TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሹመት🔝

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ክብር አቶ #ገዱ_አዳርጋቸው ለሁለት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ሹመት መስጠታቸው
ተገለጸ ፡፡

ሹመቱ የተሰጣቸው የስራ ኃላፊዎች አቶ #ዮሐንስ_ቧያለው እና አቶ #አለባቸው_የሱፍ ናቸው፡፡

አቶ ዮሐንስ ቧያለው ከህዳር ሰባት ቀን 2011 ዓ.ም ጀምረው በርዕሰ መስተዳደሩ ጽ/ቤት የበይነ መንግስታት ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ተሹመዋል፡፡

አቶ አለባቸው የሱፍ ደግሞ ከህዳር አንድ ቀን 2011 ዓ.ም ጀምረው የዚሁ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ መሾማቸው ታውቋል፡፡

አቶ ዮሐንስ ቀደም ሲል በመንግስት የተለያዩ ኃላፊነቶች ሲሰሩ መቆየታቸውና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በመምህርነት እያገለገሉ ነበር፡፡

አቶ ዮሐንስ ቧያለው በቅርቡ ብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን አካሄዶ ስሙን ወደ አማራ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (አዴፓ)ሲቀይር የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው እንደተመረጡ ይታወሳል፡፡

አቶ አለባቸው የሱፍም በተለያዩ የመንግስት የስራ ሓላፊነቶች በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ምንጭ፦ የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት(Amhara Democratic Party /ADP/ CC office)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹አማራ ክልል ውስጥ ወንጀል ሠርተው ሌላ ክልል #እንደበቃለን ብለው የሚያስቡ ካሉ #ተስፋቸውን ይቁረጡ፡፡›› የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ #ዮሐንስ_ቧያለው
.
.
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው በክልሉ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን በተከሰተው #ግጭት ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በግጭቱ ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች እና በደረሰው የንብረት ውድመት አዴፓ ማዘኑን የገለፁት አቶ ዮሐንስ ለተጎጅ ቤተሰቦችና ወገኖች #መፅናትን ተመኝተዋል፡፡

ጉዳቱ ከመድረሱ በፊት የክልሉ መንግሥት ሥጋቱን ያውቀው እንደነበር ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም ‹‹እንደስጋት በክልሉ የፖለቲካ ኃይሎች ግጭትን ለዓላማቸው መጠቀሚያ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ግምቶች ነበሩን፤ ግን ከገመትነው #የፈጠነ ሆኖብናል›› ብለዋል። ይህን ያክል የንብረት እና የሰው ሕይወት ጠፍቷል ለማለት የቴክኒክ ቡድኑ የጥናት ምላሽ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል፡፡

ሕዝቡ ሕግና ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ በአዴፓ እና በክልሉ መንግሥት እምነት አጥቷል የሚሉ ሐሳቦች ይደመጣሉ በእናንተ በኩል ምን ግምገማ አለ? ተብሎ ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎችም አቶ ዮሐንስ ‹‹እንዲያውም አሁን ሕዝቡ በአዴፓ ላይ ከፍተኛ #እምነት የጣለበት ወቅት ነው፤ አዴፓ በሕዝቡ አመኔታ ማግኘቱን ተከትሎ #ለመነጣጠል የሚፈልጉ ኃይሎች የፈጠሩት ሴራ በመሆኑ ሕዝቡ ከጎናችን ሊሆን ይገባል›› ብለዋል፡፡ ‹‹በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶች የአዴፓ እና የአማራ ሕዝብ አንድነት የሚያስፈራቸው ኃይሎች የፈጠሩት ሴራ ነው›› በማለትም ተናግረዋል፡፡

ሕዝቡ መራር በሆነው በዚህ ጊዜ #አብሮነቱን እንዲያጠናክር የጠየቁት አቶ ዮሐንስ ‹‹አማራ ክልል ውስጥ ወንጀል ሠርተው በሌላ ክልል እንደበቃለን ብለው የሚያስቡ ካሉ ተስፋቸውን ይቁረጡ፤ ከአጐራበች ክልሎች እስከ ፌዴራል መንግሥት ድረስ ወንጀለኞችን ለመያዝ በጥምረት እየሠራን ነው›› ብለዋል፡፡ በክልሉ መሠል ችግር እንዳይከሰት ብቁ ዝግጅት እንደተደረም ተናግረዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia