TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Vote‼️

እጅግ በርካታ ከሚባሉ ከተሞች እንደሚደርሰን ጥቆማ የከተማ ውስጥ ውንብድና እና ዝርፊያ እየከፋ መጥቷል። የፖሊስ ስራ #አጠያያቂም እየሆነ እንደሆነ እየተነገረን ነው። በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች መንግስት የፖሊስ ሀይሉን ሊፈትሽ ይገባል ብለዋል። በሀገራችን ልንዘረፍ፤ አምሽተን ለመስራት ልንሳቀቅ አይገባም ሲሉ ይናገራሉ።
.
.
ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች እናተ በምትኖሩበት አካባቢና ከተማ የህዝብን ፀጥታ ለማስጠበቅ ብሎ መንግስት ያሰማራቸው የአካባቢና የከተማ ፖሊስ ላይ ያላችሁ ምልከታ ምን ይመስላል??

የአካባቢና የከተማ ፖሊስ ላይ #እምነት አላችሁ?

እምነት አለን
እምነት የለንም

🔹የሚመለለታችሁ አካላት ይህ የድምፅ አሰጣጥ ለቀጣይ ስራችሁ ግብአት ይሆናል ብለን እናስባለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Vote‼️

እጅግ በርካታ ከሚባሉ ከተሞች እንደሚደርሰን ጥቆማ የከተማ ውስጥ ውንብድና እና ዝርፊያ እየከፋ መጥቷል። የፖሊስ ስራ #አጠያያቂም እየሆነ እንደሆነ እየተነገረን ነው። በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች መንግስት የፖሊስ ሀይሉን ሊፈትሽ ይገባል ብለዋል። በሀገራችን ልንዘረፍ፤ አምሽተን ለመስራት ልንሳቀቅ አይገባም ሲሉ ይናገራሉ።
.
.
ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች እናተ በምትኖሩበት አካባቢና ከተማ የህዝብን ፀጥታ ለማስጠበቅ ብሎ መንግስት ያሰማራቸው የአካባቢና የከተማ ፖሊስ ላይ ያላችሁ ምልከታ ምን ይመስላል??

የአካባቢና የከተማ ፖሊስ ላይ #እምነት አላችሁ?

እምነት አለን
እምነት የለንም

🔹የሚመለለታችሁ አካላት ይህ የድምፅ አሰጣጥ ለቀጣይ ስራችሁ ግብአት ይሆናል ብለን እናስባለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹አማራ ክልል ውስጥ ወንጀል ሠርተው ሌላ ክልል #እንደበቃለን ብለው የሚያስቡ ካሉ #ተስፋቸውን ይቁረጡ፡፡›› የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ #ዮሐንስ_ቧያለው
.
.
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው በክልሉ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን በተከሰተው #ግጭት ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በግጭቱ ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች እና በደረሰው የንብረት ውድመት አዴፓ ማዘኑን የገለፁት አቶ ዮሐንስ ለተጎጅ ቤተሰቦችና ወገኖች #መፅናትን ተመኝተዋል፡፡

ጉዳቱ ከመድረሱ በፊት የክልሉ መንግሥት ሥጋቱን ያውቀው እንደነበር ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም ‹‹እንደስጋት በክልሉ የፖለቲካ ኃይሎች ግጭትን ለዓላማቸው መጠቀሚያ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ግምቶች ነበሩን፤ ግን ከገመትነው #የፈጠነ ሆኖብናል›› ብለዋል። ይህን ያክል የንብረት እና የሰው ሕይወት ጠፍቷል ለማለት የቴክኒክ ቡድኑ የጥናት ምላሽ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል፡፡

ሕዝቡ ሕግና ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ በአዴፓ እና በክልሉ መንግሥት እምነት አጥቷል የሚሉ ሐሳቦች ይደመጣሉ በእናንተ በኩል ምን ግምገማ አለ? ተብሎ ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎችም አቶ ዮሐንስ ‹‹እንዲያውም አሁን ሕዝቡ በአዴፓ ላይ ከፍተኛ #እምነት የጣለበት ወቅት ነው፤ አዴፓ በሕዝቡ አመኔታ ማግኘቱን ተከትሎ #ለመነጣጠል የሚፈልጉ ኃይሎች የፈጠሩት ሴራ በመሆኑ ሕዝቡ ከጎናችን ሊሆን ይገባል›› ብለዋል፡፡ ‹‹በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶች የአዴፓ እና የአማራ ሕዝብ አንድነት የሚያስፈራቸው ኃይሎች የፈጠሩት ሴራ ነው›› በማለትም ተናግረዋል፡፡

ሕዝቡ መራር በሆነው በዚህ ጊዜ #አብሮነቱን እንዲያጠናክር የጠየቁት አቶ ዮሐንስ ‹‹አማራ ክልል ውስጥ ወንጀል ሠርተው በሌላ ክልል እንደበቃለን ብለው የሚያስቡ ካሉ ተስፋቸውን ይቁረጡ፤ ከአጐራበች ክልሎች እስከ ፌዴራል መንግሥት ድረስ ወንጀለኞችን ለመያዝ በጥምረት እየሠራን ነው›› ብለዋል፡፡ በክልሉ መሠል ችግር እንዳይከሰት ብቁ ዝግጅት እንደተደረም ተናግረዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም

Ethio-Telecom በምን ምክንያት #የቴሌግራም አገልግሎትን #ሊያግድ እንደቻለ በቂና አሳማኝ ማብራሪያ #በግልፅ ሊሰጥ ይገባል። መሰል ድርጊቶች ዜጎች በመንግስት ላይ ያላቸውን #እምነት ይሸረሽረዋል። ድርጅቱ የተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎት ተመልሷል ቢልም ቴሌግራም ያለproxy server/VPN ውጪ እንደታገደ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia