TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrLiaTadesse

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 105 ደርሰዋል!

በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 659 የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠኝ (9) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 105 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊት የጅማ ከተማ ነዋሪ ፤ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ በፊት ከሊባኖስ የመጣች።

ታማሚ 2 - የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።

ታማሚ 3 - የ40 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።

ታማሚ 4 - የ13 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 5 - የ73 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ ከአሜሪካ የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ።

ታማሚ 6 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ነዋሪ፤ ከጅቡቲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 7 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ነዋሪ፤ ከጅቡቲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 8 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ነዋሪ፤ ከጅቡቲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 9 - የ38 ዓመት ኢኳቶሪያል ጊኒያዊ ከእንግሊዝ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,890
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 659
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 9
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ያሉ - 84
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 1
• አዲስ ያገገሙ - 1
• አጠቃላይ ያገገሙ - 16
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 105

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙ ሪፖርት ከተደረጉት 9 ሰዎች መካከል (ከታማሚ 9) ከኢኳቶሪያል ጊኒ ዜግነት ካለው ውጪ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ከኢትዮጵያውያኑ መካከል ደግሞ ሶስት (3) ወጣቶች ከጅቡቲ የመጡ የድሬዳዋ ነዋሪዎች ናቸው። በጅቡቲ ቫይረሱ እጅግ በጣም በፍጥነት እየጨመረ ነው። ከመጀመሪያው ኬዝ አንስቶ በቲክቫህ የተቀመጡትን የጅቡቲን መረጃዎች መለስ ብላችሁ ተመልከቱ።

ትላንትም እንደገለፅነው በጅቡቲ መስመር ያለው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጥንቃቄ ካልተደረገበት ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል ነው። መንግስት ያለውን አቅም ተጠቅሞ በጅቡቲ በኩል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ሊቆጣጠር ይገባል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoHE

በጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ደኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የሚመራ ቡድን ለለይቶ ማቆያና የህክምና ማዕከላት የተዘጋጁ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

የተጎበኙት ስፍራዎች የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ፤ የቅዱስ ጴጥሮስ ቲቢ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፤ የጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፤ የሚሊኒየም አዳራሽ ፤ የካቲት 12 ሆስፒታል እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ናቸው፡፡

(ጤና ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከመሞት መሰንበት ይሻላል!

(በጋዜጠኛ ተስፋዬ ማሞ)

በየአቅጣጫው "ሞትን በእጃችን ካልጨበጥነው" የሚል አይነት ከፍ ያለ መዘናጋት ይታያል። ይህ ደግሞ ከፍ ያለ ዋጋ ማስከፈሉ የሚቀር አይመስልም።

አንድን በግ ለመግዛት ያለተገቢ ጥንቃቄ ስንት ሰው ሽንጡን እንደሚጨብጠው ላቱን ይዞ እንድሚያልመዘምዘው ፤ ቀንዱን ይዞ እንደሚወዘውዘው ስታስቡ በአንድ በግና በብዙ በግ ገዥ መካከል በሚደረግ ቀጥተኛ ንኪኪ የኮሮና ቫይረስ ከአንዱ ሰው እጅ ወይም አካል ከተነሳ ምን ያህል ሊዛመት እንደሚችል መገመት ይቻላል።

እባካችሁ ከቻልን ቢቀርብን...የግድ ከሆነ ደግሞ በቻልነሁ ሁሉ እንጠንቀቅ።

ከመሞት መሰንበት ይሻላልና!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Djibouti

የጅቡቲን የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ውጤት እጠበቅን ነው። በሰዓታት ውስጥ ይፋ ይደረጋል።

የጅቡቲ ጉዳይ ይህን ያህል የሚያስጨንቀን በእነዚህ ምክንያቶች ነው ፦

- በርካታ ዜጎቻችን ከጅቡቲ እየተመለሱ በመሆናቸው።

- የተሽከርካሪና የባቡር ትራንስፖርት ቢቁምም በተለያዩ መንገዶች በእግርም ጭምር ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ በመሆኑ።

- የጭነት ተሽከርካሪዎች አሁንም ወደጅቡቲ ይሰራሉ። ሹፌሮቻችን ደህንነታቸው ካልተጠበቀ በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ስለሚሆኑብን።

ዛሬ የድ/ዳ/አስ/ጤ/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ባወጡት መግለጫቸው በተለይ በጅቡቲ በኩል ስጋት በመኖሩ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለህዝብ አሳውቀዋል፦

- በተሽከርካሪዎች ላይ የመድሃኒት ርጭት የማካሄድ ስራ እየተሰራ ነው።

- ለሹፌሮች የሙቀት ልኬት እየተደረገላቸው ይገኛል። ስልክ እና የመኖሪያ አድራሻቸው ተወስዶ ክትትል እየተደረገ ነው።

- በእግር የሚመጡ የጅቡቲ ተመላሾች በኬላዎች እንዲሰባሰቡ በማድረግ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲቆዩ እየተደረገ ነው (ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲና ሃይስኩል)

#DrLemlem #TIKVAH #DMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከተለየዩ አገሮች ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ሰዎች የለይቶ ማቆያ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስን ጎበኙ።

ካምፓሱ በዋናነት ከውጭ አገሮች መጥተው ለአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ በተዘጋጁ ሆቴሎች ለመቆየት አቅም ለሌላቸው ኢትዮጵያውያን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ይታወሳል።

የሚኒስትሯ ጉብኝት በዋናነት በካምፓሱ ውስጥ የሚከናወኑ አገልግሎት አሰጣጦች ምን እንደሚመስሉ ለመገምገም መሆኑ ነው የተገለጸው።

በጉብኝታቸውም ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና በጉዳዩ ከሚሰሩ ሌሎች አካላት ጋር ተወያይተዋል። አሁን ላይ በካምፓሱ ከተለያዩ አገሮች የመጡ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 321 ሰዎች ያሉ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 49ኙ ሴቶች ናቸው።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KENYA

ከደቂቃዎች በፊት የኬንያ ጤና ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓት 1,115 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 16 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተግልጿል። በሀገሪቱ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 262 ደርሷል።

ዛሬ ሪፖርት ከተደረጉት ከአስራ ስድስቱ (16) ኬዞች መካከል አስራ አምስቱ (15) የኬንያ ዜጎች ሲሆኑ አንደኛው የውጭ ሀገር ዜጋ ነው።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት ሰባት (7) ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 60 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሞት እንዳንሸምት እንጠንቀቅ!

(በጋዜጠኛ ጥላሁን በየነ)

አስቸኳይ አዋጁ ከወዴት አለ ? ወንድሜ ካልሞተ ፣ እህቴ ካልሞተች ፣ አባቴ ካልሞተ ፣ እናቴ ካልሞተች ፣ ሚስቴ ካልሞተች ፣ ባሌ ካልሞተ ፣ ልጄ ካልሞተ ፣ ጓደኛዬ ካልሞተ በስተቀር የኮቪድ19 ወረሽኝ ምን ያህል ገዳይ እንደሆነ ለማወቅ አልቻልንም።

ዛሬም በርካቶች ዓለም በምን ያህል ጭንቀት እና ዜጎች ለህልፈተ ሞት እየበቁ በሚሊዮን የሚቆጠሩም ከቤታቸው እንዲቀመጡ ተደርገው እኛ በከፍተኛ ቸለተኝነት እንገኛለን።

ይህ ምስል በጀርመን አደባባይ እና በቄራ ገበያ በግን ለመግዛት በግን ለመሸጥ የወጡ ናቸው። በስፍራውም የፀጥታ አካላቶች ይገኛሉ እባካቹ ሞትን ለመሸመት አንውጣ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሐመዱ ቡሐሪ የቅርብ ረዳት የነበሩት አባ ኪያሪ በኮሮናቫይረስ ከተያዙ በኋላ መሞታቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

ከፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ "የኪያሪ ህልፈትን ለሕዝቡ ሲያሳውቅ በጥልቅ ሐዘን" እንደሆነ ጠቅሷል።

"ኪያሪ በተደረገላቸው ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ህክምናም ሲከታተሉ መቆየታቸውን" መግለጫው ጨምሮ አመልክቷል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrDerejeDuguma

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ህክምና ማገገሚያ ሊሆን ነው!

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ደረጄ ድጉማ በዛሬው ዕለት የሆስፒታሉን ዝግጅት በተመለከቱበት ወቅት ነው ሆስፒታሉ ሙሉ ለሙሉ የኮሮና ቫይረስ ህክምና የሚሰጥበት እንዲሆን መመረጡን የተናገሩት፡፡

(የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ገላቭ የሰረቁ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገለፀ!

በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተያዙ ሰዎች ህክምና ከሚያገኙበት ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ግላቭ የስረቁ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የሆስፒታሉ ሁለት የቧንቧ ሰራተኞች ከሌሎች ሁለት (2) ግበረአበሮቻቸው ጋር በመሆን በየካ ክፍለ ከተማ ከሚገኘው ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል የሰሌዳ ቁጥር A 74615 አ/አ ቶዮታ የቤት መኪና ግምቱ ከ3 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ ግላቭ ሰርቀው በጥበቃ ሰራተኞችና በፖሊስ አማካኝነት እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ የኮተቤና አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ኮማንደር በየነ ዱሬሳ ገልፀዋል፡፡

ግለሰቦቹ ወንጀሉን መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ/ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ እንደፈፀሙ የጣቢያው የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ፀጋዬ ጴጥሮስ ተናገረው ተመሳሳይ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚረዳ ምርመራ የማስፋት ስራ ተጠናክሮ እንደቀጠለና በወንጀሉ የተጠረጠሩ አራት (4) ግለሰቦች በቁጥጥር ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WezeroLemlemBezabeh

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰቡ ላይ የሚስተዋለው መዘናጋት ለውጥ ካላመጣ ተጨማሪ የእንቅስቃሴ ክልከላዎችንና እገዳዎችን ለማድረግ እንደሚገደድ ገልጿል፡፡

የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ ከጅቡቲ ተመላሽ በሆኑና በድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ማቆያ በሚገኙ 574 ተመላሾች ላይ በተደረገ የናሙና ምርመራ ሶስቱ (3) ላይ ቫይረሱ ሊገኝ ችሏል ብለዋል፡፡

የበሮ ኃላፊዋ አክለውም ግለሰቦቹ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የሳቢያን ሆስፒታል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው ከነርሱ ጋር ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በመለየትም ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የፈረንሳይ ሆስፒታል ተገቢውን ክትትል እንዲያገኙ መለየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ማህበረሰቡ በበሽታው ላይ ያለው #መዘናጋት ከቀን በቀን እየጨመረ ነው ያሉት ወይዘሮ ለምለም የበሽታውን ገዳይነት በመረዳት የተቀመጡ የአካላዊ ርቀት ፤ ንፅህናን ባግባቡ የመጠበቅ እንዲሁም ተያያዠ ህጎችን በማክበር ለራሱም ሆነ ለማህበረሰቡ ጤና ሊጠነቀቅ ይገባል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በጅቡቲ ያለው የቫይረሱ ስርጭት ድሬዳዋን ስጋት ላይ ጥሏታል" - ወይዘሮ ለምለም በዛብህ /የጤና ቢሮ ኃላፊ/

ወይዘሮ ለምለም በዛብህ በአሁኑ ሰአት በጅቡቲ ያለው የቫይረሱ ስርጭት ድሬደዋን ስጋት ላይ እንደጣላት በዛሬው ማግለጫቸው አስታውቀዋል።

ማህበረሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ካላደረገ በርካቶችን በህመም እንዲሁም በሞት ማጣታችን የማይቀር ነው ይህ ከመሆኑ በፊት ግን ሁሉም ሚተላለፉ ህጎችን ማክበርና ማስከበር ይገባዋል ብለዋል።

አሁን የሚያተው መዘናጋት በዚህ ሚቀጥል ከሆነ አስተዳደሩ ማንኛውንም እቅስቃሴዎች ወደማገድ እንቅስቃሴ ይሸጋገራል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ወይዘሮ ለምለም ማህበረሰቡ አዳዲስ ሰዎችን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል በማሳወቅም ለቁጥጥር ስራው ውጤታማነት የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መላው የክርስትና እምነት ተከታይ የፋሲካ በዓልን ሲያከብር አካለዊ ርቀትን በመጠበቅና በቤቱ ሊሆን ይገባል ያሉት ወ/ሮ ለምለም ለበአሉ አክባሪዎችም መልካም በአልን ተመኝተዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ በመቐለና አርባ ምንጭ ከተሞች የአንበጣ መንጋ መልከታቸው የቲክቫህ አባላት ጠቁመዋል። መንጋው እንዳያርፍና ጉዳት እንዳያደርስም በተለያዩ ባህላዊ መንገዶችን ለማባራረር እንደተሞከረም የቤተሰባችን አባላት ገልፀዋል።

ይህን መልዕክት ያቀረብነው ከኮሮና ቫይረስ ጎን ለጎን በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚታየው የአንበጣ መንጋ ጉዳት እንዳይደርስ ትኩረት እንዲሰጠው ለማስታወስ ያህል ነው።

#NACHU #NATY #KIKI
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia