#ምርጫ2013

ኢሰመኮ ዛሬ በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ በምርጫው የሰብዓዊ መብት ሁኔታዎችን የሚከታተሉ ባለሙያዎችን እንዳሰማራ አሳውቋል።

ኢሰመኮ ባለሙያዎቹን ያሰማራው በተሻሻለው የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀፅ 6 በተሰጠው ስልጣንና ሀላፊነት
መሰረት ነው።

በዚህም ምርጫ በሚካሄድባቸው በሁሉም ክልሎች የክትትል ቡድኖችን ማሰማራቱን አስታውቋል፡፡

ቡድኖቹ በሚሰማሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ በምርጫው እለት እና ከምርጫው በኋላ ባሉት ቀናት በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ምልከታ ያደርጋሉ ያለው ኮሚሽኑ መራጮችን፣ የምርጫ አስተባባሪዎችን፣ የፀጥታ አካላትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ እጩዎችን፣ ታዛቢዎችን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማነጋገር መረጃዎችን እንደሚሰባስቡ ገልጿል፡፡

በፖሊስ ጣቢያዎች እና በሕክምና ተቋማት በመገኘት አስፈላጊውን ክትትል እንደሚያደርጉም ነው ያስታወቀው።

የኮሚሽኑን መለያ ካርድ (ባጅ) በመያዝ ለሚሰማሩት የክትትል ቡድኑ አባላት አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግላቸው ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#አልዓይን

@tikvahethiopia