TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Djibouti

የጅቡቲን የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ውጤት እጠበቅን ነው። በሰዓታት ውስጥ ይፋ ይደረጋል።

የጅቡቲ ጉዳይ ይህን ያህል የሚያስጨንቀን በእነዚህ ምክንያቶች ነው ፦

- በርካታ ዜጎቻችን ከጅቡቲ እየተመለሱ በመሆናቸው።

- የተሽከርካሪና የባቡር ትራንስፖርት ቢቁምም በተለያዩ መንገዶች በእግርም ጭምር ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ በመሆኑ።

- የጭነት ተሽከርካሪዎች አሁንም ወደጅቡቲ ይሰራሉ። ሹፌሮቻችን ደህንነታቸው ካልተጠበቀ በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ስለሚሆኑብን።

ዛሬ የድ/ዳ/አስ/ጤ/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ባወጡት መግለጫቸው በተለይ በጅቡቲ በኩል ስጋት በመኖሩ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለህዝብ አሳውቀዋል፦

- በተሽከርካሪዎች ላይ የመድሃኒት ርጭት የማካሄድ ስራ እየተሰራ ነው።

- ለሹፌሮች የሙቀት ልኬት እየተደረገላቸው ይገኛል። ስልክ እና የመኖሪያ አድራሻቸው ተወስዶ ክትትል እየተደረገ ነው።

- በእግር የሚመጡ የጅቡቲ ተመላሾች በኬላዎች እንዲሰባሰቡ በማድረግ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲቆዩ እየተደረገ ነው (ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲና ሃይስኩል)

#DrLemlem #TIKVAH #DMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia