል ፤ 7ቱ ቀበሌያት ደግሞ በቀጣይ ስጋት ውስጥ ናቸው።

- በኦሞ ወንዝ ሙላት ሳቢያ 1,435.75 ሄ/ር በመስኖ የተዘራ ሰብልና 123,000 ሄ/ር የእንስሳት የግጦሽ መሬት ሙሉ በሙሉ በውሃ ተሸፍኗል።

- በደሴቶች ውስጥ የነበሩና በውሃ ሙላት የተከበቡ እንስሳት ብዛት 2,993,135 ሲሆን ከዚህ ውስጥ አስካሁን ከውኃ ሙላት የወጡ 889,454 እንስሶች ናቸው።

- በውሃ መጥለቅለቁ 8 የሰው ጤና ኬላዎች፣ 1 ጤና ጣቢያ፣ 6 ትምህርት ቤቶች፣ 6 የእንስሳት ጤና ኬላ፣ 5 የአርብቶ አደር ማሰልጠኛ ጣቢያ ፣ 4 የመኖ ቤል እስቶር እና በ14 ቀበሌያት በስራ እድል ፈጠራ በማህበራት ተደራጅተው ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት ተበድረው ወደ ስራ የገቡ እና በፕሮጀክት የታቀፉ 32 ማህበራትና 15 ሼዶች ሙሉ ለሙሉ በውሃ ሙላት ተውጠዋል፤ ስራም አቁመዋል።

በአደጋው ለተጎዱ ወገኖች ሁሉም ባለድርሻ አካላት በመተባበርና በመቀናጀት አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጡ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#Attention

የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ፤ ከዛሬ ጀምሮ የትኛውም አይነት የትራንስፖርት አገልግሎት ከደሴ - ሸዋሮቢት_ ደ/ብረሀን እንዲሁም ከደ/ብረሀን -ሸዋሮቢት - ደሴ እንዲቆም ውሳኔ መተላለፉን አሳውቋል።

የትራንስፖርት እንቅስቃሴው እንዲቆመ የተደረገው ኮማንድ ፖስቱ " ፅንፈኛ " ባላቸው ታጣቂዎች ላይ ኦፕሬሽን በመጀመሩና ቀጠናውን ነፃ ለማድረግ እርምጃ መውሰድ በመጀመሩ እንደሆነ ተገልጿል።

በመሆኑም በቀጠናው የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቆም የተወሰነው ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ መሆኑን ያሳወቀው ኮማንድ ፖስቱ ውሳኔው ለጊዜው ነው ብሏል።

ህብረተሰቡ ከዛሬ ጀምሮ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ #እንዲቆም የተወሰነ መሆኑ እንዲያውቅና አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ፤ የፀጥታ ሀይሉም ውሳኔው እንዲፈፀም ክትትል እንዲያደርግ ትዕዛዝ መሰጡቱ ታውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢፍጧር የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል። በነገው ዕለት በአዲስ አበባ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመስቀል አደባባይ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር  ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት፡- - ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን - ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ   ኦሎምፒያ…
#ATTENTION

ሁሉም ምዕመናን ወደ ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር በኢትዮጵያ-4 ሲመጡ ሊከተሏቸው የሚገቡ ደንቦች የሚከተሉት ናቸው።

1ኛ. ለጸጥታ አካላትና ለበጎ ፍቃድ አስተባባሪዎች #ለፍተሻ ትብብር ማድረግ ይገባል።

2ኛ. የሰላት መስገጃ እና ጥላ ይዘው መምጣት እንዳይዘነጉ።

3ኛ. ለማፍጠሪያ የሚሆንና ሙስሊም እህትና ወንድሞችን በማካፈል ኢፍጣርን ለሌሎች በማጋርት የሚገኘውን አጅር ተቋዳሽ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል። ምግቦቹ እንደ ፦
- ቴምር፣
- ውሃ
- የታሸጉ ምግቦች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

4ኛ. ማንኛውም ለደህንነት አጠራጣሪ ሁኔታዎች ከተመለከቱ ለበጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎችና ለጸጥታ አካላት በአፋጣኝ ማሳወቅ ይገባል።

5ኛ. ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ዝግጅት ዋናው ዓላማ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሌሎች ጋር ኢፍጣርን በማጋራት የሚገኘውን አጅርና ደስታ እንዲያጣጥም ከማስቻል ባሻገር ሙስሊሞች ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይገድባቸው ህብር ብሄራዊ  አንድነታቸውን በማሳየት ለሃገር ሰላምና ዕድገት በጋራ አላህን የሚማፀኑበት ዝግጅት ስለሆነ ከዝግጅቱ ዓላማ ውጪ ከሆኑ ድርጊቶች በመቆጠብ ኢስላማዊ ስነምግባርን ለሌሎች ዓርኣያ በመሆን ማሳየት ይገባል።

6ኛ. በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለተፈናቀሉ ወገኖችን ድጋፍ ስለሚሰበሰብ ከወዲሁ በረመዳን ለተቸገሩ ድጋፍ በማድረግ የሚገኘውን ታላቅ አጅር እንዲሸምቱ ጥሪ ተላልፏል።

7ኛ. የዝግጅቱ አላማ መዓድ መጋራት እንደመሆኑ ከአላሰፈላጊ የምግብ ብክነት በመቆጠብ ምዕመኑ ሃይማኖታዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

8ኛ. ንፅህና የሙስሊም መገለጫ እንደመሆኑ ሁሉም ምዕመን የተጠቀመባቸው እቃዎች በአግባቡ እንዲያስወግዱ።

(ከአዘጋጆቹ ሀላል ፕሮሞሽን እና ነጃሺ በጎ አድራጎት ድርጅት)

ከ5:00 ሰዓት ጀምሮ የሚዘጉ መንገዶች 👇
https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/86345

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Attention🚨

የትራፊክ አደጋ የበርካቶች ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል።

በዚህ ወር ብቻ ፦

- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 2 ሰዎች ሲሞቱ 5 ሰዎች ተጎድተዋል።

- በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ ከኔጌሌ ወደ ዶዶላ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና 'አላንቱ' ላይ ከ " ሲኖትራክ " የጭነት መኪና ጋር ተጋጭቶ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። ሌሎችም ተጎድተዋል።

- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በካፋ ዞን ጨና ወረዳ ፤ ከዋቻ ወደ ቦንጋ ሲጓዝ የነበረ ዶልፊን ተሸከርካሪ እና ከሚዛን ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ #ሲኖ_ትራክ ተሸከርካሪ በጨና ወረዳ ቦባ በላ ቀበሌ ተጋጭተው 5 ሰዎች ሲሞቱ 13 ሰዎች ተጎድተዋል።

-  በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ወርት በተባለች ቀበሌ እንጨት ጭኖ ሲጓዝ የነበረ #ሲኖ_ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ   የ6 ወጣቶች ህይወት ወዲያዉ ሲያልፍ በ10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል። አደጋዉን የከፋ ያደረገው ሲኖ ትራኩ  ወጣቶችን እንጨት ላይ አሳፍሮ እየተጓዘ ባለበት ወቅት አደጋው በመድረሱ ነው።

ከላይ በተጠቀሰው እና በይፋ በታወቀው ብቻ 28 ዜጎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል። በርካቶች የአካል ጉዳተኛ ሆነው።

እባካችሁ ጥንቃቄ አይለያችሁ !

@tikvahethiopia
#ATTENTION🚨

“ የካንሰር ሕመም እየጨመረ ነው ” - ዶክተር አስቻለው ወርቁ

በኢትዮጵያ የካንሰር ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን፣ በተለይም ማኀበረሰቡ ትንቦሆ፣  አልኮል ነክ ነገሮችን ከመጠቀም እንዲታቀብ ጥሪ ቀረበ።

ለካንሰር ሕሙማን የሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ ቢሆንም በተለይ በኢትዮጵያ በኩል የፋይናንስ እጥረት ችግር እንደፈተነው ማቲዎስ ወንዱ ካንሰር ሶሳይቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ተቋሙ የ20ኛ ዓመት ምስረታውን በማስመልከት መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ካንሰር #በኢትዮጵያ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ? በበሽታው የተጠቂ ሰዎች ቁጥር ቀነሰ ወይስ ጨመረ ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

የተቋሙ የቦርድ አባልና የውስጥ ደዌ ባለሙያው ዶክተር አስቻለው ወርቁ ምን አሉ ?

“ በጣም እየጨመረ ነው ያለው። ለመጨመሩ የተለያዩ ምክንያቶች ይኖራሉ። በአጠቃላይ ተላላፊ ያልሆኑ በሽዎች እየጨመሩ ነው። የካንሰር ህመምም እየጨመረ ነው።

ለምሳሌ፦ የሳንባ ካንሰርን ብናዬው ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ነው ያለው። የምንመረምረው ጥቂት ሰዎችን ስለሆነ በዚያችው ዳታ ተመርኩዘን ነው የምንገልጸው። ማኀበረሰቡን ያማከለ የዳሰሳ ጥናት ካልሰራን ቁጥሩን በትክክል መግለጽ ከባድ ነው።

10 ሰዎችን መርምሮ 5 ሕሙማን ቢገኝ 50 በመቶ ማለት አይቻልም። ምክንያቱም ያልተመረመሩ ብዙ ስለሚኖሩ። እንደ አጠቃላይ ካየነው ግን ፦
- የሳንባ፣
- የአንጀት፣
- የጉበት፣
- የማህፀን፣
- የደም ሴል ካንሰር ታማሚሞች ቁጥራቸው እጅግ ባጣም እየጨመረ ነው ያለው። ” ብለዋል።

ካንሰር ዋነኛ የሞት እና የስቃይ ምክንያት እየሆነ መምጣቱን ቁጥሮች እንደሚያመላክቱ ተገልጿል።

ለአብነት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከሞቱ ሰዎች ካንሰር የመገኘት እድሉ ከፍ ብሏል። ምክንያቱም የሳንባ ካንሰር ካሉት የካንሰር ዝርዝሮች ወደ 6ኛ ደረጃ ላይ ነው ያለው ተብሏል።

የማቲዎስ ወንዱ ካንሰር ሶሳይቲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ምን አሉ ?

“ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትንባሆ መሸጥም መግዛትም እንዳይችል የሚነገርበት ጊዜ መቼ ነው ?

ትንባሆ ነክ ነገሮች፣ አልኮል በሽታውን እያስፋፉት ነው።
 
ከ3,000 በላይ የካንሰር ሕሙማንና ቤተሰባቸውን እረድተናል። በአሁኑ ወቅት 175 ለካንሰር ሕሙማንና ለቤተሰባቦቸው፦

° ከአገራቸው የሚመጡበት ሙሉ የትራንስፖርት፣
° ከውጪ የሚገዙ መድኃኒቶች፣ 
° በሆስፒታል ውጪ በግል ተቋማት ለሚሰሩ የላብራቶሪ ምርመራ፣ 
° ሆስፒታል ለተኙት ሕሙማን ለአንዳንድ ነገር መሸፈኛ በወር 1,000 ብር፣
° እየታከሙ ለሚማሩ ተማሪዎች በወር 1,000 ብር፣
° 24 አልጋ ባለው የካንሰር ሕክምና ማዕከል በየዕለቱ ለቁርስ፣ ምሳ፣ በክሰስና እራት ወጪዎችን እየሸፈንን ነው። ”

NB. ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ የአቶ ወንዱ በቀለ የ4 ዓመት ጨቅላ ልጃቸው በካንሰር በሽታ ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ ቤተሰቦቹ የደረሰባቸውን መሪር ሀዘን “ ማቲዎስ ቢሞትም ብዙ ማቲዎሶችን ማዳን እንችላለን ” በሚል መልካም አስተሳሰብ በመቀየር በ15 መስራች አባሎች ሚያዚያ 9 ቀን 1996 ዓ/ም የተመሠረተ ለካንሰር ሕሙማን የሕክምና አገልግሎት የሚሰጥ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ATTENTION🚨

" አንዳንድ ወጣት ሴቶች ከቫይረሱ በላይ #እርግዝናን_ይፈራሉ "

ስለኤች አይቪ/ኤድስ ስርጭት የሚሰጠው የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ከጊዜ ወደጊዜ እየተቀዛቀዘ መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ገልጿል።

ችግሮች ከመባባሳቸው በፊት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ አሳስቧል።

ቫይረሱ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ በተሰራው እንቅስቃሴ ብዙ ለውጦች መመዝገባቸውን አስታውሷል።

ይሁን እንጂ የተመዘገቡት ለውጦች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን መዘናጋት እንደፈጠሩ ፤ የሚዲያዎች ተሳትፎም መቀዛቀዙን ጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት ኤች አይ ቪ ቫይረስን በተመለከተ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ትኩረት የሚሹና በይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ ብቻ ትኩረት ያደረጉ ናቸው ብሏል።

እነዚህም ፦
- ሴተኛ አዳሪዎች፣
- አደንዛዥ እፅ የሚጠቀሙ ሰዎች፣
- የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፣
- አፍላ ወጣቶች በተለይ (ከማኅበራዊ ሚዲያ ጋር በተያያዘ)፣
- የቀን ሠራተኞች፣
- ከማኅበራዊ ችግሮች ጋር ተያይዞ ተጋላጭ የሆኑት እንደሆኑ አመልክቷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የስርጭት መጠኑ ከ1 በመቶ በላይ ቢሆንም ከቦታ ቦታ በፆታ፣ በኅብረተሰብ ክፍል፣ በገጠርና በከተማ ከፍተኛ ልዩነት አለው ብሏል።

በከተሞች ያለው ስርጭት በገጠር ካለው በሰባት እጥፍ እንደሚበልጥም ጠቁሟል።

ይህንን ልዩነት መሠረት ያደረገ አጠቃላይ ማኅበረሰቡን ተደራሽ የሚያደርግ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እየተከናወነ አይደለም ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፦
° የመጠጥ ቤቶች ፣
° የጫት ቤቶች
° በሺሻ ቤቶች መስፋፋት ሌላ ተግዳሮቶች እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጿል።

" አንዳንድ ወጣት ሴቶች ከቫይረሱ በላይ እርግዝናን ይፈራሉ። የወጣቶች አዲስ የመያዝ ምጣኔ ጨመረ ባይባልም እየቀነሰ አይደለም፤ ይህ በራሱ ችግር ለመኖሩ አመላካች ነው "ም ብሏል።

በተለይ በወጣቶች በኩል ሁሉን አቀፍ ሥራ ባለመሠራቱ እንደ ሀገር ዋጋ ሊያስከፍሉ የሚችሉ አጋላጭ ባሕሪያት እየተስተዋሉ መሆኑን አመልክቷል።

የኤች አይ ቪ ቫይረስን በተመለከተ ጠንካራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እንደሀገር ማከናወን እንደሚጠበቅ አሳስቧል። #ኢፕድ

@tikvahethiopia
#ATTENTION🔔

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ወላይታ ዞን ባሉ ወረዳዎች ያሉ መምህራን ከደመወዝ ጋር በተያያዘ ስራ እንዳቆሙ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አማኑኤል ጳውሎስ ፦

" ... ጉዳዩ ስር የሰደደና የቆየ ነው። አሁን ላይ ' በተራበ አንጀታችን መስራት አልችልም ' በሚል መምህራኑ ስራ አቁመዋል።

በፐርሰንት እየተቆራረጠ የሚከፈላቸው ደመወዝ በዚህ ወር ለ16 ቀን ዘግይቷል።

ከደመወዝ በላይ የሌሎች ጥቅማጥቅሞች ፥ የወዝፍ ደሞዝ ፣ ከደረጃ እድገት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደሞዝ ጭማሪና የእርከን ጭማሪ መቅረት ፈተና ሆኖባቸዋል። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ መረጃዎችን ይልካል።

ከዚህ ቀደም ወላይታ ዞን ስለሚገኙ መምህራን ቅሬታ የቀረበ ፦ https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/86484?single

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Attention ⚠️

" ራኒቲዲን #ካንሰርን ሊያመጣ የሚችል ንጥረ ነገር በውስጡ በመገኘቱ ምክንያት #ታግዷል " - የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን

ለጨጓራ ተያያዥ ህመሞች በመድኃኒትነት ጥቅም ላይ ሲውል የነበረው ' ራኒቲዲን ' የተባለው መድሃኒት በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውል #ማገዱን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የባለስልጣኑ የመድኃኒት ደህንነት ክትትልና የሕክምና ሙከራ መሪ ስራ አስፈጻሚ አስናቀች ዓለሙ ፤ " በመጀመሪያ ደረጃ በሌሎች ሀገር የወጡ ሪፖርቶችን አይተን ነበር። ስለዚህ በሀገራችንስ ይሄ መድሃኒት እንዴት ነው ? የሚለውን በማገናዘብ የላብራቶሪ ምርመራ አድርገናል " ብለዋል።

በዚህም መድሃኒቱ ካንሰር ሊያመጣ የሚችል ' N-nitrosodimethylamine ወይም NDMA ' የተሰኘ ንጥረ ነገር እንደተገኘበት መሪ ስራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል።

" በመሆኑም ይህንን መድሃኒት ከምዝገባ ፋይላችን አውጥተናል። የተሰራጩ መድሃኒቶችም #እንዲሰበሰቡ እና ጥቅም ላይ እንዳይውሉ መልእክት አስተላልፈናል " ብለዋል።

" በዚህ በሰረትም ጥቅም እንዳይውል #ታግዷል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

" የጤና ባለሙያዎችም፣ የጤና ተቋማትም ሌሎች አማራጭ መድሃኒቶችን እንዲያዙ እና እንዲጠቀሙ ይህንን መድሃኒት #እንዳይጠቀሙ " ሲሉም አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ATTENTION🚨

“ የ2 አውቶብስ ተማሪዎች በታጣቂዎች ታግተዋል ” - ከእገታ ያመለጠ ተማሪ

“ ‘ ከአሁን ወዲህ ስልኬ አይሰራም ፤ ታግተናል ’ አለችኝና ከዛ ስልኳ አይሰራም ” - የአንዷ ታጋች ተማሪ እህት

“ አጋቾቹ ለአንድ ተማሪ 400 ሺህ ብር እየጠየቁ ነው ” - የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት

ሰኞ እለት ተሳፍረው ወደ ቤተሰብ እየተጓዙ የነበሩ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ዓመት ያሉ ተማሪዎች በታጣቂዎች መታገታቸውን የዓይን እማኝ፣ የታጋች ቤተሰብና ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

አንድ ከእገታው አመለጥኩ ያለ ተማሪ ፥ ሶስት (3) አውቶብሶች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እየተጓዙባቸው የነበሩ ረቡዕ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ/ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ገደማ ገብረ ጉራቻ የሚባል ቦታ ሲደርሱ መታገታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ከ3 አውቶብሶች 2ቱን ታጣቂዎች እንዳስቆሟቸው፣ ተሳፋሪዎቹን ካስወረዷቸው በኋላ አግተው ወደ ጫካ እንዳስገቧቸው፣ እርሱ ገለባ ውስጥ ተደብቆ እንዳመለጠ ገልጾ፣ “ የሁለቱ አውቶብስ ተማሪዎች በታጣቂዎች ታግተዋል ” ብሏል።

ከታጋቾቹ መካከል የሚያውቃቸው የIT ፣ የአኒሚል ሳይንስ ዲፓርትመንት ተማሪዎች እንዳሉ ገልጾ፣ ያገቷቸው “የሸኔ ታጣቂዎች” መሆናቸውን አስረድቷል።

አንዷ የታጋች እህት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠችው ቃል፣ “ ረቡዕ 3 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ደወለችልኝ (እየሮጡ ነበር፣ የተኩስ ድምጽም ነበር) ‘በቃ ከአሁን ወዲህ ስልኬ አይሰራም። ላታገኝኝ ትችያለሽ በታጣቂዎች ታግተናል’ አለችኝ። መለሽ ስደውል ስልኳ አይሰራም ” ብላለች።

ቤተሰቡ ሁሉ በጣም ከፍተኛ ጭንቀት ላይ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ታጋቾቹን በህይወት እንዲያተርፏቸው ተማጽናለች።

በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፤ የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት በበኩሉ፣ እገታው እውነት መሆኑን እንዳረጋገጠ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ኀብረቱ በሰጠው ቃል “ አጋቾቹ ለአንድ ተማሪ 400 ሺህ ብር እየጠየቁ ነው። ‘ ገንዘቡን ካላመጣችሁ እንገድላችኋለን ’ እያሏቸው ይገኛል ” ሲል የሰማውን አስረድቷል።

የሞቱ ፣ የተጎዱ ስለመኖራቸው የደረሰው መረጃ እንደሌለ የገለጸው ማህበሩ ፣ የሚመለከታቸውን  አካላት ሁሉ ለማነጋገር ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

በጉዳዩ ላይ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሰጠንን ምላሽ በቀጣይ ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam " የኦንላይን ፈተናው አልቀረም። የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል። ሚኒስቴሩ ይህ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ…
#ATTENTION🚨

" የበይነ መረብ (ኦንላይን) ተፈታኞች በተመደባችሁበት የፈተና ጣቢያ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይ) እንዲሁም በወረቀት እንደሚሰጥ በዛሬው ዕለት በድጋሚ አሳወቀ።

በሁለቱም መንገድ ለሚሰጠው ፈተና ዝግጅት ተደርጓል ብሏል።

ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ያሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች " የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተና ቀርቷል " እያሉ ለተማሪዎች መናገራቸውን እና የጽሁፍ መልዕክት በቴሌግራም ላይ መለጠፋቸውን የተማሪ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

እንዲህ ያለው ውሳኔ የሚተላለፈው ከማዕከል ከትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ ሳለ ፥ ትምህርት ቤቶቹ ውሳኔውን ማን እንዳሳለፈ በይፋ ያሉት ነገር ሳይኖር በደፈናው " ቀርቷል " የሚል ነገር ብቻ ነው የነገሯቸው።

በኋላም እራሳቸው ት/ቤቶቹ ቀድሞ ያሰራጩትን ያልተረጋገጠ መረጃ በማጥፋት የኦላንይን ፈተናው እንዳልቀረ መልሰው ገልጸዋል።

ዛሬ እሁድ ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው በፍጹም እንዳልቀረ በድጋሜ አረጋግጧል።

ብሔራዊ ፈተናውን በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቅቆ የተማሪዎችን የመፈተኛ ቀን እየተጠባበቀ እንደሚገኝም አሳውቋል።

" ፈተናውን አስመልክቶ የተሳሳቱ መልዕክቶች በየጊዜው ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር ባልሆኑ ገጾች እየተለቀቁ ይገኛሉ " ሲልም ገልጿል።

ለተማሪዎች፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ባስተላለፈው መልዕክት ፈተናው ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት እንደተማሪዎች የቀደመ ምርጫ መሰረት ይሰጣል ብሏል።

አስቀድመው በወረቀት የመረጡ ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ፣ በበይነ መረብ (ኦንላይን) የመረጡም በተመደቡበት የፈተና ጣቢያ ተገኝተው ፈተናውን እንዲወስዱ በጥብቅ አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ተማሪዎች ከላይ በምስሉ እንደተያያዘው አይነት ከሃሰተኛ ወሬ ራሳቸውን በመከላከል ለፈተናው የሚያደርጉትን ዝግጅት እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ለማንኛውም መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ብቻ እንዲከታተሉም አደራ ብሏል።

#TikvahEthiopia
#NationalExam
#MoE

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#ATTENTION🔈

" ከሕጋዊው አካዉንት ውጭ በመጠቀም ድጋፍ የምታሰባስቡ አካላት ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ !! " - የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ

በጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ የመሬት ናዳ ከተከሰተ ዛሬ 6ኛ ቀኑን ይዟል።

በዚህ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

የጠፉ ሰዎችን ፍለጋና አስከሬን በቁፋሮ የማውጣቱ ስራ አሁንም የቀጠለ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።

እስካሁንም ድረስ ያልተገኙ በርካታ የቤተሰብ አካላት በመኖራቸዉ የሟቾችን ቁጥር ቀድሞ ከተገለጸው ሊጨምር ይችላል።

ከጉዳቱ የተረፉ ሰዎችን ወደ አንድ አካባቢ አድርጎ ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው።

ከአራቱም የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚደረገው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ተብሏል።

ግን ከተፈቀደው የንግድ ባንክ አካውንት እና የአጭር መልዕክት ድጋፍ ማድረጊያ ቁጥር ውጭ " ድጋፍ እናሰባስባለን " በሚል አንዳንድ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ ኢ/ር ዳግማዊ አየለ ፥ " ከተፈቀደዉ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ቁጥሮች ወጭ ጥቅም ላይ የዋሉ የንግድ ባንክ አካውንቶች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች እየተዘዋወሩ በመሆኑ በዚህ ድርጊት ላይ የምትሳተፉ አካላት ከድርጊታችሁ  እንድትቆጠቡ "  ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የዞኑ አስተዳዳሪ ፥ " አሁን ላይ ህጋዊ ሆኖ ገንዘብ የሚሰበሰብበት የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000511561276 እንዲሁም በአጭር መልእክት ድጋፍ ለማድረግ ደግሞ 8991 ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

ማህበረሰቡ ከዚህ ዉጭ በሚዘዋወሩ አካውንቶችን እንዳይጠቀም ገልጸዋል።

በመጨረሻም ከመላው ኢትዮጵያ እየመጣ ያለው ድጋፍ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ከጉዳት የተረፉ ወገኖችን ስነልቦና የማከሙ ስራ የቀጣይ ዋና ተግባር እንደሚሆንና ይህም የሁሉም ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #Silte ስልጤ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ በመከሰቱ በርካታ ወገኖቻችን ለመፈናቀል መገደዳቸውን ነዋሪዎችና ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተለይ በዞኑ የስልጢ ወረዳ ጎፍለላ ቀበሌ በጎርፍ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ወገኖቻችን ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ ቤት ንብረታቸውን ትተው ወደ ተለያዩ ስፍራዎች ተፈናቅለዋል። አደጋው እንስሳትን ጨምሮ በንብረት ላይ ውድመት አስከትሏል…
#ATTENTION🚨

ከ6 ሽህ በላይ ወገኖቻችን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

በስልጤ ዞን ባሉ 2 ወረዳዎችና 8 ቀበሌዎች ከአንድ ሺህ በላይ አባዉራ ቤትና ማሳዉ በውሀ መዋጡን ተከትሎ ከአካባቢዉ መነሳታቸው ተሰምቷል።

እስካሁን ባለዉ መረጃ ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች ድጋፍ እንደሚሹ የዞኑ የአደጋ ስጋት ኃላፊ ወሲላ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ጎርፉ የፈጠረዉን ሀይቅ በዚህ ወቅት ማፋሰስ አሰቸጋሪ መሆኑን ያነለከቱት ኃላፊዋ " የሁለቱን ወረዳ ነዋሪዎች በክልሉና በዞኑ ድጋፍና ትብብር አውጥተን በትምህርት ቤቶችና በአርሶ አደሩ የስልጠና መዕከላት አስፍረን ስላልበቃን ትርፍ ቤት ያለዉ ሁሉ ትርፍ ቤቱን በመስጠት በጊዜያዊነት ለማስጠለል ተሞክሯል " ብለዋል።

" የመሬቱ አቀማመጥና የጎርፉ ብዛት የፈጠረዉ የዉሀ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ዝናቡ እስኪቆም ዘላቂ መፍትሄ መስጠት አንችልም ፤ ይሁንና አንዳንድ ቦታ ላይ ቋሚ ሰብሎች እንዳይጎዱና ቤቶች እንዳይበሰብሱ አንዳንድ ስራዎች እየሰራን ነው " ሲሉ አክለዋል።

አሁን ላይ ለተጎጂዎች እየቀረበ ያለው የምግብ እና አልባሳት ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ የዞኑ አደጋ ስጋት ምክር ቤት ተቋቁሞ ድጋፍ የሚሰበሰብበት መንገድ መመቻቹትን አመልክተዋል።

የስልጤ ዞን የጎርድ ድጋፍ ማሰባሰቢያ አካዉንት 1000647585535 (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) መሆኑ ተገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia