TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ምርጫ2013

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ድምፅ የሚሰጡት እንዴት ነው?

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በምርጫ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የመራጮች ምዝገባ በኦላይን በዩኒቨርሲቲያቸው እያሉ ሲያካሂዱ ነበር።

አሁን ላይ ተማሪዎች ወደቤታቸው ተመልሰዋል በምርጫው እንዴት መሳተፍ ይችላሉ ? ለሚለው ጥያቄ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚውኬሽን ኃላፊ ወዘሪት ሶልያና ሽመልስ ለቲክቫህ ቤተሰቦች ምላሽ ሰጥተዋል።

ወ/ሪት ሶሊያና ፥ ተማሪዎች በኦንላይን ምዝገባ ተመዝግበው እንደጨረሱ የተሰጣቸው #የማረጋገጫ_ወረቀት እንዳለ በመጠቆም ተማሪዎች ያንን ማረጋገጫ ይዘው አቅራቢያቸው የሚገኝ የምርጫ ጣቢያ መሄድ እንዳለባቸው አሳውቀዋል።

በአካባባያቸው ያለው የምርጫ ጣቢያ በትክክል የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆነው መመዝገባቸውን ሲያረጋግጥ ድምጻቸውን እንዲሰጡ ያደረጋል ሲሉ አስረድተዋል።

ስለዚህ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰኞ ድምፅ ለመስጠት ምን ማድረግ አለባችሁ ?

- በኦንላይን ላይ ምዝገባችሁን ያጠናቀቃሁበትን ማረጋገጫ ወረቀት መያዝ ይጠበቅባችኋል።

- በመኖሪያ አከባቢያችሁ አቅራቢያ ወደሚገኝ ምርጫ ጣቢያ በማቅናት የማረጋገጫ ወረቀቱን በማሳየት የምርጫ ወረቀት ማግኘት ትችላላችሁ።

- ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ እንድትይዙ ይመከራል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

አንድ መራጭ ለክልል ምክር ቤት መቀመጫ ምን ያህል እጩዎችን መምረጥ ይችላል?

ለክልል ወይም ለከተማ ም/ቤት መቀመጫ አንድ መራጭ መምረጥ የሚችለው የእጩዎች ብዛት እንደየምርጫ ክልሉ ይለያያል።

አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 1 እጩ፣ እንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 3 እጩዎች አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ደግሞ ላይ 9 እጩዎች አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 14 እጩዎች ወይም ሌላ ቁጥር ያለው የመቀመጫ ብዛት ሊኖራቸው ይችላል።

ብዛቱ የሚወሰነው የምርጫ ክልሉ በክልል ምክር ቤቱ ባለው የመቀመጫ ቁጥር ብዛት ነው።

በመሆኑም አንድ መራጭ በክልል ምክር ቤት ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ መምረጥ የሚችለው የዕጩዎች ብዛት በክልል ምክር ቤት ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ ከላይ ተፅፎ ይገኛል።

በዚህም መሰረት አስፈጻሚዎች የድምፅ መስጫ ወረቀት ሲሰጡ ለመራጩ በምርጫ ጣቢያ ውስጥ እስከ ስንት እጩ መምረጥ እንደሚችል ያስረዳሉ።

ሆኖም ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች አንድ ዕጩ ብቻ የሚመረጥ ይሆናል። ስለዚህም ከዚህ ቁጥር ገደብ በላይ ምልክት የተደረገባቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ዋጋ አይኖራቸውም።

ስለሆነም ድምፅዎን ሲሰጡ በወይን ጠጁ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወረቀት #አንድ በክልል ምክር ቤት ወረቀት ደግሞ ወረቀቱ ላይ በተጻፈው እና ምርጫ አስፈጻሚው በሚነግርዎ ቁጥር መሰረት መሆኑን አይርሱ። ከተፈቀደው የእጬ ቁጥር በላይ ምልክት አያድርጉ።

#ሼር #Share

(የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ)

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ኢሰመኮ ዛሬ በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ በምርጫው የሰብዓዊ መብት ሁኔታዎችን የሚከታተሉ ባለሙያዎችን እንዳሰማራ አሳውቋል።

ኢሰመኮ ባለሙያዎቹን ያሰማራው በተሻሻለው የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀፅ 6 በተሰጠው ስልጣንና ሀላፊነት
መሰረት ነው።

በዚህም ምርጫ በሚካሄድባቸው በሁሉም ክልሎች የክትትል ቡድኖችን ማሰማራቱን አስታውቋል፡፡

ቡድኖቹ በሚሰማሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ በምርጫው እለት እና ከምርጫው በኋላ ባሉት ቀናት በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ምልከታ ያደርጋሉ ያለው ኮሚሽኑ መራጮችን፣ የምርጫ አስተባባሪዎችን፣ የፀጥታ አካላትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ እጩዎችን፣ ታዛቢዎችን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማነጋገር መረጃዎችን እንደሚሰባስቡ ገልጿል፡፡

በፖሊስ ጣቢያዎች እና በሕክምና ተቋማት በመገኘት አስፈላጊውን ክትትል እንደሚያደርጉም ነው ያስታወቀው።

የኮሚሽኑን መለያ ካርድ (ባጅ) በመያዝ ለሚሰማሩት የክትትል ቡድኑ አባላት አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግላቸው ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#አልዓይን

@tikvahethiopia
ምን ያህል ታዛቢዎች ምርጫውን ይታዘባሉ ?

እስካሁን ባለው መረጃ 6ኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ ከቦርዱ ፈቃድ የወሰዱ የሀገር ውስጥ ታዛቢ ድርጅቶች 42 ናቸው።

በቁጥር ሲሰላ ወደ 46,000 በላይ የምርጫ ታዛቢዎች ምርጫውን ለመታዘብ ከቦርዱ እውቅና አግኝተዋል።

ለታዛቢነት ፍቃድ የመስጠቱ ሂደት ባለማብቃቱ ቁጥሩ ወደ 50 ሺህ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ዓለም አቀፍ ታዛቢዎችን በተመለከተ የትላንቱን ሳይጨምር እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ከተለያዩ ተቋማት የመጡ ቁጥራቸው 120 የሚሆኑ ታዛቢዎች ባጅ ወስደዋል።

ማስታወሻ፦ የምርጫ ታዛቢዎች ፍቃድ የመስጠቱ ስራ ባለመጠናቀቁ በቀጣይ ቀናት የታዛቢዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፍቃድ ሳይኖር (የምርጫ ጣቢያ ኮድ ሳይሰጣቸው) የተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ ይሰጣል ?

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፍቃድ ሳይኖር (የምርጫ ጣቢያ ኮድ ሳይሰጣቸው) የተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች እንደነበሩ መግለፁ አይዘነጋም።

አዲስ አበባ ላይ 2 እና ድሬዳዋ ላይ 6 የምርጫ ጣቢያ ኮድ ሳይሰጣቸው ተከፍተው ተገኝተዋል ፤ ከዚህም ጣቢያዎች ጋር በተያያዘም እንዴት ነው የሚሆነው የድምፅ መስጫ ቀን የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው።

ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ የሰጡት ምላሽ ፦

"... በዕለቱ እዛው ድጋሚ ህጋዊ ምዝገባ እያደረግን ዜጎች እንዲመርጡ እናደርጋለን።

ምርጫ ጣቢያው ክፍት ነው የሚሆነው የተመዘገቡ ዜጎች የመራጮች ካርዳቸውን እና መታወቂያቸውን ይዘው ይመጣሉ በዛ መሰረት እዛ ጣቢያ ላይ መመዝገባቸው ካወቅን በኃላ የድጋሚ ምዝገባ እያደረግን ትክክለኛ ምዝገባ ከሆነ ትክክለኛነቱን እያረጋገጥን ችግር ያለበትን ደግሞ እዛው ድጋሚ ምዝገባ እየተደረገ አስፈፃሚዎች የዜጎችን ድምፅ መስጠት ያረጋግጣሉ።

ሌላ ቦታ ላይ ምዝገቡን መንካት፣ መቀየር፣ ድጋሚ ምዝገባ ማከናወን ከዚህ በፊት የተመዘገበን ሰው እንዳይመዘገብ ማድረግ ወይም እንደአዲስ መመዝገብ አይቻልም በሌሎች ሁኔታዎች ላይ ለዚህ ግን በልዩ ሁኔታ እዛ ምርጫ ጣቢያ ላይ የተመዘገቡ ዜጎችን መብት ለማረጋገጥ ሲባል መራጮች ካርዳቸውን ይዘው ሲመጡ ህጋዊ ምዝገባ እየተደረገ ድምፃቸውን እንዲሰጡ ይደረጋል። አዲስ አበባ ላይም ድሬዳዋ ላይም በዚህ ሂደት በምርጫ ጣቢያዎቹ ድምፅ መስጠት ይከናወናል"

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ኢ-ቪዛ (E-Visa) እና በመዳረሻ በሚሰጥ ቪዛ (Visa on Arrival) አገልግሎት ቆሟል ?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትናንት ምሽት በይፋዊ ድረ-ገፁ ላይ እንዳሰፈረው ከኢሚግሬሽን ቢሮ በመጣ መመርያ መሰረት የE-Visa እና Visa on Arrival አገልግሎቶች ከአርብ እኩለ-ለሊት ጀምሮ ለግዜው አይሰጡም።

ይህ ግን የትራንዚት መንገደኞችን እንደማይመለከት አክሎ ገልጿል።

የኢሚግሬሽን ድረ-ገፅ ደግሞ የ E-Visa ድረ-ገፁ እድሳት ላይ እንዳለ ገልፆ ተገልጋዮች ለቪዛ ጉዳዮች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ኤምባሲ ወይም ቆንፅላ ቢሮ እንዲያመሩ ይመክራል።

በዚህ ዙርያ ኢሚግሬሽን ዛሬ ጥዋት ለኢትዮጵያ ቼክ በሰጠው ቃል አገልግሎቱ የተቋረጠው በድረ-ገጹ ላይ የማሻሻያ ስራ እየተከናወነ በመሆኑ ነው።

የማሻሻያ ስራው በቅርቡ ይጠናቀቃል ሲል ገልጿል።

በዚህም መሰረት የ E-Visa ያላቸው እንዲሁም Visa on Arrival የሚፈልጉ ተጓዦች ወደ ኢትዮጵያ የሚደረግ የአየር ጉዞን ማድረግ አይችሉም፣ አየር መንገዶችም አያሳፍሩም።

ይህም ማለት ፦
- ፓስፖርት፣
- ቢጫ ካርድ (የትውልደ ኢትዮጵያዊ ካርድ)
- የተለጠፈ ቪዛ ያላቸው ብቻ መጓዝ ይችላሉ።

ይህ ጉዳይ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ወደ ኢትዮጵያ በረራ የሚያደርጉ አየር መንገዶችን ይመለከታል።

#ኢትዮጵያቼክ

@tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ነገ ሰኔ 14/2013 ከሚካሄደው 6 ኛው ብሔራዊ ምርጫ በፊት ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ለመስጠት እንዲንቀሳቀሱ የተደረገውን የመጨረሻ ዝግጁነት ለመገምገም የብሔራዊ ምርጫ ደኅንነት ስትራቴጂ ማዘዣ ዛሬ ጠዋት መምከሩን አሳውቀዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ የጸጥታ ዘርፉ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲሠማራ እና በቴክኖሎጂ ድጋፍ ለተለዩ እና ለሚከሠቱ አደጋዎች ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት ሰፊ ሥራ ተሠርቷል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ባሰራጩት መልዕክት ፥ "ሁሉም ዜጎች ነገ ድምፅ ለመስጠት ሲወጡ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲከታተሉ አበረታታለሁ" ብለዋል። አክለውም "መንግሥት ለሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ቀን በቂ ዝግጅት ማድረጉን አረጋግጣለሁ" ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች በዛሬው ዕለት "የምርጫ ወቅት እና ሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት" ላይ ትኩረቱት ያደረገ አጭር ገለፃ በቀጥታ በቴሌግራም Voice Chat ይኖረናል።

ገለፃው በዋነኝነት በዚህ ለሀገሪቱ ወሳኝ በሆነ ወቅት ላይ በሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት ሊፈጠር የሚችለውን ችግር በማስቀረቱ ረገድ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለን እንጠብቃለን።

አቅራቢዎቹ : ከመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (CARD) በፍቃዱ ኃይሉ እና ከኢትዮጵያ ቼክ ኤልያስ መሰረት ናቸው።

ሰዓት : ከቀኑ 9:30 ጀምሮ ለ30 ደቂቃ ቆይታ ያደርጋለን።

ማስታወሻ፦ ቴሌግራም መተግበሪያችሁ Update ካልተደረገ ይህን የቀጥታ ስርጭት መከታተል ስለማትችሉ መተግበሪያችሁ Update መደረጉን አረጋግጡ።

@tikvahethiopia
ነገ በአዲስ አበባ ሁሉም የትራንስፖርት አማራጮች አገልግሎት ይሰጣሉ።

ለነገው ምርጫ በአዲስ አበባ ሁሉም የትራንስፖርት አማራጮች ከማለዳው 12:00 ጀምሮ አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

በእለቱ የትራንስፖረት አገልገሎት አሰጣጡን የሚከታተል፣ የሚመራና ከየዘርፉ የተውጣጣ ግብረ ሃይል ተቋቁሟል ተብሏል።

የታክሲ አሽከርካሪዎችና ማህበራት፤ የብዙሃን ትራንስፖርት አቅራቢ ድርጅቶች ማለትም አንበሳ፣ ሸገርና ሃይገር ባሶች፣ የላዳ ሾፌሮች እና ማህበራት ጋር ውይይት በማድረግ የስራ መመሪያ ተላልፏል።

የአንበሳ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት በእለቱ 665 አውቶብሶችን ለትራንስፖርት ዝግጁ ማድረጉም ተረጋግጧል።

የከተማው የትራንስፖርት ቢሮ ፥ የትራንሰፖርት እጥረት ይከሰትባቸዋል የተባሉ አካባቢዎችን በመለየት ተጨማሪ ስምሪቶች ይሰጣል ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
Live stream started
Live stream finished (31 minutes)
በሀላባ ቁሊቶ የሰዓት ገደብ ተጥሏል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ፅ/ቤት ነገ ከሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ከሰኔ 12/2013 ዓ/ም ጀምሮ ተግበራዊ የሚደረግ የሰዓት ገደብ መጣሉን አሳውቋል።

እነዚህም መሰረት ፦

- ምርጫው ተካሄዶ እስክጠናቀቅ ድረስ ባለ ሁለት እግር ሞተር ሠይክሎች ከ12:00 ሠዓት በኃለ ማንኛውንም እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ተከልክሏል።

- ማንኛውም የህዝብ ማመላላሻና የባለ ሶስት እግር በጀጅ ተሽከርከሪዎች ከ1:00 ሠዓት በኃለ መንቀሠቀስ አይችሉም።

- የግል የቤት መኪና ከ3:00 በኃለ እንዳይንቀሳቀስ ገደብ ተጥሏል።

- ማንኛውም ሠው እስከ ምርጫ ማብቂያ ማምሻ ከ3:00 ሠዓት በኃላ እንቅስቃሴ መካሄድ አይቻልም።

- መጠጥ ቤቶች ፣ የንግድ ሱቆች ፣ ሆቶሎች ፣ ቡና ቤቶችና ግሮሰሪዎች ከሰኔ 12 ጀምሮ 2:00 ሠዓት ላይ መዘጋት ይገባቿል።

ይህን የሠአት ገደብ በሚተላለፍ አካል ላይ የፀጥታ አካላት እርምጃ እንደሚወስዱ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

"ነገ ስራ ዝግ ሆኖ ይውላል"

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ነገ እንደማንኛውም የስራ ዝግ ቀን/እንደ በዓል ቀን ስራ ዝግ ሆኖ እንደሚውል በድጋሚ ተናግረዋል።

ከትራንስፖርት ፣ ከመሰረታዊ እና ከድንገተኛ አገልግሎት (ዋና ዋና አገልግሎት) ከሚሰጡት ተቋማት በስተቀር ሌሎች ስራ ዝግ ሆነው ይውላሉ ብለዋል።

የትራንስፖርት ፣ የመሰረታዊ ፣ ድንገተኛ እና አስቸኳይ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትና ሰራተኞች አሰራራቸውን ይዘው ይቀጥላሉ። ከዛ ውጭ ያሉት ግን ተዘግተው መራጮች ድምፅ የሚሰጡበት ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

"አንዳንድ ቦታዎች ላይ ነገ ስራ ካልገባችሁ ትቀጣላችሁ/ስራ ግዴታ መግባት አለባችሁ" የሚሉ አካላትን አይትናል ያሉት ወይዘሪት ሶሊያና ይህ ህጋዊ አይደለም፤ የአዋጁን አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታን የሚጥስ ተግባር ነው ብለዋል።

"ስራ ግዴታ መግባት አለባችሁ" የሚሉ አሰሪዎች ህግን ከሚጥስ የወንጀል ተግባር እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

#TikvahFamily
@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

(ሰኔ 13 ቀን 2013 ዓ/ም)

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በኃላ ዕለታዊ መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫውን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላት በቦታው ተገኝተዋል።

ውድ አባላት በመግለጫው ላይ የሚነሱትን ዋና ዋና ጉዳዮችን የምንልክላችሁ ይሆናል።

ከዚህ ባለፈ በቀጥታ መግለጫውን በ Voice Chat መከታተል እንደምትችሉ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
#LIVE

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዕለታዊ መግለጫን በቀጥታ በ Voice Chat ይከታተሉ : https://publielectoral.lat/tikvahethiopia?voicechat=70755b28db3a6d96d7

@tikvahethiopia
Live stream finished (11 minutes)
#ምርጫ2013

የቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተ በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ሰማያዊ ሳጥኖች ተከፍተው መገኘታቸውን ምርጫ ቦርድ አሳወቀ።

ሳጥኖቹን ከፍተው የተገኙበት ምርጫ ክልሎች ላይ አንዳንዶቹ ወደወንጀል ምርመራ ሲላኩ አንዳንዶቹ #ምርጫ_እንዳይካሄድ ተወስኖባቸዋል።

- ደንቢያ የምርጫ ክልል ሰማያዊ ሳጥኖቹ ተከፍተው ፤ ውስጣቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የሚያሳየው የቡክሌት ተከፍቶ ውስጡ ያለውን ነገር አይተው ተገኝቷል፤ በዚህ ምክንያት 3 አስፈፃሚዎች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ለፌዴራል ፖሊስ ደብዳቤ ተፅፏል።

ደምቢያ ምርጫ ክልል የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶችን መነካካት ፣ መክፈት በጥብቅ የተከለከለ የወንጀል ተግባር በመሆኑን አስፈፃሚዎች ምርመራ እንዲደረግባቸው ተልኳል።

በደምቢያ ምርጫ ክልል ምርጫው #አይካሄድም

- ተውለደሬ 1 እና 2 ሰማያዊ ሳጥን ተከፍቶ ውስጡ ያሉእጩዎች እነማን እንደሆኑ ፣ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ ያሉትን እጩዎች የማየት (ፓርቲዎች ቅሬታ አለን ስላሉ ነው እዩ ተብለን ነው) በሚል ተክፍቶ ታይቷል።

በዚህ ምክንያት ተውለደሬ 1 እና 2 ነገ ድምፅ አይሰጥም፤ ታግዷል።

- ግንደበረት (ኦሮሚያ) ነገ ድምፅ #አይሰጥም ፦ ድምፅ የማይሰጥበት ምክንያት የድምፅ መስጫ ወረቀት እና ቁሳቁስ ስለተከፈተ ሳይሆን የአስፈፃሚዎች እጥረት ነበር። ከዚህ ውጭ ግን ወረዳው አስፈፃሚዎችን አሰልጥኖ ለማስፈፀም ለማሰማራት ሲል በመገኘቱ ገንደበረት ላይ ድምፅ አይሰጥም።

- ነገሌ ምርጫ ክልል (ጉጂ-ኦሮሚያ) ፦ በምርጫ ክልሉ የሚወዳደር የግል ተወዳዳሪ በምርጫ መስጫ ወረቀቱ ላይ ዝርዝሩ ባለመካተቱ ባቀረበው ቅሬታ መሰረት ቦርዱ ምርጫውን ወደ ጳጉሜ 1 አዛውሮታል።

#TikvahEthiopia #SolianaShimeles

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምርጫ2013 የቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተ በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ሰማያዊ ሳጥኖች ተከፍተው መገኘታቸውን ምርጫ ቦርድ አሳወቀ። ሳጥኖቹን ከፍተው የተገኙበት ምርጫ ክልሎች ላይ አንዳንዶቹ ወደወንጀል ምርመራ ሲላኩ አንዳንዶቹ #ምርጫ_እንዳይካሄድ ተወስኖባቸዋል። - ደንቢያ የምርጫ ክልል ሰማያዊ ሳጥኖቹ ተከፍተው ፤ ውስጣቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የሚያሳየው የቡክሌት ተከፍቶ ውስጡ ያለውን ነገር…
#Update

ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ ሳጥን ተከፍቶ ውስጡ ያለው የድምጽ መስጫ ወረቀት ማሸጊያው ባለመከፈቱ ምክንያት የምርጫ ሂደቱ እንዲቀጥል የተወሰነባቸው የምርጫ ክልሎች ስለመኖራቸው አሳውቋል።

እነዚህም ፦

• ስንቄ 1 እና 2 የምርጫ ቁሳቁስ ሳጥኑ (ሰማያዊ ሳጥን) ወድቆ በመሰበሩ የተወዳዳሪ ፖርቲዎች ወኪል ባሉበት ቃለጉባኤ ተይዞ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ የታሸገው ባለመከፈቱ ምርጫው እንዲካሄድ ተወስኗል።

ይህ ምርጫ ጣቢያ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚወዳደሩበት ነው።

• መተማ ላይ የምርጫ ቁሳቁስ መያዣ ሳጥኑ (ሰማያዊ ሳጥኑ) ቢነካካም የድምጽ መስጫ ወረቀቶቹ ማሸጊያ ባለመከፈቱ ምርጫው እንዲቀጥል ቦርዱ ወስኗል።

#SolianShimeles #TikvahEthiopia #TikvahFamily

@tikvahethiopia