TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኮፈሌ

አብነት አክሊሉ በምዕራብ አርሲ ዞን ኮፈሌ ከተማ ነዋሪ የነበሩ 2 ዘመዶቹ እና አንድ በዘመዶቹ ቤት ስላደገው ወጣት አሟሟት ለቢቢሲ ተናግሯል። አቶ ታምራት ጸጋዬ የአብነት አክሊሉ አጎት (የእናቱ ወንድም) ናቸው።

ረቡዕ ዕለት በተፈጠረው ግርግር አቶ ታምራት ጸጋዬ፣ ልጃቸው አቶ ሄኖክ ታምራት ጸጋዬ እና በአቶ ታምራት ቤት ሱቅ ውስጥ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ ሌላ ወጣት ልጅ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ መገደላቸውን አብነት አክሊሉ ይናገራል። "ተሰብስበው ወደ አጎቴ ቤት መጡ። ከዚያ በመጀመሪያ አጎቴን (አቶ ታምራት ጸጋዬ) ገደሉት። ከዚያ በተመሳሳይ ሁኔታ ልጁን ገደሉት። ከዚያ ቤት ውስጥ ያደገ ሱቅ ውስጥ ይሰራ የነበረ ልጅ ገደሉ" ይላል። አብነት የሟች አስክሬን ላይም አስነዋሪ ድርጊት መፈጸሙን ለቢቢሲ ተናግሯል።

የአቶ ታምራት ልጅ፤ ሄኖክ ታምራት ጸጋዬ በቅርቡ ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዲግሪ በምጣኔ ሃብት ዘረፍ እንደተመረቀ የሚናገረው አብነት፤ አቶ ታምራት በኮፈሌ ከተማ ወፍጮ ቤት፣ ሆቴል እና መኪኖች እንዳሏቸው ይናገራል። የቤተሰብ አባላቱን ከተገደሉ በኋላ የአቶ ታምራት መኖሪያ ቤት አና መኪና እንደተቃጠለም አብነት ጨምሮ ይናገራል።

የአቶ ታምራት እና የልጃቸው ትውልድ እና እድገት እዛው ኮፈሌ መሆኑን የሚናገረው አብነት "ተወልደው ባደጉበት ኮፈሌ እንኳ መቅበር አልቻልንም። በስንት መከራ ዛሬ በናዝሬት ከተማ 10 ሰዓት ላይ ቀብራቸው ተፈጽሟል" በማለት አብነት ያስረዳል።

Via BBC AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia