TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አዳማ

ዶ/ር ደሳለኝ ፍቃዱ በአዳማ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ናቸው። ከረቡዕ እስከ ዛሬ (ዓርብ ዕለት) ድረስ ወደ አዳማ ሆስፒታል ህይወታቸው አልፎ አስክሬናቸው የመጣ ሰዎች እና የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይቶ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር በጠቅላላው 16 መሆኑን ያስረዳሉ።

ዶ/ር ደሳለኝ እንደሚሉት ረቡዕ ዕለት የ3 ሰዎች አስክሬን ወደ ሆስፒታል መጥቷል። ከእነዚህም መካከል ሁለቱ አፍሪካ ዱቄት ፋብሪካ ዘበኛ ጥይት ተኩሶ የገደላቸው ሰዎች ይገኙበታል።

የአዳማ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ራውዳ ሁሴን የዱቄት ፋብሪካው ጥበቃ ጥይት ተኩሶ ሁለት ሰዎችን መግደሉን እና በዚህ የተበሳጩ ሰልፈኞ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ 15 መኪኖች ማቃጠላቸውን ረቡዕ ዕለት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

ዶ/ር ደሳለኝ ትናንት ሐሙስ ሆስፒታሉ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ተጎጂዎችን ያስተናገደበት ቀን እንደሆነ ያስረዳሉ። "ትናንት ጉዳት ደርሶባቸው የመጡት ሰዎች ቁጥር ከ100 በላይ ይሆናል" ያሉ ሲሆን የጉዳቱ መጠን ከከባድ እስከ ቀላል የሚባል እንደሆነ ያሰረዳሉ።

"በዱላ የተደበደቡ፣ በስለት ጭንቅላታቸው ላይ የተመቱ፣ በጥይት የተመቱ ሰዎችም አሉበት" የሚሉት ዶ/ር ደሳለኝ፤ ትናንት ብቻ ህይወታቸው አልፎ አስክሬናቸው የመጣ እና በህክምና ላይ እያሉ ህይወታቸው የያለፈ ሰዎች ቁጥር 12 ነው ይላሉ።

ረቡዕ ዕለት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ከፍተኛ የህክምና ክትትል ክፍል (አይሲዩ) ውስጥ የነበረ ወጣት ዛሬ ጠዋት ህይወቱ አልፏል ብለዋል።

"አሁንም በሆስፒታሉ በአደጋኛ የጤና ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች አሉ። የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል። አይኑ የጠፋ፣ አጥንቱ የተሰበረ ብዙ ነው" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-25-2

@tikvahethiopia
#ADAMA

የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ (ቪኦኤ) የአፋን ኦሮሞ ክፍል ሪፖርተር የሆነው ጋዜጠኛ ሙክታር ጀማል በአዳማ ከተማ 'ጀማል መጋዘን' ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በመንገድ ላይ ቃለ-መጠይቅ እያደረገ ሳለ ድብደባ እና ዘረፋ ተፈጽሞበታል። ጭንቅላቱ እና ወገቡ ላይ ጉዳት ያጋጠመው ጋዜጠኛ ሙክታር ሆስፒታል ተኝቶ የህክምና አገልግሎት እየተከታተለ ነው። ሙክታር ቃለ-መጠይቅ እያደረገ ሳለ የተደራጁ ወጣቶች መጥተው ድብደባ እንደፈጸሙበት ያስረዳ ሲሆን፤ "ቦርሳዬን ሲበረብሩ የኢቮኤ መታወቂያ ካርድ ካዩ በኋላ ትተውኝ ሄዱ" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።

Via ቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኮፈሌ

አብነት አክሊሉ በምዕራብ አርሲ ዞን ኮፈሌ ከተማ ነዋሪ የነበሩ 2 ዘመዶቹ እና አንድ በዘመዶቹ ቤት ስላደገው ወጣት አሟሟት ለቢቢሲ ተናግሯል። አቶ ታምራት ጸጋዬ የአብነት አክሊሉ አጎት (የእናቱ ወንድም) ናቸው።

ረቡዕ ዕለት በተፈጠረው ግርግር አቶ ታምራት ጸጋዬ፣ ልጃቸው አቶ ሄኖክ ታምራት ጸጋዬ እና በአቶ ታምራት ቤት ሱቅ ውስጥ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ ሌላ ወጣት ልጅ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ መገደላቸውን አብነት አክሊሉ ይናገራል። "ተሰብስበው ወደ አጎቴ ቤት መጡ። ከዚያ በመጀመሪያ አጎቴን (አቶ ታምራት ጸጋዬ) ገደሉት። ከዚያ በተመሳሳይ ሁኔታ ልጁን ገደሉት። ከዚያ ቤት ውስጥ ያደገ ሱቅ ውስጥ ይሰራ የነበረ ልጅ ገደሉ" ይላል። አብነት የሟች አስክሬን ላይም አስነዋሪ ድርጊት መፈጸሙን ለቢቢሲ ተናግሯል።

የአቶ ታምራት ልጅ፤ ሄኖክ ታምራት ጸጋዬ በቅርቡ ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዲግሪ በምጣኔ ሃብት ዘረፍ እንደተመረቀ የሚናገረው አብነት፤ አቶ ታምራት በኮፈሌ ከተማ ወፍጮ ቤት፣ ሆቴል እና መኪኖች እንዳሏቸው ይናገራል። የቤተሰብ አባላቱን ከተገደሉ በኋላ የአቶ ታምራት መኖሪያ ቤት አና መኪና እንደተቃጠለም አብነት ጨምሮ ይናገራል።

የአቶ ታምራት እና የልጃቸው ትውልድ እና እድገት እዛው ኮፈሌ መሆኑን የሚናገረው አብነት "ተወልደው ባደጉበት ኮፈሌ እንኳ መቅበር አልቻልንም። በስንት መከራ ዛሬ በናዝሬት ከተማ 10 ሰዓት ላይ ቀብራቸው ተፈጽሟል" በማለት አብነት ያስረዳል።

Via BBC AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አምቦ | ረቡዕ እና ሐሙስ ዝግ ሆነው የነበሩት መንገዶች ከዛሬ ጠዋት (ዓርብ) ጀምሮ ክፍት ተደርገዋል። ባለፉት ሁለት ቀናት በነበሩት ግጭቶ 5 ሰዎች ተገደሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል አንድ የፖሊስ አባል ይገኝበታል። ይህ የፖሊስ አባል የተገደለው ሐሙስ ዕለት ሲሆን ረቡዕ ዕለት በነበረው ግጭት 'ሰው ገድለሃል' ተብሎ በበቀል እርምጃ እንደተገለ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

(ቢቢሲ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዶዶላ

በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ ረቡዕና ሐሙስ በነበሩ ግጭቶች በጠቅላላው 6 ሰዎች መገደላቸውም ታውቋል። ሐሙስ በነበረ ግጭት 4 ሰዎች ሞተው ወደ ዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ተናግረዋል። ረቡዕ ደግሞ ሁለት ሰዎች ተገድለው ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የቢቢሲ ዜናን ያዳምጡ!
#ETHIOPIA

ባለፉት ሁለት ቀናት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በታዩባቸው አንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች አንጻራዊ ሰላም መመለሱ ኾኖም ነዋሪዎች ሥጋት ውስጥ መኾናቸውን ገለጡ።

ተቃውሞው ወደ ሃይማኖታዊ ግጭት የመቀየር አዝማሚያ መያዙ በታየባቸው የኦሮሚያ ከተሞች ዛሬም ውጥረት ሰፍኖ እንዳለ የዐይን እማኞች ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል። ድሬዳዋ፣ አዳማ እና ባሌ ሮቤ ከተሞች ውስጥ ውጥረቱ አሁንም ድረስ እንዳለ ነው የዐይን እማኞቹ የተናገሩት።

በአዳማ ከተማ የነበረው ውጥረት ረገብ ብሎ በየቀበሌው ውይይት መጀመሩን የነገሩን አንድ የከተማው ነዋሪ እንዳሉት ከሆነ መንግሥት እና የሃይማኖት ተቋማት ከሕዝቡ ጋር ውይይት ማድረግ ጀምረዋል፤ ፍራቻው ግን አኹንም አለ።
«ሕዝቡ ውስጥ ፍራቻ አለ? አዎ አለ፤ ነገር ግር እርስ በራስ የሕዝቦች ለሕዝቦች ግንኙነትን መንግሥትም እየሠራ ይመስላል። የሃይማኖት ተቋማትም በጣም ተረባርበው [እየሠሩ ነው።] ጠዋት እኔ ዐይቼዋለሁ። ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በርካታ ሰዉ ይጸልያል። እና ደስ የሚል ነገር ነው ያየኹት፤ እና ያ ነው አሁን ያለው።»

በድሬዳዋ ከተማ የተቃውሞ ሰልፉን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ግጭት ረገብ ማለቱ ተገልጧል። ኾኖም ዛሬ ከነጋ አንድ ባጃጅ መቃጠሉን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የከተማው ነዋሪ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የከተማይቱ ነዋሪዎች ከአንዱ ሰፈር ወደ ሌላኛው ሰፈር ለመሄድ እንደሚቸገሩም እኚሁ ነዋሪ አስረድተዋል። ስለኹኔታው ከአዳማ፣ ከድሬዳዋ እና ከባሌ ሮቤ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከፖሊስ አካላት ለማጣራት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ38 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት በበጎፈቃድ መሰብሰብ ተችሏል!

በትምህርት ሚኒስቴር አነሳሽነት የተጀመረው “የእኛ ለእኛ” የበጎ ፈቃደኞች መርኃግብር ላይ ላለፉት 3 ወራት ለተሳተፉ በጎፈቃደኛ ወጣቶች ዛሬ በትምህርት ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ በተገኙበት የሰርተፍኬት አሰጣጥ መርኃግር ተከናውኗል፡፡ በአጠቃላይ የበጎ ፈቃድ ዘመቻው ከ350 በላይ በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉ ሲሆን ዛሬ በአዲስ አበባ ለሚገኙት በጎፈቃደኞች ይህ መርኃግብር ተዘጋጅቷል፡፡

በሦስት ወር የበጎ ፈቃድ ስራ በትምህርት ቁሳቁስ ከ3 ሚሊየን ዘጠኝ መቶ ሺ በላይ የተሰበሰበ ሲሆን በአልባሳትና በሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘውን ድጋፍ ጨምሮ 30 ሚሊየን የሚቆጠር ድጋፍ ማሰባሰብ ተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ ግን በዚህ መርኃግብር 38 ሚሊየን ሀብት መሰብሰብ ተችሏል፡፡ በዚህም በበርካታ ቦታዎች የሚገኙ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ጉዳት ትምህርታቸውን መከታተል ላልቻሉና ችግር ለደረሰባቸው አከባቢዎች ድጋፍ ማድረግ ተችሏል፡፡ በቀጣይ የትምህርት ሚኒስቴር በእኛ ለእኛ የበጎፈቃድ አገልግሎት ስር “የተማረ ያስተምር” የተሰኘ መርኃግብር የሚጀመር ሲሆን በዚህም በርካታ በጎፈቃደኞች ይሳተፉበታል ተብሎ ይታመናል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ "የእንኳን ደስ አላችሁ!" መልዕክት ለማስተላለፍ የማይመች ቢሆንም ወድ ቤተሰቦቻችን ለሰራችሁት በጎ ስራ ከትምህርት ሚኒስቴር ሰርተፍኬት ተበርክቶላችኀል!

በኤ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ስር ለተደራጀው "እኛ ለእኛ" የኢትዮጵያ በጎፈቃደኞች መርኃግብር ላይ ተሳታፊ በመሆን በልዩ ልዩ ምክንያት ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ትምህርታቸውን በአግባቡ ላልተከታተሉ እና ላቋረጡ ተማሪዎቻችንን ትምህርት ማስቀጠያ የሚሆኑ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ከህብረተሰቡ በማሰባሰብ፣ በማምረት፣ በመለገስ ሂደት TIKVAH-ETH የቤተሰቡን አባላት በማስተባበርና መረጃዎችን በመስጠት ላደረገው አስተዋጽኦ ይህ የምስክር ወረቀት ተበርክቶልናል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዘላቂ ሰላምን መገንባት!" በሚል ርዕስ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከኢንሼቲቭ አፍሪካ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው መርኃግብር ነገ በUNECA መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በኮንፍረንሱ ላይ የሁሉም የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች፣ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችና የሰላም ፎረም አባላት ይገኙበታል፡፡ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦችም ባለፈው ዓመት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ባካሄዱት "የጥላቻ ንግግር እናቁም!" ዘመቻ ምክንያት በዚህ ስብሰባ ላይ የሚገኙ ይሆናል፡፡

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia @tsegabwolde
#EliasMeseret #TikvahFamily

የሀሰተኛ ዜናዎች መድሃኒት "ኤልያስ"!

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰባችን አባል የሆነው ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ነገ ከምሽቱ 12:00-1:00 ለናተ ለውድ ቤተሰቦቻችን የተመረጡ መረጃዎችን ያደርሳችኃል።

STOP FAKE NEWS!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሟቾች ቁጥር 67 ደርሷል!

#Reuters

ሮይተርስ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነገሩኝ ብሎ ባወጣው ዘገባ መሰረት ባለፉት ሁለት ቀናት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች በነበረው ተቃውሞ የ67 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን ዘግቧል። ከሟቾቹ ውስጥ 5ቱ የፖሊስ አባላት ናቸው። 13 ሰዎች ደግሞ በጥይት ተመተው የተገደሉ ሲሆን የተቀሩት በድንጋይ ተደብድበው እንደተገደሉ ነው የተገለፀው።

https://telegra.ph/ETH-10-25-3

http://www.dailystar.com.lb/News/World/2019/Oct-25/494338-67-people-killed-in-protests-in-ethiopias-oromiya-region-police.ashx#.XbNI_WnU9lV.facebook

Via #DailyStar
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የድፍድፍ ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ግንባታም ከኦጋዴን እስከ ጅቡቲ ድረስ በዚህ አመት ለማስጀመር ድርድር እየተካሄደ መሆኑን የማእድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኳንግ ቱትላን እንደተናገሩት፥ ስለነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ከጅቡቱ ጋር ያለው የስምምነት ፊርማ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ለመፅደቅ እየተጠባበቀ ነው። ስምምነቶች ሲጠናቀቁም የማስተላለፊያ መስመር ግንባታ እንደሚጀመርም አስታውቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ተስፋዬ መንገሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

የቀድሞ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ጸሃፊ የነበሩትአቶ ተስፋዬ መንገሻ አበጋዝ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ የፍተኛ ትምህርትታቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያጠናቀቁት አቶ ተስፋዬ መንገሻ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በኃላፊነት አገልግለዋል።

ከ1991 እስከ 1996 ዓመተ ምህረት በብሔራዊ ምረጫ ቦርድ ምክትል ጸሃፊነትን ጨምሮ በተለያዩ የስራ ሃላፊነቶች፣ ከ1998 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለስድስት ዓመታት የምርጫ ቦርድ ዋና ጸሃፊ ሆነው አገልግለዋል። አቶ ተስፋዬ በአሜሪካ ሎሳንጀለስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቆንስላ ጽህፈትም አገልግለዋል፡፡

አቶ ተስፋዬ መንገሻ የሁለት ወንዶችና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበሩ፡፡ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በውጭ እና ሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓመተ ምህረት በ50 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

የቀብር ስነ ስርዓታቸው ዛሬ ጥቅምት 15 ቀን 2012 ዓመተ ምህረት በመካኒሳ አቦ ቤተክርስቲያን ከቀኑ በስምንት ሰዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ይፈጸማል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA | አዳማ ከተማ ውስጥ የተፈጠረውን ሁከትና ግጭት ሲዘግብ የነበረው የቪኦኤ ሪፖርተር ሙክታር ጀማል ጥቃት እንደተፈፀመበት ይታወቃል፡፡ ሙክታር ጀማል በራሱ ላይ የመፈንከት ጉዳት እንደደረሰበት፣ ከንፈሩ መሰንጠቁና በጀርባውና በእግሮቹም ላይ በድንጋይ፣ በጡጫና በሌላም ማጥቂያ መደብደቡን ተናግሯል፡፡ ሙክታር ጀማል ህክምና እየተደረገለት ይገኛል፡፡ በሌላም በኩል ግን የዘጠኝ ሰው ሕይወት ከጠፋበት ሁከት በኋላ የአዳማ ፀጥታ እየተሻሻለ መሆኑን የከተማይቱ አስተዳደር ለቪኦኤ አስታውቋል፡፡

Via VOA AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#ADAMA

የVOA (ቪኦኤው) ጋዜጠኛ ሙክታር ጀማል በአዳማ ከተማ ስለደረሰበት የደቦ ጥቃት ይናገራል፤ ያዳምጡ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HARAR

በሐረር ከተማና አካባቢው ሰላምና መረጋጋት በመስፈን ላይ ነው። ረቡዕና ሀሙስ የነበረው ውጥረት ጋብ ብሎ ሕይወት መደበኛ መሥመሯን መያዝ ጀምራለች። በከተማዋ በሁለቱ ቀናት  በነበረው ግጭት በሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። የከተማዋ የታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት ጀምሯል። እንዲሁም ከሐረር – ጅግጅጋ የትራንስፖርት እንቅሰቃሴ መጀመሩንም ተጀምሯል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA

68 ተጠርጣሪች በቁጥጥር ስር ውለዋል!

በአዳማ ከተማ በተፈጠረው ግጭት እጃቸው አለባቸው የተባሉ 68 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ አሰግድ ጌታቸው ለOBN ገልጸዋል፡፡ ከንቲባው እንዳሉት በከተማው የተካሄደውን ሰልፍ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ወደ ዘርና ሃይማኖት ግጭት የቀየሩ የተባሉ 68 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል፡፡

via OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዳማ ከተማ ፖሊስ ከተማይቱ ወደ መረጋጋት መመለሷን ገልጿል!

በአዳማ ከተማ በያዝነው ሳምንት ረቡዕና ሀሙስ ዕለት ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር በመቃለሉ አሁን ከተማይቱ ወደ መረጋጋትና ሰላም መመለሷን የአዳማ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።

የከተማው ፖሊስ መምሪያ የሰላም ማረጋገጥ የስራ ሂደት መሪ ምክትል ኮማንደር አለምሸት ኃይሉ እንዳሉት ባለፉት ሁለት ቀናት በከተማዋ መንገድ እንዘጋለን አትዘጉም በሚል በሁለት ቡድኖች መካከል በተነሳው ጸብ ግጭት ተፈጥሮ ነበር፤ በዚህም አንድ ሴትን ጨምሮ የ13 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስታውቀዋል። (ቢቢሲ የሆስፒታል ምንጮችን ጠቅሶ ትላንት እንደዘገበው የሟቾች ቁጥር 16 ይደርሳል)

ከ50 በላይ ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በአዳማ ሪፈራል ሆስፒታልና ሜዲካል ኮሌጅ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ መደረጉን ገልፀዋል። እንዲሁም በተለያዩ ንብረቶች ላይ ጉዳት ደርሷል። ጉዳት ከደረሰባቸው ንብረቶች መካከል በከተማዋ አፍሪካ ዱቄት ፋብርካ ንብረት የሆኑ 13 ተሽከርካሪዎች ፣ አንድ መኖሪያ ቤት እና ሰባት ባጃጆች ይገኙበታል።

https://telegra.ph/ETH-10-26

Via ENA

@tikvahethiopia
የአሜሪካን ተራድዖ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር (#USAID) Mr. Sean Jones ደም ለግሠዋል። #ETHIOPIA #OCT22

እርሶስ?
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Blood donation sites: #AddisAbaba

◽️Stadium Red Cross
◽️MoH office- "Goma Kuteba”
◽️Mexico Square
◽️Megenagna Square
◽️Tor-Hayloch Square + 38 blood bank branches in the regional cities all over 🇪🇹

Come let’s #DonateBlood together!

Via Dr. Amir Aman
@tsegabwolde @tikvahethiopia