#ምርጫ2013

በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፍቃድ ሳይኖር (የምርጫ ጣቢያ ኮድ ሳይሰጣቸው) የተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ ይሰጣል ?

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፍቃድ ሳይኖር (የምርጫ ጣቢያ ኮድ ሳይሰጣቸው) የተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች እንደነበሩ መግለፁ አይዘነጋም።

አዲስ አበባ ላይ 2 እና ድሬዳዋ ላይ 6 የምርጫ ጣቢያ ኮድ ሳይሰጣቸው ተከፍተው ተገኝተዋል ፤ ከዚህም ጣቢያዎች ጋር በተያያዘም እንዴት ነው የሚሆነው የድምፅ መስጫ ቀን የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው።

ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ የሰጡት ምላሽ ፦

"... በዕለቱ እዛው ድጋሚ ህጋዊ ምዝገባ እያደረግን ዜጎች እንዲመርጡ እናደርጋለን።

ምርጫ ጣቢያው ክፍት ነው የሚሆነው የተመዘገቡ ዜጎች የመራጮች ካርዳቸውን እና መታወቂያቸውን ይዘው ይመጣሉ በዛ መሰረት እዛ ጣቢያ ላይ መመዝገባቸው ካወቅን በኃላ የድጋሚ ምዝገባ እያደረግን ትክክለኛ ምዝገባ ከሆነ ትክክለኛነቱን እያረጋገጥን ችግር ያለበትን ደግሞ እዛው ድጋሚ ምዝገባ እየተደረገ አስፈፃሚዎች የዜጎችን ድምፅ መስጠት ያረጋግጣሉ።

ሌላ ቦታ ላይ ምዝገቡን መንካት፣ መቀየር፣ ድጋሚ ምዝገባ ማከናወን ከዚህ በፊት የተመዘገበን ሰው እንዳይመዘገብ ማድረግ ወይም እንደአዲስ መመዝገብ አይቻልም በሌሎች ሁኔታዎች ላይ ለዚህ ግን በልዩ ሁኔታ እዛ ምርጫ ጣቢያ ላይ የተመዘገቡ ዜጎችን መብት ለማረጋገጥ ሲባል መራጮች ካርዳቸውን ይዘው ሲመጡ ህጋዊ ምዝገባ እየተደረገ ድምፃቸውን እንዲሰጡ ይደረጋል። አዲስ አበባ ላይም ድሬዳዋ ላይም በዚህ ሂደት በምርጫ ጣቢያዎቹ ድምፅ መስጠት ይከናወናል"

@tikvahethiopia