TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቡሌ ሆራ ገብተዋል...

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ቡሌ ሆራ ሲደርሱ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በቆይታቸውም ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ተስፋዬ በካፒታል ጋዜጣ ላይ ክስ መሰረቱ...

- ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት ካፒታል ጋዜጣ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁን በመጣስ ደሞዝ፣ ጥቅማ ጥቅም እና ባገለገልኩበት ቋንቋ የስራ ልምድ ከልክሎኛል ሲሉ በቦሌ ክፍለ ከተማ የስራ ክርክር ችሎት አርብ ታህሳስ 24/2012 ክስ መስርተዋል።

- ከሚያዚያ 2006 ጀምሮ በድርጅቱ ውስጥ በዘጋቢነት ሲያገለግሉ መቆየታቸውን በክሳቸው ውስጥ አመላክተዋል።

- ጋዜጠኛ ተስፋዬ በህጉ መሰረት የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ በመስጠት ድርጅቱን ለቀው ቢወጡም ድርጅቱ ግን አስፈላጊውን ክፍያ ህጉ በሚያዘው መሰረት ሳይከፍላቸው ቀርቷል። ድርጅቱ ሊከፍላቸው የሚገባውን የአገልግሎት ክፍያ እንዳልከፈላቸው፤ ፍርድ ቤቱም ይህንን እንዲያስፈፅምላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል።

- ጋዜጠኛ ተስፋዬ ክሱን ከመመስረታቸው በፊት በህጉ መሰረት ቅድመ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን እና ተከሳሽ (ካፒታል ጋዜጣ) ይህንን ባለመቀበላቸው ክስ መመስረታቸውን ተናግረዋል።

- በአጠቃላይ የተለያዩ ክፍያዎች ተደምረው 67 ሺህ 200 ብር እንዲከፈላቸው እና ለህግ ሂደቱ ያወጡትን 3 ሺህ ብር ድርጅቱ እንዲከፍላቸው ፍርድ ቤቱ እንዲፈርድላቸው ጠይቀዋል።

(አዲስ ማለዳ ጋዜጣ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ በሃጅ ጉዞ ዙሪያ መከሩ...

ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ በሃጅ ጉዞ ዙሪያ መክረዋል። ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረቢያ የሃጅ ጉዞን ለማመቻቸት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ያስታወቁ ሲሆን ስምምነቱ ከኢትዮጵያ የሚሄዱ የሃጅ ተጓዦች በቆይታቸው በቀላሉ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ያግዛል ተብሏል። ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እድሪስና የሳዑዲ አረቢያ የሃጅና ኡምራ ሚኒስትር ም/ል ዋና ፀሃፊ ሁሴን ቢን ናስር አል ሻሪፍ ናቸው።

#AlAin
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለጥያቄያችሁ መልስ...

ምርጫው የሚካሄድበት ቀን መቼ ነው?

- የጊዜ ሰሌዳው እስካሁን አልተወሰነም

የምርጫ 2012 የጊዜ ሰሌዳን በሚመለከት ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ጥያቄ አቅርበንላቸው ነበር። ምርጫ ቦርድ እስካሁን የጊዜ ሰሌዳውን እንዳልወሰነ፤ ምናልባትም በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሊያሳውቅ እንደሚችል ገልፀውልናል።

#TIKVAH_ETHIOPIA

#Election2012
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ...

- ሳወት “የትግራይ ጥቅም መሰረቱ ትግራይ ባደረገው ሁለንተናዊ ትግል ይረጋገጣል” በሚል መሪ ሃሳብ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የመጀመርያ ጉባኤውን አካሂዷል።

- በጉባኤው የተለያዩ የሕብረተሰ ክፍሎች፣ የፓርቲ ተወካዮች በተለይም ትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች፣ የምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት ተወካይ፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የሞያ ማህበራት፣ የዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ተገኝተው ነበር፡፡

- ጉባኤው ታህሳስ 25/2012 ዓ/ም ከሰአት በኋላ 3 ፕሬዚድየም አባላትን በመምረት በ7 ቡድን በመቧደን ሰፊ ውይይትና ክርክር በማድረግ የፓርቲው ፕሮግራም አፅድቋል፡፡ ታህሳስ በ26/2012ዓም ከሰአት በኋላ የፓርቲው ብሄራዊ አመራር (ማእከላዊ ኮሚቴ) መርጧል።

- በ3 የምርጫ አስፈፃሚዎች እየተመራ 2 ሴቶች ን ያካታተ 25 ብሄራዊ አማራር፤ 1 ሴት የተካታተችበት 5 የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት መርጧል።

- ማእከላዊ ኮሚቴው ድርጅቱ በሰጠው ስልጣን መሰረት የፓርቲው ሊቀ-መንበር አቶ ሃያሉ ጎዶፋይ እና ምክትል ሊቀመንበር ደግሞ አቶ አሉላ ሃይሉን የመረጠ ሲሆን የተለያዩ ተጨማሪ ሃለፊዎችንም በየዘርፉ ሰይሟል።

(አውሎ ሚዲያ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ እርምጃ ወሰደ...

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በታህሳስ 27/2012 ዓ.ም በአደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በ2012 ዓ/ም በተደጋጋሚ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር የተለያየ ተሳትፎ በነበራቸው ተማሪዎች ላይ የሚከተሉትን ውሳኔዎች ወስኗል፡፡

- ሁለት (2) ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ከትምህርት ገበታቸው እንዲሰናበቱ፣

- ሰባት (7) ተማሪዎች እያንዳንዳቸው ለሶስት(3) ዓመት ከትምህርት ገበታቸው እንዲታገዱ፣

- ስምንት (8) ተማሪዎች እያንዳንዳቸው ለሁለት(2) ዓመት ከትምህርት ገበታቸው እንዲታገዱ፣

- አንድ (1) ተባሮ የነበረ (በወቅቱ የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ያልነበረ) ነገር ግን በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ውስጥ ተሳታፊ የነበረ ዩኒቨርሲቲው ክስ መስርቶ ግለሰቡን በህግ ተጠያቂ እንዲያደርግ::

በመጨረሻም በወቅቱ ለሴኔቱ ውሳኔ ለቀረበ ተጨማሪ ስልሳ ዘጠኝ (69) ተማሪዎች ዲሲፕሊን ጉዳይ ላይ ተወያይቶ ጥፋታቸው በሂደት ተጣርቶ ወደ ፊት እርምጃ እንደሚወሰድባቸው እንዲሁም በቀጣይ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር በተለያየ መልኩ ተሳታፊ የነበሩ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ላይ እንደየጥፋታቸው እርምጃ እንደሚወሰድ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

(ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የህወሓት አንደኛ አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤ የአቋም መግለጫ : https://telegra.ph/TPLF-01-06
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ...

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቦርዱ ተመዝግበው የሚገኙ የአገር አቀፍና የክልል ፓርቲዎች (በአዋጅ ቁ. 1162/2011 መሰረት) ማሟላት ያሉባቸው ግዴታዎች መመርያ አጸደቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ 1162/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባን አስመልክቶ ታህሳስ 26 ቀን 2011 ዓ.ም መመሪያ አጽድቋል፡፡ መመሪያው ከመጽደቁ በፊት ከፓርቲዎች ጋር የተለያዩ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን ሰባት ፓርቲዎች ደግሞ በጽሁፍ ግብአታቸውን አስገብተዋል፡፡ በመመሪያው የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

1.ሁሉም ተመዝግበው የሚገኙ የፓለቲካ ፓርቲዎች በአዋጅ 1162/2011 የተቀመጠውን የመስራች አባላት ፊርማ ለማሟሟላት ሁለት ወራት የጊዜ ገደብ አላቸው፡፡

2.ጠቅላላ ጉባኤ ሳያካሂዱ ጊዜ ያለፈባቸው ፓርቲዎች በአዋጅ 1162 መሰረት አሟልተው በሁለት ወር ውስጥ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡

3.ጠቅላላ ጉባኤ በወቅቱ ያካሄዱ አገር አቀፍ ፓርቲዎች በአዲሱ አዋጅ 1162 ላይ የተቀመጠውን የጠቅላላ ጉባኤ መስፈርት በሟሟላት እስከ ጥር 2013 ዓ.ም ድረስ አጠናቀው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4.ጠቅላላ ጉባኤ በወቅቱ ያካሄዱ ክልላዊ ፓርቲዎች በአዲሱ አዋጅ 1162 የተቀመጠውን የጠቅላላ ጉባኤ መስፈርት ለሟሟላት እስከ ታህሳስ 2013 ድረስ አጠናቀው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

More : https://telegra.ph/NEBE-01-06

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን...

#AddisAbeba

የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን በበአላት መዳረሻ ወቅት የሚፈፀሙ ወንጀሎችንና ህገ - ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል ባከናወነው ኦፕሬሽን ህገ- ወጥ የጦር መሣሪያዎችን እና ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ጨምሮ በርካታ የወንጀል ፍሬዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል፦

- 11 ሽጉጦች ከ1600 በላይ መሰል የሽጉጥ ጥይቶች እንዲሁም ሀሰተኛ የብር ኖቶች ከማተሚያ ማሽን ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

- ቅዳሜ ታህሣስ 25/2012 ዓ.ም ከጧቱ 2፡30 አካባቢ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው ኒያላ ሞተርስ ጀርባ ወንጀል የፈፀሙ 6 አባላት ያሉት አንድ የዘረፋ ቡድን በህብረተሰቡ ትብብር በሰዓታት ልዩነት ተጠርጣሪዎቹን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

- በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ መርካቶ ሸክላ ተራ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ከበርበሬ ጋር ባዕድ ነገር ቀላቅለው ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 6 ተጠርጣሪዎች ከነ-ኤግዚቢቱ ሊያዙ ይችለዋል።

- ከተለያዩ ተሽከርካሪዎች ላይ 8 ተጠርጣሪዎች ከሰረቁት 331 ስፖኪዮ፤ የዝናብ መጥረጊያ እና ሌሎች የተሽከርካሪ አካላት፣ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ፣ላፕቶፕ ኮምፒውተር ፣ ቴሌቪዥን ፣ የቤት እና የግንባታ ዕቃዎች እንዲሁም ግራሙ ያልታወቀ አደዛዠ እፅ በተደረገ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ውሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወሎ ዩኒቨርሲቲ...

ከሰሞነኛው የወሎ ዩኒቨርሲቲ ግጭት የተጠረጠሩ 14 ግለሰቦች ተይዘዋል። ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አንድ መምህር መኖሩንም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር አባተ ጌታሁን ገልፀዋል። በግጭቱ የአንድ ተማሪ ህይወት መጥፋቱ አይዘነጋም። ለዚህም ኃላፊነቱን ይወስዳል የተባለ አንድ ተማሪ ሐሙስ ታህሳስ 23/2012 ዓ/ም በቁጥጥር ስር መዋሉ የሚታወስ ነው።

(#AlAin)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቡሌ ሆራ...

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ከኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር ውይይት ያደረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች የውሃና መንገድ መሰረተ ልማት ጥያቄዎች አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ተከታዩን ብለዋል፦

- መንግስት በጀመረው የብልጽግና ጉዞ የዜጎችን ጥያቄ መፍታት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል።

- በተያዘው ዓመት አገሪቱ በአጠቃላይ 50 ቢሊዮን ብር ለመንገድ መሰረተ ልማት በጀት ይዛለች። ከዚህ ውስጥም 2 ቢሊዮን ብር የሚሆነው በቡሌሆራና አካባቢው ለሚገነቡ መንገዶች የሚውል ነው።

- የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከሚመለከተው ሚኒስትር መስሪያ ቤት ጋር ተቀናጅቶ የተነሳውን የውሃ ችግር ለመፍታት እንዲሰራም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መመሪያ ሰጥተዋል።

- የአካበቢው ማህበረሰብ ብሎም የኦሮሞ ህዝብ ሌብነትን በመታገል እንዲሁም አንድነቱንና ሰላሙን በመጠበቅ ለተጀመረው የብልጽግና ጉዞ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፦

- ከኮንሶ -ያቤሎ- ዶሎ ኦዶ ድረስ የሚዘረጋ የአስፓልት መንገድ ግንባታ ለመጀመር የኮንትራት ሂደት መጠናቀቁን ይፋ አድርገዋል።

- በያቤሎ ከተማ የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባትም መሰል ሂደት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

- የአካባቢው ህዝብ ለግጭት ከሚዳረጉት ጉዳዮች ራሱን ጠብቆ የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
 
ገና በላል-ይበላ...

የላል-ይበላ ከተማ አስተዳደር የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ለማክበር ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶችን እየተቀበለች ነው፡፡ የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በቅዱስ ላልይበላ ከተማ በየዓመቱ በድምቀት ይከባራል ከሃገሪቱ ከአራቱም አቅጣጫዎች በርካታ የዕምነቱ ተከታዮች ወደ ከተማዋ ይገባሉ፡፡ ዘንድሮም በርከታ የእምነቱ ተከታዮች ወደ ከተማዋ በመግባት ላይ ናቸው፡፡ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት በማድረግ እየተቀበሉ መሆኑን የላል-ይበላ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ማንደፍሮ ታደሰ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሃይማኖት አባቶች ጥሪ ለኢትዮጵያውያን..

መላው ኢትዮጵያዊያን አመፅንና በቀልን በመተው ለአገራቸው ሰላምና መረጋጋት እንዲተጉ የሃይማኖት አባቶች ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የገና በዓል ሲከበር የተቸገሩትን በማሰብ ሊሆን ይገባል ሲሉም የእምነቱ አባቶች ምእመኑን መክረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ-ክርስቲያን ፕሬዚዳንት ቀሲስ ዮናስ ይገዙ፦

- ምእመኑ የገና በዓልን ሲያከብር ለአገሪቱ  ሰላም ፣ ለህዝቦች አብሮነት፣ፍቅርና መቻቻል በማሰብ መሆን አለበት ብለዋል። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ችግር ውስጥ እያስገባ ያለውን የሰው ህይወት መጥፋት፣ የእምነት ተቋማት መቃጠል፣ የዜጎች መፈናቀልና የተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ማቋረጥ የሚወገዝ ተግባር ሲሉ ገልፀዋል።

- ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የአገራችን ህዝቦች ከአመፅና ከበቀል እንዲወጡና መንግስትም ከህዝቡ ጋር በቅርበት በመስራት ኃላፊነቱን እንዲተገብር መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

- አገርን ለማስተዳደር ፉክክር የሚያደርጉ የፖለቲካ ፖርቲዎችም የአገራቸው ሰላም እንዳይደፈርስ አርቆ በማሰብ ለህዝቡ የሚያስተላልፉትን መልዕክት ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ በማከናወን የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡም አሳስበዋል።

- አገሪቱ ዘንድሮ ታካሄደዋለች ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ሆኖ የህዝብን ሰላም በማያደፈርስ መልኩ እንዲካሄድ የሁሉም ኃላፊነት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

(ENA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ሊቀ ጳጳስ ብጹ ካርዲናል ብርሃነእየሱስ ሱራፌል፦

- ሀገር ያለህዝብ ህዝብም ያለ ሀገር መኖር እንደማይችል አውቀን አገሪቷን ከጥፋትና ከክፋት መንገድ ልንጠብቃት ይገባል ብለዋል።

- በህዝቦች መካከል መተማመን እየጠፋ ዛሬ ወንድም በወንድሙ ላይ እጁን ሲዘነዝር እያየን ነው፤ ዜጎች ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬ በኃይማኖታቸው አልያም በብሄራቸው ምክንያት እየተፈናቀሉ ነው፤ ከዚህ ባሻገርም የቤተ እምነቶች መቃጣል አሳዛኝ ነው ብለዋል።

- ይህ ዓይነቱ አሳዛኝ ክስተት ይወገድ ዘንድ ሁሉም ከምንም በላይ ለሰላምና ይቅር ባይነት እንዲተጋ አሳስበዋል። የተቸገሩትን የሚያስብ ሰው ብጹእ ነው፤ በዓሉን ከአቅመ ደካሞች፣ አስታዋሽ ከሌላቸውና ከተቸገሩት ጋር በመሆን በጋራ ማክበር ተገቢ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብጹወቅዱስ አቡነ ማትያስ፦

- የክርስቶስ ልደት በዓል ምህረትንና ይቅርታን ለሁላችን ማድረጉን በማስተማር የሚከበር በዓል ነው ብለዋል። ሰላም ከሌለ ኃማኖታዊ ስርዓትንም ሆነ ሀይማኖታዊ ትምህርትን ማካሄድ አይቻለም ሲሉም ገልፀዋል።

- የሰላም መጥፋት ኑሮን በማናጋት ለዚህኛው ዓለም አጠቃላይ ደስታ እንቅፋት በመሆኑ ሁሉም ለሰላም ግንባታ የበኩሉን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።

- በተለይም ወጣቶች ‘እርስ በእርስ መፋቀርን እንጂ ተጣሉ’ የሚል ኃይማኖታዊ አስተምህሮ የሌለ መሆኑን መረዳት አለባችሁ፤ ለህገ ወጥ ድርጊት እንዳይተባበሩም ጥሪ አስተላልፈዋል። ሕዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና በመርዳት ሊያሳልፍ ይገባል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በወቅታዊ የክልሉ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፦

- በአርማጭሆ አካባቢ ሕጻናትን፣ ሾፌሮችን እና ግለሰቦችን በማገት ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ በመጠየቅ የአካባቢውን ሠላም በማደፍረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ወደ 50 የሚደርሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል ብለዋል።

- በሞጣ ከተማ በሃይማኖት ተቋማት እና በንግድ ተቋማት ከደረሰውን ጥቃት ጋር በተያያዘም 80 ያህል ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳዩ ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑን አቶ ተመስገን ጥሩነህ አስረድተዋል።

- በሞጣ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ከማዋል ጎን ለጎን ጉዳት የደረሰባቸውን መስጂዶች እና የንግድ ተቋማትን በመገንባት እና ተጎጂዎችን በማቋቋም ረገድ የክልሉ መንግሥት ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

https://telegra.ph/AAMA-01-06

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት...

የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲንና የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በሰሞነኛው የመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ ላይ ለመወያየት በመጭው ቅዳሜ ዕለት በሩሲያ እንደሚገናኙ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia