TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ተርኪዬ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ከአንካራ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት በድርጅቱ የቱርክ ሪፐብሊክ የሀገሪቱን ስም ከ "ቱርክ" ወደ "ተርኪዬ" መቀየሩን ዛሬ አሳውቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ፤ ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ለዋና ፀሃፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተላከው ደብዳቤ ለሁሉም ጉዳዮች የሀገሪቱ ስም ከ "ቱርክ" ይልቅ "ተርኪዬ" የሚለው ሥራ ላይ እንዲውል ተጠይቋል።

ቃል አቀባዩ ፤ የአገሪቱ የስም ለውጥ ደብዳቤው ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ (የግንቦት 2014 ዓ/ም) የመዝጊያ መግለጫ በቅዱስ ሲኖዶስ ፅ/ቤት እየተሰጠ ይገኛል። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ርእሰ መንበርነት ሲመራ የነበረ የብፁዓን አበው ሊቀነ ጳጳሳት ጉባኤ ነበር። ጉባኤው ለ16 ቀናት በዝግ የተካሄደ…
#Update

ከመግለጫው ፦

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በአሁን ደረጃ በአገራችን ያለው የሰላም እጦት ላይ በሰፊው ውይይት አካሂዷል።

ውይይቱን ተከትሎ በቀጣይ ጦርነትና የእርስ በርስ ግጭት ተወግዶ አጠቃላይ ሰላም በሚሰፍንበት መልኩ ተነጋግሮ ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት እንዲቻል፣ ቤተ ክርስቲያኗ #የአስታራቂነት ሚናዋን መጫወት እንድትችል ለማድረግ ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ እንዲቀርብ ማድረጉን አሳውቋል።

በክልል ትግራይ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቤተ ክርስቲያኒቱን አስመልክተው በ30/04/2014 እና በ3/06/2014 ዓ.ም. ባወጡት መግለጫን ምልዓተ ጉባኤው ገምግሞ በቀጣይ የክልሉ አባቶች በማዕከል እንደ ቅዱስ ሲኖዶስ አባልነታቸው ለአገር አንድነትና ሰላም በጋራ እንዲሠሩ ምልዓተ ጉባኤው ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን በተከሰተው የሰላም እጦት ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ፣ በካህናት አገልጋዮች እንዲሁም በምእመናኖች ላይ የደረሰውና እየደረሰ ያለው የሰው ሕይወት መጥፋትና የአብያተ ክርስቲያናት መቃጠል፣ የበዓል ማክበሪያ ቦታዎች መነጠቅ አስመልክቶ ጉባኤው የተነጋገረ ሲሆን አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡ፣ በቀጣይም በመንግሥት በኩል አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግ ጥያቄ ቀርቧል።

እስከአሁን ድረስ በቤተ ክርስቲያን ላይ ደረሰ የተባለው ችግር በዓይነትና በቁጥር ተለይቶ ለሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል መንግሥት አካላት እንዲቀርብ መደረጉም ተገልጿል።

(የግንቦት ወር 2014 የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መጠናቀቅን አስመልክቶ አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የሰጡት ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#USA

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ጋር ተገናኝተው መምከራቸውን በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ አሳውቋል።

ምክክሩ ፥ በኢትዮ-አሜሪካ ግንኙነት መጠናከር ላይ በሚኖር ሚና ፣ ስለ #አገራዊ_ምክክሩ (National Dialogue) እንዲሁም በኃይለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ መሆኑ ተገልጿል።

ውይይቱ መቼ እንደተደረገ ኤምባሲው ቀን አልጠቀሰም።

የቀድሞው ጠ/ሚ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ ጥዋት ከአሁን የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፣ ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ እና ከሌሎች የፌዴራል እና የክልል ባለስልጣናት ጋር በመሆን በባሌ ሮቤ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውን ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተርኪዬ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ከአንካራ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት በድርጅቱ የቱርክ ሪፐብሊክ የሀገሪቱን ስም ከ "ቱርክ" ወደ "ተርኪዬ" መቀየሩን ዛሬ አሳውቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ፤ ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ለዋና ፀሃፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተላከው ደብዳቤ ለሁሉም ጉዳዮች የሀገሪቱ ስም ከ "ቱርክ" ይልቅ "ተርኪዬ" የሚለው…
ቱርክ (ተርኪ) ስሟን ወደ ተርኪዬ መቀየር ለም አስፈለጋት ?

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) በድርጅቱ የቱርክ /ተርኪ ስያሜ ወደ ተርኪዬ መቀየሩን ዛሬ በይፋ አሳውቋል።

ይህ ተርኪዬ የሚለው ስያሜ የቱርክን ሕዝብ ባህል፣ ሥልጣኔ እና ዕሴቶችን በበለጠ የሚወክል አገላለጽ ነው " በማለት ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ባለፈው ወር ተናግረው ነበር።

ለውጡን ተከትሎ TRT የተሰኘው የሀገሪቱ የመንግስት ወዲያው ተግባራዊ አድርጓል።

ሚዲያው ለሀገሪቱ ስያሜ ለውጥ ምክንያት ብሎ ካስቀመጣቸው ነገሮች መካከል " ቱርኪ " የሚለው ስያሜ ምዕራባውያን በዓል ወቅት ለምግብ ከምትቀርበው የዶሮ ዝርያ ጋር መያያዙ እንደሆነ ገልጿል።

በተጨማሪ በኬምብሪጅ የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ላይ ለቃሉ ተሰጠው ትርጉም እንደሆነ ተመላክቷል። በመዝገበ ቃላቱ 'ተርኪ' የሚለው ቃል፤ 'ሙሉ በሙሉ ያልተሳካ' ወይም 'ውድቀት የሆነ ነገር' የሚል ትርጓሜን ይሰጣል።

የቱርክ /ተርኪ መንግስት ሀገሪቱን በአዲስ ስያሜ ተርኪዬ ለማስተዋወቅ ዘመቻ ማድረግ የሰነባበተ ሲሆን በአገሪቱ ተመርተው ወደ ውጪ የሚላኩ ሁሉም ምርቶች ላይ አዲሱ ስያሜ እንዲሰፍር ተደርጓል።

ካለፈው ጥር ወር ጀምሮም  "ሄሎ ተርኪዬ" የሚል የቱሪዝም ዘመቻ እየተካሄደ ነው።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#Hulugram

አንድ አፕ፣ ብዙ አማራጭ ! በሁሉግራም ይሸምቱ፣ ፎቶዎን ያጋሩ፣ አዲስ ስው ይተዋወቁ!

ሁሉም በሁሉግራም ይቻላል!
Download Hulugram SuperApp 👇

https://play.google.com/store/apps/details?id=plus.ride.huluchat
#ችሎት

6 ሺህ 1 መቶ ብር የወራዊ ደሞዝ ተከፋይ ለነበረ የመንግስት ሠራተኛ በተጭበረበረ መንገድ 69 ሺህ 1መቶ ብር እንዲከፈለው ያደረጉ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።

የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቃቤ ህግ ጥቅምት 12/2014 ዓ.ም የቀረበለት ክስ መርምሮ ውሳኔ መስጠቱን አስታውቋል።

የቅጣት ውሳኔ ያሳለፈው በምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ የሙስና ወንጀል ህጎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13 አንድ ሐ ላይ የተመለከተውን ተላልፈው በተገኙ 3 ግለሰቦች ላይ ነው።

• 1ኛ ተከሳሽ ጌታቸው ሻሜቦ በምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የሂሳብ ባለሙያ ፤

• 2ኛ ማርቆስ ሄራሞ ተከሳሽ በምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የክፍያ ክፍልና የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ቡድን መሪ፤

• 3ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ታዬ አለሙ በምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት መምህር፤

ለ3ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ታዬ ሊከፈል የሚገባው እና ያልተጣራ ወራዊ ደምወዝ ጣሪያ 6 ሺህ 1መቶ 46 ብር ሆኖ በዚህ ደምወዝ የተጣራ በእጁ ላይ መድረስ የነበረበት 4 ሺህ 7መቶ 12 ብር ከ32 ሳንቲም መሆን ነበረበት።

1ኛ ተከሳሽ ለወረዳው ፋይናንስ ከተሰጠው የክፍያ ትዕዛዝ ውጭ ያለ አግባብ ያልተጣራ የወር ደምወዝ ጣሪያ 69 ሺህ 1መቶ 46 ብር በእጁ የሚደርስ የተጣራ ገንዘብ ደምወዝ መጠን 41ሺህ 6መቶ አራት ብር ከ68 ሳንቲም የሚያገኝ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ የደምወዝ ፔሮል አዘጋጅቷል።

2ኛ ተከሳሽ በበኩሉ የተዘጋጀውን የደምወዝ ፔሮል አጽድቆ ወጪ እንዲሆን አዟል።

3ኛ ተከሳሽ ሊከፈለው የማይገባውን ገንዘብ በልዩነት 36 ሺህ 8 መቶ 92 ብር ከ36 ሳንቲ ለ1 ወር ከምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሂሳብ ቁጥር ተቀናሽ ተደርጎ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግለሰቡ የሂሳብ ቁጥር ገቢ ተደርጓል።

ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነትና በልዩ ወንጀል ተካፋይነት በመንግሥት ሀብት ላይ ጉዳት በማድረስ ለራሳቸው ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በፈጸሙት የመንግሥት ስራን በማያመች አኳኋን በመምራት የሙስና ወንጀል አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል።

የክሱን ሂደት ሲመረምር የቆየው የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 12/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሾች በምክንያትነት ያቀረቡትን የቅጣት ማቅለያ እና ገንዘቡ ለመንግሥት ተመላሽ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት ውሳኔ ሰጥቷል።

በዚህ መሠረት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 2 ዓመት እና የ3 ሺህ ብር መቀጮ እንዲሁም 3ኛው ተከሳሽ 1 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

ምንጭ፦ የሃዲያ ዞን ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ክልል ካለፈው ሰኞ ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል።

እየተቆራረጠም ቢሆን የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል።

በዚህ የኃይል እጦት ደግሞ የትግራይ ትልቁ የህክምና ተቋም አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ስራዎቹን ሊቋርጥ ተገዷል።

ሆስፒታሉ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በሚያገኘው የነዳጅ አቅርቦት ኃይል እያገኘ መቆየቱን የገለፀ ሲሆን አሁን ላይ ኤሌክትሪክ በመቋረጡ በቂ ነዳጅም ማግኘት ባለመቻሉ አገልግሎት ለማቋረጥ ተገጿል።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ክብሮም ገ/ስላሴ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ቃል "በኤሌክትሪክ በሚሰራ ቬንቲሌተር ለሚተነፍሱ የነበሩ ታካሚዎች ይሰጥ የነበረው ህክምና ተቋርጧል። ከቀናቸው በፊት ለተወለዱ ህፃናት ይሰጥ የነበረ ሜካኒካል የትንፋሽ እና ሙቀት የመስጠት አገልግሎት ተቋርጧል። ያለ ኤሌክትሪክ ኦፕሬሽን መስራት አንችልም። ስለዚህ ሆስፒታሉ እንደ ሪፈራል ሆስፒታል ይሰጠው የነበረው አገልግሎት ሁሉ አቋርጧል። ማድረግ የምንችለው ለድንገተኛ አደጋ የመጀመሪያ ደረጃ ድጋፍ መስጠት ወይም መድሃኒት እንዲገዙ ወረቀት ፅፎ መስጠት እንጂ ምርመራ እና ክትትል ማድረግ የለም " ብለዋል።

አክለውም " ይህን ችግር እንዲፈቱልን የሚገባቸው መንግስታዊ ያልሆኑ አለም አቀፍ ድርጅቶች አሉ ለእነሱ አንድ በአንድ እየሄድን ያለውን ችግር ገልፀናል ኤሌክትሪክ ማግኘት የሚያስችለን ነዳጅ ማስገባት የሚችሉ እንደ OCHAና WFP ያሉ ድርጅቶችን አሳውቀናቸው ነበር ይሁንና ያደረጉልን ምንም አይነት ድጋፍ የለም ። ይሄ ትልቅ ሆስፒታል እንዳይዘጋ ለማድረግ ምንም አይነት ምላሽ አለመስጠታቸው ያሳዝናል" ሲሉ አስረድተዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tig-06-03

@tikvahethiopia
የ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት ፦

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባ በ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

በዚህም መሰረት ለ2015 በጀት ዓመት ለመደበኛ ወጪ ብር 347.12 ቢሊዮን፣ ለካፒታል ወጪ ብር 218.11 ቢሊዮን እንዲሁም ለክልል መንግሥታት ድጋፍ ብር 209.38 ቢሊዮን እና ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ብር 12.0 ቢሊዮን የተያዘ ሲሆን አጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀት ብር 786.61 ቢሊዮን ሆኖ ቀርቧል፡፡

ከ2014 በጀት ዓመት በጀት ጋር ሲነጻጸር የብር 111.94 ቢሊዮን ወይም የ16.59 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

ም/ ቤቱ በቀረበለት የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀት ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ በመንገድ ግንባታ ምክንያት ዝግ የሚሆን መንገድ !

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከወሎ ሰፈር ወደ ኡራኤል አደባባይ መታጠፍ የሚያስችል የትራፊክ መብራት ኡራኤል ቤተክርስቲያን መዳረሻ አካባቢ ሊተከል እንደሆነ አሳውቋል።

በዚህም ከቅዳሜ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ እስከ ሰኞ ጠዋት ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ከወሎ ሰፈር ወደ ኡራኤል እና ከኡራኤል ወደ አትላስ እና ወደ ወሎ ሰፈር ሚወስዱት መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ሆነው ይቆያሉ ብሏል።

አሽከርካሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ከወሎ ሰፈር አደባባይ በቦሌ ሩዋንዳ ወደ አትላስ እና ኡራኤል፤ እንዲሁም ከመገናኛ በ22 ወደ ኡራኤልና አትላስ ለሚሄዱ ደግሞ ከጎላጎል ህንፃ በኤድናሞል በኩል ወደ አትላስ የሚወስደውን እና ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለስልጣኑ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#WFP #ETHIOPIA

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ወደ ትግራይ እና በግጭት ወደ ተጎዱ አካባቢዎች ኮንቮይዎችን መላክ መቀጠሉን እንደገፋበት አመልክቷል።

በሚያዝያ/ግንቦት በ1,045 የጭነት ተሽከርካሪዎች አማካኝነት 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ቶን ምግብ ማቅረብ መቻሉንና 350 ሺህ ሰዎችን በህይወት አድን ምግብ መድረስ መቻሉን ድርጅቱ አሳውቋል።

ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ቀጣይነት ያለው የአቅርቦት ፍሰት እንዲኖር እና ድጋፍ እንዲደርሳቸው ለማድረግ ከባለሥልጣናት ጋር እየሰራ መሆኑንም ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እርምጃ ተወስዶባቸዋል " በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ሰው በማገት ፣ ሰው በመግደል ሲፈለጉ የነበሩ 3 ግለሰቦች እርምጃ እንደተወሰደባቸው የመተማ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት አስታወቀ። የወረዳው ሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ፥ " የማህበረሰብ እንቅስቃሴ ሲያውኩ የነበሩ ሶስት ጸረ-ሰላም ኃይሎች በጥምር የጸጥታ ኃይል (ልዩ ኃይል ፣ ፀረሽምቅ እና ፖሊስ) ርምጃ ተወስዶባቸዋል " ብሏል። በጣምራ…
#Metema

የመተማ ወረዳ ፖሊስ #ሰው_በማገት_ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ግለሠቦች በተካሄደ ኦፕሬሽን መመታታቸውን እንዲሁም ቆስለው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳወቀ።

ትላንት በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ መቃ ቀበሌ ልዩ ስሙ " ጎርድም " በተባለው ተራራ በተደረገ ኦፕሬሽን ሰው በማገት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ 4 ግለሰቦች መመታታቸው እና ቆስለው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

ፖሊስ ይፋ ባደረገው መረጃ ባዜ ብርሀኑ እና ላቀው የኔሁን የተባሉ ግለሰቦች የተመቱ ሲሆን አያናው አማረ እና ወርቁ ድረስ የተባሉ ግለሰቦች ደግሞ ቆስለው በህግ ጥላ ስር መሆናቸው ተገልጿል።

ከቀናት በፊት በዚሁ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ሰው በማገት ፣ ሰው በመግደል ሲፈለጉ የነበሩ 3 ግለሰቦች እርምጃ እንደተወሰደባቸው የወረዳው ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፤ በወረዳው አኩርፈው ሆነ ሸፍተው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በተደረገው የምህረት አዋጅ እድል ተጠቅመው በሰላም ገብተው ከህብረተሰቡ ጋር በሰላም እንዲኖሩ ፖሊስ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia