#DrLiaTadesse

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 105 ደርሰዋል!

በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 659 የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠኝ (9) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 105 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊት የጅማ ከተማ ነዋሪ ፤ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ በፊት ከሊባኖስ የመጣች።

ታማሚ 2 - የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።

ታማሚ 3 - የ40 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።

ታማሚ 4 - የ13 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 5 - የ73 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ ከአሜሪካ የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ።

ታማሚ 6 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ነዋሪ፤ ከጅቡቲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 7 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ነዋሪ፤ ከጅቡቲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 8 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ነዋሪ፤ ከጅቡቲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 9 - የ38 ዓመት ኢኳቶሪያል ጊኒያዊ ከእንግሊዝ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia