TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AGOA : ኢትዮጵያ በ "AGOA" በኩል ያላት ተጠቃሚነት ላይ አሜሪካ በቅርቡ ውሳኔ ላይ እንደምትደርስ ካትሪን ታይ (የንግድ ተወካይ) ተናግረዋል።

ኃላፊዋ በይፋዊ መንገድ እና በግብረሰናይ ድርጅቶች በኩል የሚደርሱን መረጃዎች አበረታች አይደሉም፤ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ ነው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያ ቢልለኔ ስዩም፥ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የተፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

ቢልለኔ፥ " ሰብዓዊ ቀውስ AGOA እድል ከፈጠረላቸው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሴቶች የስራ እድል በመንጠቅ አይገታም እንደውም ያባብሰዋል" ብለዋል።

ባለፈው ነሃሴ ወር ላይ አሜሪካ፥ በኢትዮጵያ እየተፈፀሙ ነው ያለችው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፍትሄ የማያገኙ ከሆነ በAGOA ያለቀረጥ ምርቶቿን ለአሜሪካ ገበያ የማቅረብ እድሏን እንደምታጣ ገልፃ ነበር።

ሮይተርስ ኢትዮጵያ በ2020 (እኤአ) 237 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ሸቀጦችን ያለቀረጥ በAGOA በኩል ለአሜሪካ ገበያ ማቅረቧን የሀገሪቱ መንግስት መረጃ ያሳያል ብሏል።

የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከፍተኛ አማካሪ እና የኢትዮጵያ የንግድ ተደራዳሪ የሆኑት ማሞ ምህረቱ ኢትዮጵያን በAGOA በኩል ያላትን እድል ማሳጣት ማለት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰራተኞች እንደሚጎዳ ለፎርየን ፖሊሲ በፃፉት የግል አስተያየት ላይ ገልፀዋል።

AGOA ምንድነው?

African Growth and Opportunity Act (AGOA) የግብይት ስርዓት ነው፤ ይህ የግብይት ስርዓት የተወሰኑ የብቃት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ከሳሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ሸቀጦችን ያለቀረጥ ለአሜሪካ ገበያ እንዲሸጡ የሚፈቅድ ነው። #DW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AGOA : ኢትዮጵያ በ "AGOA" በኩል ያላት ተጠቃሚነት ላይ አሜሪካ በቅርቡ ውሳኔ ላይ እንደምትደርስ ካትሪን ታይ (የንግድ ተወካይ) ተናግረዋል። ኃላፊዋ በይፋዊ መንገድ እና በግብረሰናይ ድርጅቶች በኩል የሚደርሱን መረጃዎች አበረታች አይደሉም፤ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ ነው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያ ቢልለኔ ስዩም፥ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ…
#AGOA : የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አማካሪና ዋና የንግድ ተደራዳሪ ማሞ ምህረቱ ኢትዮጵያ ከAGOA እንድትወጣ ከሚሰሩት መካከል የሕወሃት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም አንዳንድ አሜሪካ መንግስት ውስጥ ያሉ ሰዎችም እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

አቶ ማሞ ይህን ያሉት ከአል ዓይን አማርኛው ክፍል ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ነው።

ኢትዮጵያ ከAGOA እንድትወጣ የሚሰሩት እንነማን እንደሆኑ ? ከዜና ወኪሉ የተጠየቁት የጠ/ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ ፦ አንደኛ የሕወሃት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች እንደሆኑ አመልክተዋል።

እነዚህ ሰዎች የሚከራከሩ ሰዎችን በመቅጠር በአሜሪካ ውስጥ ያሉ የኮንግረንስ ሰዎችን እንዲያሳምኑ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ በይፋ የሚታወቅ ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ ሰዎች (አሜሪካ መንግስት ውስጥ ያሉ ሰዎችም) እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት ትግራይን አስመከልክቶ ባለው ግጭት ውስጥ የተለያዩ የፖለቲካ ሃሳቦችን፤ የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች እንዲሟሉ በማድረግ AGOAን እንደ አንድ የውጭ ፖሊሲ መሳሪያ አድርጎ የማስቀረት ጉዳይ አለ ሲሉ አቶ ማሞ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ ፥ " በእኛ እምነት የፖለቲካ ሂደቱን በተመለከተ AGOA ትክክለኛው መሳሪያ ነው ብለን አናምንም፤ ምክንያቱም AGOA ከተነሳ የሚጎዱት በዋነኛነት በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚሰሩ ሰራተኞች ናቸው በተለይ ሴቶች ናቸው የሚጎዱት " ብለዋል።

አክለውም ፥ "አንድ ሀገር የፖለቲካ መሳሪያውን ለማሳካት ሲባል ከጦርነቱ /ከግጭቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ሰዎች መጉዳት ትክክለኛ ነው ብለን አናምንም፡፡ ይህ እንዳይሆንም የበኩላችንን ጥረት እያደረግን ነው" ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AGOA : የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አማካሪና ዋና የንግድ ተደራዳሪ ማሞ ምህረቱ ኢትዮጵያ ከAGOA እንድትወጣ ከሚሰሩት መካከል የሕወሃት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም አንዳንድ አሜሪካ መንግስት ውስጥ ያሉ ሰዎችም እንደሚገኙበት ተናግረዋል። አቶ ማሞ ይህን ያሉት ከአል ዓይን አማርኛው ክፍል ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ነው። ኢትዮጵያ ከAGOA እንድትወጣ የሚሰሩት እንነማን እንደሆኑ…
#AGOA

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ተጠቃሚ ከነበረችበት የአሜሪካ የንግድ ችሮታ (AGOA) ማስወጣታቸውን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ማሳወቃቸውን ኋይት ሃውስን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ከንግድ ችሮታው እንዲትወጣ ፕሬዝዳንቱ ደብዳቤ የጻፉት ከሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ጋር ተያይዞ መሆኑንም ኋይት ሃውስ አስታውቋል።

አሜሪካ ፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ጥልቅ ውይይቶች ተደርገው እንደነበር ገልጻለች።

ጆ ባይደን ከኢትዮጵያ በተጨማሪም ጊኒ እና ማሊም ከአሜሪካ የንግድ ችሮታ (አጉአ) እንዲወጡ ደብዳቤ መጻፋቸውንም ኋይት ሃውስ አስታውቋል።

ሀገራቱ ይህ የተወሰነባቸው #የአሜሪካን_ፍላጎቶች ማሟላት ባለመቻላቸው መሆኑንም አሜሪካ ገልጻለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AGOA ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ተጠቃሚ ከነበረችበት የአሜሪካ የንግድ ችሮታ (AGOA) ማስወጣታቸውን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ማሳወቃቸውን ኋይት ሃውስን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ዘግቧል። ኢትዮጵያ ከንግድ ችሮታው እንዲትወጣ ፕሬዝዳንቱ ደብዳቤ የጻፉት ከሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ጋር ተያይዞ መሆኑንም ኋይት ሃውስ አስታውቋል። አሜሪካ ፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ጥልቅ…
#AGOA

" አሜሪካ አጎዋን በተመለከተ ያሳለፈችውን ውሳኔ ልታጤነው ይገባል " - ኢትዮጵያ

የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ከቀረጥ ነጻ ዕድል (አጎዋ) ተጠቃሚነቷ ለማገድ ያስተላለፈችውን ውሳኔ እንድታጤነው ኢትዮጵያ ጠይቃለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካን የአጎዋ ውሳኔ አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

ኢትዮጵያ ፥ አሜሪካ ያሳለፈችው ውሳኔ አግባብነት የሌለው እና የአሜሪካ መንግስት አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ መሆኑን ገልፃለች።

በውሳኔው ኢትዮጵያን ከአጎዋ ተጠቃሚነት ውጭ ማድረግ፤ ከግጭቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙት የሌላቸውን ከ200 ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የበርካታ ሴቶች ኑሮ ላይ ተጽእኖ ይኖረዋልም ብላለች።

እንዲሁም በግበዓት አቅርቦት ሰንሰለት የሚሳተፉትን የ1 ሚሊዮን ሰዎች ህይወት በእጅጉ እንደሚጎዳውም የገለፀው ኢትዮጵያ አሜሪካ ውሳኔውን እንድታጤነው ጥይቃለች።

#ENA

@tikvahethiopia
#AGOA

ኢትዮጵያ በAGOA ላይ እንድትቆይ ተሰሚነት ያላቸው የኮንግረስ መሪዎች ለአሜሪካ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ደብዳቤ አስገቡ።

የኢትዮጵያ-አሜሪካውያን የዜጎች ም/ቤት ኢትዮጵያ በAGOA እንድትቆይ ግፊት እያደረገ ይገኛል።

ይህን ተከትሎ ለዋይትሃውስ ድምፃቸውን እንዲያሰሙ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው ኮንግረስ መሪዎች የም/ቤቱን ደብዳቤ ተከትሎ ለፕሬዜዳንት ባይደን ኢትዮጵያ በAGOA ላይ እንድትቆይ ደብዳቤ አስገብተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AGOA

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያ ፣ ማሊ እና ጊንን ከAGOA እንዲሰረዙ ፈርመዋል።

ከእኤአ ከጥር 1 ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል።

ኢትዮጵያ የተሰረዘችው ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ተፈፅሟል ለተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው ፤ በተጨማሪ ከህወሓት ጋር ለድርድር እንድትቀመጥ ለማስገደድ በማለም ጭምር ነው።

አሜሪካ ፥ ኢትዮጵያን ጨምሮ ማሊን እና ጊኒን ከAGOA የሰረዘችው ፍላጎቶቼን ማሟላት አልቻላችሁም በሚል ነው።

ከመሰረዟ በፊትም የሁለት ወራት የማሰቢያ ጊዜ ገደብ ሰጥታ ነበረ።

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በAGOA ላይ እንድትቆይ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው ኮንግረስ መሪዎች ለባይደን ደብዳቤ ቢፅፉም እሳቸው ግን ኢትዮጵያን ከAGOA ሰርዘዋታል።

ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ያህል ከቆየችበት የAGOA ተጠቃሚነት እንዳትሰረዝ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ካውንስል ከፍተኛ ግፊት ሲያደርግ ነበር።

የፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ውሳኔ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰራተኞችን እንዲጎዱ የሚያደርግ ነው።

ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያን AGOA ተጠቃሚነት ውጭ ማድረግ፤ ከግጭቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙት የሌላቸውን ከ200 ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የበርካታ ሴቶች ኑሮ ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረው ማሳወቋ ይታወሳል።

በግበዓት አቅርቦት ሰንሰለት የሚሳተፉትን የ1 ሚሊዮን ሰዎች ህይወት በእጅጉ እንደሚጎዳው መግለጿ አይዘነጋም።

AGOA ምንድነው?

African Growth and Opportunity Act (AGOA) የግብይት ስርዓት ነው፤ ይህ የግብይት ስርዓት የተወሰኑ የብቃት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ከሳሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ሸቀጦችን ያለቀረጥ ለአሜሪካ ገበያ እንዲሸጡ የሚፈቅድ ነው።

@tikvahethiopia
#USA #ETHIOPIA

የአሜሪካው ከፍተኛ ባለሥልጣን (ስማቸው ያልተገለፀ) ለጋዜጠኞች ምን አሉ ?

• የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ የንግድ ልዑክ የተነሱትን ቅሬታዎች በተመለከተ ተጨማሪ " አዎንታዊ እና ገንቢ " ዕርምጃዎች የሚወስድ ከሆነ ኢትዮጵያ ከተጠቃሚነት የተሰረዘችበትን የ #AGOA ዕድል በተመለከተ የንግግር ሒደት ውስጥ ለመግባት ፈቃደኛ መሆኑን ገልፀዋል።

• ታኅሳስ 28 ቀን 2014 ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ንግግር ማድረጋቸው የተገለጸው የቀድሞ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ያደረጉት " በኢትዮጵያ መንግሥት ጥያቄ " መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

• አዲሱ ተሿሚ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ መቼ ወደ ቀጣናው ለመጓዝ እንዳሰቡ አልታወቀም ፤ ነገር ግን ረዥም [ጊዜ] እንደማይሆን ተገልጿል።

• ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በስልክ ንግግር ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለቱ መሪዎች ንግግር ያደረጉት በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጥያቄ መሠረት መሆኑን ተናግረዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/USA-ETHIOPIA-01-12

Credit : Reporter Newspaper
#AGOA

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ከዚህ ቀደም ከAGOA ተጠቃሚነት ጋር በተያያዘ በተላለፈው ውሳኔ ላይ ማስተካከያ እንዲያደርግና ተመልሳ እንድትገባ እንዲያደርግ የአሜሪካ ኢትዮጵያውያን የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ በደብዳቤ ጠይቋል።

ሙሉ መግለጫው ከላይ የተያያዘ ሲሆን በመግለጫው የተነሱት ሀሳቦች የሚከተሉት ናቸው ፦

- ኢትዮጵያን ከAGOA ዝርዝር ውስጥ ማስወጣት እስካሁን ከ200 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የስራ ዕድል እንዳሳጣ፣ በረዥም ጊዜ ተፅዕኖዎች ተጨማሪ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ለኑሯቸው መሰረት የሆነውን የስራ ዕድል ሊያጡ እንደሚችሉ ይጠበቃል ብሏል።

- ማዕቀቡ በግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን ፤ ብዙሃኑን የኢትዮጵያን ህዝብ የሚጎዳ ነው። አብዛኞቹ ስራ ያጡት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው በጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉ ሴት ሰራተኞች ናቸው። ይህን ስራ ማጣት ለመላው ቤተሰብ እና ማህበረሰብ ድህነት እና እጦት አስከትሏል።

- የኢትዮጵያ ሕዝብ የተጠየቀውን አድርጓል። መንግሥት ታሪካዊ የሰላም ስምምነት ፈፅሟል ፤ ዕርዳታ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፣ አስፈላጊ አገልግሎቶች እየተመለሱ ነው፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ጥሰትን የሚያጣራ ኮሚሽን ባለፈው ዓመት አዲስ አበባን ጎብኝቷል።

- ኢትዮጵያን ከAGOA ለተጨማሪ አንድ አመት አስወጥቶ ማቆየት ሙሉ በሙሉ ፋይዳ የለውም። የአሜሪካ መንግስት በምትኩ ሀገሪቱ ሰላም ለማስፈን፣ ለመገንባትና ዲሞክራሲያዊትነቷን ለማስጠበቅ እየሰራች ባለችበት ወቅት ድጋፍ ማድረግ አለበት።

ኮሚቴው በመግለጫው ላይ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ውሳኔውን እንደገና እንዲያጤኑት እና በAGOA ውስጥ ኢትዮጵያ እንድትመለስ ጠይቋል።

ኢትዮጵያ ከAGOA ዝርዝር ከወጣች 1 ዓመት ተቆጥሯል።

@tikvahethiopia
የ ' ቅጥር ደመወዝ ' አልበቃ ቢላት ፤ ፊቷን ወደ " ሊስትሮነት " ያዞረችው የምህድስና ምሩቋ ምንታምር በለጠ ፦

" ስሜ ምንታምር በለጠ እባላለሁ።

በሊስቶር ስራ ነው የምተዳደረው አዲስ አበባ፤ ቦሌ አካባቢ ።

የተወለድኩት በአማራ ክልል ፣ ዳንግላ ከተማ ነው። ተወልጄ የተማርኩትም እዛው አካባቢ ነው።

እናት አባቶቼ አቅመ ደካማ ነበሩ። አሁን ላይ በህይወት የሉም ሁለቱም። እህቶች እና ወንድሞች አሉኝ።

ዩኒቨርሲቲ የገባሁት በ2007 ዓ/ም ነው በ2011 ዓ/ም በቴክስታይል ኢንጂነሪንግ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመርቄያለሁ።

ከተመረቅኩ በኃላ ስራ ፍለጋ ነበር የወጣሁት ፤ ስራ ቶሎ ማግኘት ከባድ ስለነበር ወደ ሐዋሳ ነው የሄድኩት።

ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ገባሁ፤ በ2500 ብር ደመወዝ ስራ ጀመርኩ የስራ ድርሻዬ የጥራት ደረጃ ማስጠበቅ ቁጥጥር ነበር እሰራበት የነበረው ጨርቃ ጨርቅ ነው፣ ጋርመት ቲሸርቶች ሱሪ ይሰራል እሱ ላይ ጥራት መቆጣጠር ነበር የኔ ስራ።

እዚያ ሁለት ዓመት ሰራሁ ፤ ከዛ በጦርነቱም በ #AGOA / አጎዋ ምክንያት እየቀነሱ ነበር ድርጅቶቹ ሰራተኞችን ፤ ከእሱ ወጥቼ ወደ አዲስ አበባ መጣሁ።

አዲስ አበባ መጥቼ እንደጠበኩት ስራ አላገኘኹም። እየፈለኩኝ ነበር አንዳንድ ቦታዎችም ገብቻለሁ ፤ ደሞዝ የማይሰጥ ድርጅትም አጋጥሞኝ ያውቃል፤ ብዙ ተግዳሮቶችን አሳልፌያለሁ።

ሰው ቤት በተመላላሽነት ምግብ መስራትም ጀምሬ ነበር መጨረሻ ላይ ሊስትሮ / ጫማ ማስዋብ ጀመርኩ።

ዲግሪ ይዣለሁ ፤ ያሳፍራል ዲግሪ ጥቅም የለውም፤ በዲግሪ ስራ ማግኘት አልቻልኩም። ባገኝም ህይወቴን Survive የማያደርግ  ፣ የቤት ኪራይ የማይከፍል ፣ ቤተሰብ የማያስተዳድር ፣ ህይወቴን የማይቀይር ደመወዝ ነው ያለው።

ቤተሰብ መርዳት ቀርቶ እራስን መቀየሪያ የለም ፤ እኔ ዩኒቨርሲቲ ስማር የገዛሁትን ልብስ ነው እስካሁን የምለብሰው ፤ ምናልባት ይሄን ሊስትሮ ከሰራሁ በኃላ ልገዛ እችላለሁ።

ከጥዋቱ 11:30 ከቤቴ እወጣለሁ ፤ ታክሲ ይዤ እዚህ ስራ ቦታዬ ላይ 12:30 ደርሳለሁ ፤ ከጥዋቱ 12:30 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12:40 ድረስ ስራ ቦታዬ ላይ እገኛለሁ።

ደስ ብሎኝ ነው የምሰራው፤ የራሴ መመሪያ አለኝ ፤ በጥዋት ተነስቼ መጥቼ እሰራለሁ፤ ለኔ መስሪያ ቤቴ ድርጅቴ ነው።

ወጣቱ ተስፋ መቁረጥ የለበትም ፤ ያኔ ተስፋ ቆርጬ እራሴን አልጎዳሁም አማራጭ ሳጣ ወደ ሊስትሮ ዝቅ ብዬ መስራት እንዳለብኝ አእምሮዬ ነገረኝ ፤ ይህንን በመስራቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።

ይሄን ወጥሬ ስለምሰራ እራሴን ለመቀየረ፣ ወደዓላማዬ ፣ ወደ መንገዴ ያስገባኛል።

ከዚህ በኃላ የተሻለ ነገር መስራት አስባለሁ። ከዚህ ቀጥሎ ከሞያዬ ጋር ስለሚያያዝ ወደ ፋሽን ፣ ጋርመንት ፣ ስፌት ሞያ ሰልጥኜ ፣ ትንሽዬ ማሽንም ይሁን ገዝቼ ወደዛ የማዘንበል እቅድ አለንኝ። "

Credit : BBC AMHARIC

@tikvahethiopia