#ATTENTION🔈

" ከሕጋዊው አካዉንት ውጭ በመጠቀም ድጋፍ የምታሰባስቡ አካላት ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ !! " - የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ

በጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ የመሬት ናዳ ከተከሰተ ዛሬ 6ኛ ቀኑን ይዟል።

በዚህ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

የጠፉ ሰዎችን ፍለጋና አስከሬን በቁፋሮ የማውጣቱ ስራ አሁንም የቀጠለ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።

እስካሁንም ድረስ ያልተገኙ በርካታ የቤተሰብ አካላት በመኖራቸዉ የሟቾችን ቁጥር ቀድሞ ከተገለጸው ሊጨምር ይችላል።

ከጉዳቱ የተረፉ ሰዎችን ወደ አንድ አካባቢ አድርጎ ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው።

ከአራቱም የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚደረገው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ተብሏል።

ግን ከተፈቀደው የንግድ ባንክ አካውንት እና የአጭር መልዕክት ድጋፍ ማድረጊያ ቁጥር ውጭ " ድጋፍ እናሰባስባለን " በሚል አንዳንድ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ ኢ/ር ዳግማዊ አየለ ፥ " ከተፈቀደዉ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ቁጥሮች ወጭ ጥቅም ላይ የዋሉ የንግድ ባንክ አካውንቶች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች እየተዘዋወሩ በመሆኑ በዚህ ድርጊት ላይ የምትሳተፉ አካላት ከድርጊታችሁ  እንድትቆጠቡ "  ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የዞኑ አስተዳዳሪ ፥ " አሁን ላይ ህጋዊ ሆኖ ገንዘብ የሚሰበሰብበት የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000511561276 እንዲሁም በአጭር መልእክት ድጋፍ ለማድረግ ደግሞ 8991 ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

ማህበረሰቡ ከዚህ ዉጭ በሚዘዋወሩ አካውንቶችን እንዳይጠቀም ገልጸዋል።

በመጨረሻም ከመላው ኢትዮጵያ እየመጣ ያለው ድጋፍ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ከጉዳት የተረፉ ወገኖችን ስነልቦና የማከሙ ስራ የቀጣይ ዋና ተግባር እንደሚሆንና ይህም የሁሉም ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM