የአዳማ ከተማ ፖሊስ ከተማይቱ ወደ መረጋጋት መመለሷን ገልጿል!

በአዳማ ከተማ በያዝነው ሳምንት ረቡዕና ሀሙስ ዕለት ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር በመቃለሉ አሁን ከተማይቱ ወደ መረጋጋትና ሰላም መመለሷን የአዳማ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።

የከተማው ፖሊስ መምሪያ የሰላም ማረጋገጥ የስራ ሂደት መሪ ምክትል ኮማንደር አለምሸት ኃይሉ እንዳሉት ባለፉት ሁለት ቀናት በከተማዋ መንገድ እንዘጋለን አትዘጉም በሚል በሁለት ቡድኖች መካከል በተነሳው ጸብ ግጭት ተፈጥሮ ነበር፤ በዚህም አንድ ሴትን ጨምሮ የ13 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስታውቀዋል። (ቢቢሲ የሆስፒታል ምንጮችን ጠቅሶ ትላንት እንደዘገበው የሟቾች ቁጥር 16 ይደርሳል)

ከ50 በላይ ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በአዳማ ሪፈራል ሆስፒታልና ሜዲካል ኮሌጅ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ መደረጉን ገልፀዋል። እንዲሁም በተለያዩ ንብረቶች ላይ ጉዳት ደርሷል። ጉዳት ከደረሰባቸው ንብረቶች መካከል በከተማዋ አፍሪካ ዱቄት ፋብርካ ንብረት የሆኑ 13 ተሽከርካሪዎች ፣ አንድ መኖሪያ ቤት እና ሰባት ባጃጆች ይገኙበታል።

https://telegra.ph/ETH-10-26

Via ENA

@tikvahethiopia