TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #Silte ስልጤ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ በመከሰቱ በርካታ ወገኖቻችን ለመፈናቀል መገደዳቸውን ነዋሪዎችና ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተለይ በዞኑ የስልጢ ወረዳ ጎፍለላ ቀበሌ በጎርፍ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ወገኖቻችን ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ ቤት ንብረታቸውን ትተው ወደ ተለያዩ ስፍራዎች ተፈናቅለዋል። አደጋው እንስሳትን ጨምሮ በንብረት ላይ ውድመት አስከትሏል…
#ATTENTION🚨

ከ6 ሽህ በላይ ወገኖቻችን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

በስልጤ ዞን ባሉ 2 ወረዳዎችና 8 ቀበሌዎች ከአንድ ሺህ በላይ አባዉራ ቤትና ማሳዉ በውሀ መዋጡን ተከትሎ ከአካባቢዉ መነሳታቸው ተሰምቷል።

እስካሁን ባለዉ መረጃ ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች ድጋፍ እንደሚሹ የዞኑ የአደጋ ስጋት ኃላፊ ወሲላ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ጎርፉ የፈጠረዉን ሀይቅ በዚህ ወቅት ማፋሰስ አሰቸጋሪ መሆኑን ያነለከቱት ኃላፊዋ " የሁለቱን ወረዳ ነዋሪዎች በክልሉና በዞኑ ድጋፍና ትብብር አውጥተን በትምህርት ቤቶችና በአርሶ አደሩ የስልጠና መዕከላት አስፍረን ስላልበቃን ትርፍ ቤት ያለዉ ሁሉ ትርፍ ቤቱን በመስጠት በጊዜያዊነት ለማስጠለል ተሞክሯል " ብለዋል።

" የመሬቱ አቀማመጥና የጎርፉ ብዛት የፈጠረዉ የዉሀ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ዝናቡ እስኪቆም ዘላቂ መፍትሄ መስጠት አንችልም ፤ ይሁንና አንዳንድ ቦታ ላይ ቋሚ ሰብሎች እንዳይጎዱና ቤቶች እንዳይበሰብሱ አንዳንድ ስራዎች እየሰራን ነው " ሲሉ አክለዋል።

አሁን ላይ ለተጎጂዎች እየቀረበ ያለው የምግብ እና አልባሳት ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ የዞኑ አደጋ ስጋት ምክር ቤት ተቋቁሞ ድጋፍ የሚሰበሰብበት መንገድ መመቻቹትን አመልክተዋል።

የስልጤ ዞን የጎርድ ድጋፍ ማሰባሰቢያ አካዉንት 1000647585535 (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) መሆኑ ተገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia