#AGOA : ኢትዮጵያ በ "AGOA" በኩል ያላት ተጠቃሚነት ላይ አሜሪካ በቅርቡ ውሳኔ ላይ እንደምትደርስ ካትሪን ታይ (የንግድ ተወካይ) ተናግረዋል።

ኃላፊዋ በይፋዊ መንገድ እና በግብረሰናይ ድርጅቶች በኩል የሚደርሱን መረጃዎች አበረታች አይደሉም፤ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ ነው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያ ቢልለኔ ስዩም፥ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የተፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

ቢልለኔ፥ " ሰብዓዊ ቀውስ AGOA እድል ከፈጠረላቸው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሴቶች የስራ እድል በመንጠቅ አይገታም እንደውም ያባብሰዋል" ብለዋል።

ባለፈው ነሃሴ ወር ላይ አሜሪካ፥ በኢትዮጵያ እየተፈፀሙ ነው ያለችው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፍትሄ የማያገኙ ከሆነ በAGOA ያለቀረጥ ምርቶቿን ለአሜሪካ ገበያ የማቅረብ እድሏን እንደምታጣ ገልፃ ነበር።

ሮይተርስ ኢትዮጵያ በ2020 (እኤአ) 237 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ሸቀጦችን ያለቀረጥ በAGOA በኩል ለአሜሪካ ገበያ ማቅረቧን የሀገሪቱ መንግስት መረጃ ያሳያል ብሏል።

የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከፍተኛ አማካሪ እና የኢትዮጵያ የንግድ ተደራዳሪ የሆኑት ማሞ ምህረቱ ኢትዮጵያን በAGOA በኩል ያላትን እድል ማሳጣት ማለት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰራተኞች እንደሚጎዳ ለፎርየን ፖሊሲ በፃፉት የግል አስተያየት ላይ ገልፀዋል።

AGOA ምንድነው?

African Growth and Opportunity Act (AGOA) የግብይት ስርዓት ነው፤ ይህ የግብይት ስርዓት የተወሰኑ የብቃት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ከሳሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ሸቀጦችን ያለቀረጥ ለአሜሪካ ገበያ እንዲሸጡ የሚፈቅድ ነው። #DW

@tikvahethiopia