TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MoSHE

የኢፌዴሪ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው ደብዳቤ #ሀሰተኛ ነው አለ።

ዛሬ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ለደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ እንደተጻፈ የሚገልጽ ደብዳቤ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተዘዋወረ ነው።

ደብዳቤው “የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስለመስጠት” የሚል አርዕስት ያለው ሲሆን ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎችን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እውቅና ውጭ ምደባ ማካሄዱን እንዲያቆም የሚያስጠነቅቅ ይዘት አለው።

በዚህ ጉዳይ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶን ለ "ኢትዮጵያ ቼክ" በሰጡት ቃል ደብዳቤው ሀሰተኛ መሆኑ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ፥ ደብዳቤው ተጻፈ በተባለበት የታሕሳስ ወር የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ገና መሰጠት አልተጀመረም ነበር ብለዋል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደዚህ ዓመት የተሸጋገረው የ2012 ዓ.ም ፈተና ከካቲት 19 ጀምሮ እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን ውጤቱ ይፋ የተደረገው በመጋቢት ወር አጋማሽ እንደነበር አስታውሰዋል።

ሚኒስትሩ ፥ የተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምደባ በሚያዚያ ወር የተከነወነ መሆኑ በመግለፅ ደብዳቤው ተጻፈ በተባለበት ታሕሳስ ወር ምንም አይነት የተማሪዎች ምደባ እንዳልነበር አስረድተዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል ደብዳቤውን እርሳቸው እንዳልጻፉት ገልጸዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል በታህሳስ ወር የተማሪዎችን ምደባ የተመለከተ ደብዳቤ ሊጻፍ እንደማይችል አክለዋል።

ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ማምሻው በፌስቡክ ገጹ በለጠፈው አጠር ያለ መልዕክት “ዩኒቨርስቲያችንን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጩ ወሬዎች አሳሳችና የውሸት መሆናቸውን እንገልጻለን” ብሏል።

#ኢትዮጵያቼክ

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ኢ-ቪዛ (E-Visa) እና በመዳረሻ በሚሰጥ ቪዛ (Visa on Arrival) አገልግሎት ቆሟል ?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትናንት ምሽት በይፋዊ ድረ-ገፁ ላይ እንዳሰፈረው ከኢሚግሬሽን ቢሮ በመጣ መመርያ መሰረት የE-Visa እና Visa on Arrival አገልግሎቶች ከአርብ እኩለ-ለሊት ጀምሮ ለግዜው አይሰጡም።

ይህ ግን የትራንዚት መንገደኞችን እንደማይመለከት አክሎ ገልጿል።

የኢሚግሬሽን ድረ-ገፅ ደግሞ የ E-Visa ድረ-ገፁ እድሳት ላይ እንዳለ ገልፆ ተገልጋዮች ለቪዛ ጉዳዮች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ኤምባሲ ወይም ቆንፅላ ቢሮ እንዲያመሩ ይመክራል።

በዚህ ዙርያ ኢሚግሬሽን ዛሬ ጥዋት ለኢትዮጵያ ቼክ በሰጠው ቃል አገልግሎቱ የተቋረጠው በድረ-ገጹ ላይ የማሻሻያ ስራ እየተከናወነ በመሆኑ ነው።

የማሻሻያ ስራው በቅርቡ ይጠናቀቃል ሲል ገልጿል።

በዚህም መሰረት የ E-Visa ያላቸው እንዲሁም Visa on Arrival የሚፈልጉ ተጓዦች ወደ ኢትዮጵያ የሚደረግ የአየር ጉዞን ማድረግ አይችሉም፣ አየር መንገዶችም አያሳፍሩም።

ይህም ማለት ፦
- ፓስፖርት፣
- ቢጫ ካርድ (የትውልደ ኢትዮጵያዊ ካርድ)
- የተለጠፈ ቪዛ ያላቸው ብቻ መጓዝ ይችላሉ።

ይህ ጉዳይ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ወደ ኢትዮጵያ በረራ የሚያደርጉ አየር መንገዶችን ይመለከታል።

#ኢትዮጵያቼክ

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የህዝብ እና ቤት ቆጠራ #የፊታችን መጋቢት 29 ይካሄዳል " ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሠተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ ይህን ያሳወቀው ለኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ ማጣሪያ ድረገፅ ነው።

ቃላቸውን ለመረጃ ማጣሪያው የሰጡት የአገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሳፊ ገመዲ " የህዝብና ቤት ቆጠራ የፊታችን መጋቢት 29 ይካሄዳል ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሠተኛ ነው " ብለዋል።

የህዝብና ቤት ቆጠራ የሚካሄድበትን የጊዜ ሠሌዳ በፌዴሬሽንና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች እንደሚወስን ገልጸው ምክር ቤቶቹ ምንም አይነት ውሳኔ አለማሳለፋቸውን ገልፀዋል።

ም/ቤቶቹ 4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ  እንዲራዘም በተደጋጋሚ መወሰናቸው ይታወሳል።

#ኢትዮጵያቼክ

@tikvahethiopia