#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ በመንገድ ግንባታ ምክንያት ዝግ የሚሆን መንገድ !

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከወሎ ሰፈር ወደ ኡራኤል አደባባይ መታጠፍ የሚያስችል የትራፊክ መብራት ኡራኤል ቤተክርስቲያን መዳረሻ አካባቢ ሊተከል እንደሆነ አሳውቋል።

በዚህም ከቅዳሜ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ እስከ ሰኞ ጠዋት ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ከወሎ ሰፈር ወደ ኡራኤል እና ከኡራኤል ወደ አትላስ እና ወደ ወሎ ሰፈር ሚወስዱት መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ሆነው ይቆያሉ ብሏል።

አሽከርካሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ከወሎ ሰፈር አደባባይ በቦሌ ሩዋንዳ ወደ አትላስ እና ኡራኤል፤ እንዲሁም ከመገናኛ በ22 ወደ ኡራኤልና አትላስ ለሚሄዱ ደግሞ ከጎላጎል ህንፃ በኤድናሞል በኩል ወደ አትላስ የሚወስደውን እና ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለስልጣኑ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia