ነገ በአዲስ አበባ ሁሉም የትራንስፖርት አማራጮች አገልግሎት ይሰጣሉ።

ለነገው ምርጫ በአዲስ አበባ ሁሉም የትራንስፖርት አማራጮች ከማለዳው 12:00 ጀምሮ አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

በእለቱ የትራንስፖረት አገልገሎት አሰጣጡን የሚከታተል፣ የሚመራና ከየዘርፉ የተውጣጣ ግብረ ሃይል ተቋቁሟል ተብሏል።

የታክሲ አሽከርካሪዎችና ማህበራት፤ የብዙሃን ትራንስፖርት አቅራቢ ድርጅቶች ማለትም አንበሳ፣ ሸገርና ሃይገር ባሶች፣ የላዳ ሾፌሮች እና ማህበራት ጋር ውይይት በማድረግ የስራ መመሪያ ተላልፏል።

የአንበሳ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት በእለቱ 665 አውቶብሶችን ለትራንስፖርት ዝግጁ ማድረጉም ተረጋግጧል።

የከተማው የትራንስፖርት ቢሮ ፥ የትራንሰፖርት እጥረት ይከሰትባቸዋል የተባሉ አካባቢዎችን በመለየት ተጨማሪ ስምሪቶች ይሰጣል ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia