TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አጫጭር አለም አቀፍ መረጃዎች፦

- ፊልፒንስ ተጨማሪ የ73 ሰዎችን ኬዝ ሪፖርት አድርጋለች። አጠቅላይ 360 ሰዎችም በሀገሪቱ በቫይረሱ መጠቃታቸው ተነግሯል። በሀገሪቱ በ24 ሰዓት ውስጥ 6 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 25 ደርሷል።

- ቻይና በሀገሯ የሚዛመትን አዲስ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ መቆጣጠር ብትችልም ከውጭ የሚገቡ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ዛሬም መጨመር አሳይቷል።

- በኮሮና ቫይረስ 2 ሰዎች የሞቱባት፣ እንዲሁም 432 ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁባት ሲንጋፖር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ማንኛውም ግለሰብ ለአጭር ጊዜ ጉብኝት [በትራንዚትም ቢሆን] እንዳይመጣብኝ ብላለች።

- የሮማኒያ መንግስት በሀገሪቱ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ሞት መመዝገቡን አሳውቋል። ሟቹ እድሜያቸው 67 እንደሆነና የካንሰር ህመምተኛም እንደነበሩ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኳታር መንግስት ተጨማሪ ውሳኔዎች፦

- በጣም አስፈላጊ ለሆኑ ጉዳዮች ካልሆነ በቀር በትንንሽ መኪና ፣ በአውቶቡስ እና በጭነት መኪና ከሚደረግ ጉዞ በስተቀር በአንድ መኪና ውስጥ ከአንድ በላይ ሰው መግባት የለበትም፤ በመኪና ውስጥ መሰባሰብ ክልክል ነው።

- በየትኛውም ቦታ (ኮርኒሽን ጨምሮ) ምንም ዓይነት መሰባሰብ ሊኖር አይገባም። ለዚህም በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በተንቀሳቃሽ የፖሊስ መኪኖች (mobile patrols) አማካኝነት ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን፣ ይህን ተግባራዊ የማያደርጉ ሰዎች በቁጥጥር ስር ይውላሉ።

- መንግስት በምግብ አቅራቢ ድርጅቶች (Food delivery companies) ጥብቅ ቁጥጥር ያደርጋል፤ የንጽህና መስፈርቶችን በትክክል ያሟሉ መሆኑ ይጠበቅባቸዋል።

- በርካታ ሰዎች ሊሰባሰቡባቸው የሚችሉ የምግብ አቅራቢ ድርጅቶች ሊዘጉ ይችላሉ።

- ሁሉም የመዝናኛ ፓርኮች (parks) እና የባህር ዳር የሕዝብ መዝናኛዎች (public beaches) ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ይሆናሉ።

- እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ብዛት 481 የደረሰ ሲሆን፣ 27 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

#EthiopianEmbassyDoha
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ እንደመጣ ቢነገርም አሁንም በየአካባቢው የሚደረጉ 'የብልፅግና ፓርቲ' የታችኛው አመራሮች ስልጠና መቀጠላቸው እየተመለከትን ነው።

ቢያንስ የሚደረጉት ስብሰባዎች የማህበራዊ ርቀትን የጠበቁ አለመሆናቸው ለቫይረሱ ስርጭት የተሰጠውን ዝቅተኛ ቦታ የሚያሳይ ነው። የበላይ አመራሮች ጉዳዩን ያውቁት ይሆን?

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሎዛ አበራ ስለ ኮሮና ቫይረስ!

የሉሲዎቹ የፊት መስመር ፊት አውራሪ ጀግኒት ሎዛ አበራ አስደናቂ የውድድር አመትን እያሳለፈች ትገኛለች። ሎዛ ለመላው ኢትዮጵያውያን እህት ወንድሞቿ ራሳችንን በተገቢው መንገድ በማራቅ በቫይረሱ እንዳንያዝ ተገቢው ጥንቃቄ እንድናረግ ስትል መልእክቷን አስተላልፋለች።

ቲክቫህ ስፖርት ከሃትሪክ ስፖርት ጋር በመሆን በስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ እያካሄደ ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በ @tikvahethsport መከታተል ትችላላችሁ። ከኮሮና ቫይረስ ጋር የሚገናኙ የስፖርቱን ዓለም መረጃዎችም ማግኘት ትችላላችሁ።

@tikvahethsport @tikvahethiopia
የሉሲዎቹ ብሎም የአዳማ ከተማ ኮከቧዋ የፊት መስመር አጥቂ እዲሁም የ2011 ኮከብ ተጫዋች ሴናፍ ዋቁማ፦

ሴናፍ ዋቁማ በ @tikvahethsport እና በሀትሪክ ስፖርት አማካኝነት እየተካሄደ በሚገኘው የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሱን ከኮሮና ቫይረስ እንዲከላከል መልእክቷን አስተላልፋለች።

@tikvahethsport @tikvahethiopia
ዛሬ በአዲስ አበባ መካኒሳ ጉባኤ እግዚያብሄር ቤተክርስቲያን እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት የአምልኮ ኘሮግራም መካሄዱን ተገልፆልናል። ሁሉም ሰው እጁን በሳሙና ታጥቦ እንደገባ፣ በገባው ሰው መሃል መነካካትም አልነበረም፤ ሰላምታም በሩቁ ነበር፡፡ የመቀመጫ ወንበሮችም በርቀት ተነጣጥለው የተቀመጡ ነበሩ፡፡ መስኮቶች በሙሉ ክፍት ነበሩ፡፡ በቂ አየርም ነበር ተብለናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopianCOVID19MonitoringPlatform

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኢጀንሲ “የኢትዮጵያ የተቀናጀ የኮሮና ቫይረስ መከታተያና መቆጣጠሪያ ሲስትም” አዘጋጀ። አዲስ የተዘጋጀው ሲስተም ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት የምታደርገውን ጊዜ የማይሰጥ ርብርብ የሚያግዝ መሆኑንም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የተቀናጀ የኮቪድ19 መቆጣጠሪያ ስርአት - Ethiopian COVID-19 Monitoring Platform ምን ምን ሥራዎችን ይሰራል?

- ሃገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሆኑ ወቅታዊ የcovid-19 መረጃዎችን ለመከታተል፤

- ገላጭ በሆኑ የቦታ ማሳያ መረጃዎች ለማየት፤

- ስለ covid-19 ምልክቶች፣ ጥንቃቄዎች፣ ህክምናዎች እና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት፤

- ዜጎች በራሳቸውም ሆነ በሌሎች ላይ የሚያጋጥሟቸውን ጥርጣሬዎች ሪፖርት ለማድረግ፤

- የተለያዩ ሙያ እና አቅም ያላቸውን በጎ ፈቃደኞች ለመመዝገብ፤

- የተለያዩ እርዳታዎችን (በአይነትም ሆነ በገንዘብ) ለመሰብሰብ፤

- ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ መረጃ ያላቸውን ምንጮችን (ሊንኮችን) ለመጠቆም፤

- አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ-ልማቶችን (ሆስፒታል፣ ፋርማሲ፣ ፖሊስ ጣቢያ) ለማመላከት፤ እንዲሁም ሌሎችን መረጃዎች ለማሰራጨት የሚያገለግል ሲስተም ነው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በውጭ ሀገር የምትኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች መልዕክቶቻችሁን በፅሁፍ ፣ በድምፅ ፣ በቪድዮ የምትልኩት በ wtsegab@gmail.com በቴሌግራም @tsegabwolde @tsegabtikvah እናተ ባላችሁበት ምን አይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው?

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከሰሜን ጀርመን ቲክቫህ አባል፦

በጀርመን የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮ. አባል ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን እንዲሰጡ፣ ህዝቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ቢደረግ መልካም እንደሆነ አንስቷል።

የቤተስችን አባል በሚገኝበት ጀርመን ያሉ የኤፍ ኤም ሬድዮ ጣባያዎች ፣ ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን የጤና ባለሞያዎችን፣ ሳይንቲስቶችን እያጋባዙ ከህዝቡም ጥያቄ እየተቀበሉ ምላሽ እንዲሰጥባቸው እየሰሩ እንደሚገኙም ነግሮናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአርባ ምንጭ ከተማ በኮሮና ቫይረስ ጋር የተጠረጠረ የ36 ዓመት ግለሰብ በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ!

የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊና የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተሻለ ማናዬ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የ36 ዓመት ግለሰብ ጉንፋን መሰል ምልክቶች ታይቶበት አርባምንጭ ሆስፒታል ለህክምና በመጣበት ተጠርጥሮ ለጥንቃቄ ሲባል ለይቶ ማቆያ መዕከል ላይ እንዲቆይና የባለሙያ ክትትል እየተደረገለት ይገኛል፡፡

ግለሰቡም በቀን 07/07/2012 ዓ.ም. ለአንድ ቀን በኬንያ ለንግድ የተንቀሳቀሰ በመሆኑና ኬንያ ደግሞ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት አገር በመሆኑ ምክንያት ግለሰቡ ሊጠረጠር ችሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግለሰቡ በመልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛል ያሉት አቶ ተሻለ ከግለሰቡ ጋር ንኪኪ ያላቸዉን ሰዎች የመለየት ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡

ምንጭ፦ የጋሞ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአርባ ምንጭ ከተማ በኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዉ ግለሰብ በዛሬዉ ዕለት ናሙና ተወስዶ በምርመራ እንዲረጋገጥ የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ከክልል ጤና ቢሮ ጋር በጥምረት እየተሰራን እንደሚገኝ ተልጿል፡፡ ህብረተሰቡ በምርመራ ባልተረጋገጠ መረጃ መረበሽና መደናገር እንደሌለበት የዞኑ ጤና መምሪያ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች የታክሲ እና የባስ ማቆሚያዎች ሰዎች ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲቆሙ ለማድረግ ስራዎችም እየሰሩ እንደሆነ ነገርውናን። ይህ ስራ መላው ከተማይቱን ማዳረስ ይኖርበታል👍

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከUS ኒውዮርክ ቲክቫህ አባል፦

የምኖረው ኒውዮርክ ነው። በዚህች ከተማ ብቻ ኮሮና የያዘው ሰው በመላው አሜሪካ ያለውን 1/3ኛ ይሸፍናል፣ በአጭር ቀናት ከ8 ሺህ አልፏል።

ለዚህም ዋናው ምክንያቱ የአስተዳዳሪዎች ቸልተኝነት እንዳለ ሆኖ የመመርመር አቅም መጨመር ነው ፣ ማለትም ብዙ ሰው ስትመረምር ብዙ ሰው በበሽታው የተያዘ ታገኛለህ።

በሽታው ሲጀምር ትንሽ ሰዎችን ስለሚይዝ ያዘናጋል፣ ከተወሰነ ቀን በኋላ ደግሞ በጣም ብዙ ሰዎች ስለሚይዝ በድንጋጤ የምትሰራውን አታውቅም። ስለዚህ ሁላችንም ቀድመን የቤት ስራችንን እንስራ ፣ አንዘናጋ ቀልዱንም ካለፈ በኋላ እንደርስበታለን!

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ኒው ዴልሂ ህንድ የቲክቫህ አባል፦

በህንድ የሚገኘው የቤተሰባችን አባል መሰረት ማህበራዊ ርቀታችንን እንጠብቅ፣ በቻልነው አቅም እንጠንቀቅ፣ በሽታው ወደገጠር ከተስፋፋ ጉዳቱ ከፍተኛ ስለሚሆን የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ እንደሚገባ መልክት አስተላልፏል። በህንድ ኒው ዴልሂ ስላለውም ጥንቃቄ ነግሮናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከጀርመን ባቫሪያ የቲክቫህ አባል፦

ይህ ፈታኝ ወቅት እስኪያልፍ ድረስ ሁሉም ሰው በጤና ባለሞያዎች እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር በኩል የሚተላለፉትን የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ ቢያደርግ መልካም ነው። ጀርመኖች ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረጉ ነው፤ የሚተላለፉትንም የጥንቃቄ መልዕክቶች በመተግበር በሽታውን ለመቆጣጠር እየሰሩ ናቸው ይለናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከልን እና ላቦራቶሪን ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡

ከጤና ሚኒስትር ዴኤታዎች ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እና ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ጋር በመሆን ማዕከሉን የጎበኙት ሚኒስትሯ ከማዕከሉ አስተባባሪዎች ጋርም ውይይት አድርገዋል፡፡

#MoH #etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia