TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbeba

የከባድ ጭነት ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት አጀንሲ አስታውቋል፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጅሬኛ ሂርጳ ትናንት በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የከተማዋን ትራፊክ እንቅስቃሴ ለማሳለጥና አሁን ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ
ከግምት ውስጥ በማስገባት በከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች የእንቅስቃሴ ገደብ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡ በተሻሻለው መመሪያ መሠረትም፤ ማንኛውም የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ ከጠዋቱ 12፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት እና ከቀኑ ከ10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ካለው ጊዜ ውጪ መንቀሳቀስ የሚፈቅድ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ በዚህም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በከተማዋ ውስጥ መዘዋወርና ማንኛውንምአገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጎዳና ላይ ልብስ ነጋዴው የ10,000,000 ብር ዕድለኛ ሆነ። የድሬዳዋ ነዋሪው የ27 ዓመቱ ወጣት አንዳምላክ ባዴ ጳጉሜ 6 ቀን 2011 ዓ/ም በወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ 1ኛ ዕጣ 10,000,000 ብር አሸናፊ ሆኗል።

ምንጭ፦ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ2019 #NobelPeacePrize ከ25 ደቂቃ በኃላ ይፋ ይደረጋል። ጥሩ የኢንተርኔት ግንኙነት ካላችሁ ከታች ባለው የዩትዩብ ሊንክ ቀጥታ መከታተል እንደምትችሉ ልንጠቁማችሁ እንወዳለን! https://www.youtube.com/watch?v=7Vhj3N9HHj8

•የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ
•የኒውዚላንድ ጠ/ሚ ጃሲንዳ አርደርን
•የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትረምፕ ሽልማቱን ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብለው ከተገመቱ ሰዎች መካከል ይገኙበታል።

ነገር ግን...የአየር ለውጥ አክቲቪስቷ ስዊድናዊቷ የ16 ዓመት ታዳጊ ግሬታ ተንበርግ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷታል። የዘንድሮ አሸናፊ ማን እንደሆነ ከ25 ደቂቃ በኃላ ይታወቃል!!

#ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
5 ደቂቃ የ2019 Nobel Peace Prize!
BREAKING NEWS:

The Norwegian Nobel Committee has decided to award the Nobel Peace Prize for 2019 to Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed Ali.#NobelPrize #NobelPeacePrize

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የ2019 የኖቬል የሰላም ሽልማትን አሸነፉ!

የ2019ኙን የሰላም ኖቤል ሽልማት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሸነፉ፡፡ በአውሮፓዊኑ የዘመን ቀመር 1901 የተጀመረው የኖቤል ሽልማት በተለያዩ ዘርፎች ግለሰብና ድርቶችን ሲሸልም ኖኗል፡፡

በሰላም ዘርፍም የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማትን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በዋናነትም ለኢትዮ-ኤርትራ እርቅ ላደረጉት አስተዋፅኦ በሚል እንዳሸነፉ ሸላሚው ድርጅት ይፋ አድርጓል፡፡

ከጠ/ሚንስትሩ ጋር የማሸነፍ ግምትን የ16 ዓመቷ ስዊድናዊት የአየር ንብረት ተማጋች ግሪታ ቱምበርግ፣ ብራዚላዊው የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያ ራኦኒ ሜቱክተይር እና ‘’ሪፖርተርስ ዊዝአውት ቦርደርስ’’ የተባለው የመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ተማጋች ድርጅት የመጨረሻ እጩ ስለመሆናቸው ዓለም ዐቀፍ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች መረጃ አግኝተናል በማለት ሲዘግቡ ሰንብተውም ነበር፡፡ በኖርዊጂያን የኖቤል ኮሚቴ የሚሰጠው የኖቤል የሰላም ሽልማት ከሚያሰጠው ከፍ ያለ እውቅና ባሻገር 743 ሺሕ ፓወንድ እንደሚያሸልምም ይገለፃል፡፡

Via Ahadu TV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ደስ አሎት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር!

ቪድዮ፦ ስንታየሁ/TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደስ አላችሁ!! እንኳን ደስ አለን!!

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የ2019 የኖቬል የሰላም ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡ በTIKVAH-ETH ስም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን ለማለት እንወዳለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#NewsAlert

ቢሾፍቱ ከተማ /ኡኬ ደንካካ የሚባል አካባቢ አነስተኛ የጦር አውሮፕላን ተከስክሷል። አውሮፕላኑ የእህል ማሳ ላይ ነው የወደቀው። በአካባቢው ላይ አምቡላስ እንደተመለከቱም የቤተሰባችን አባላት ገልፀዋል።

Via ሮብኤል/TIKVAH-ETH/

ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሰን እናቀርባለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቢሾፍቱ -- ኡኬ ደንካካ!!

የአደጋው ምንክንያት ምን እንደሆነና ስለደረሰው ጉዳት ተጨማሪ መረጃዎችን እንዳገኘን እናጋራለን!

PHOTO: kira Dibenedetto/TIKVAH-ETH/
@tsevabwolde @tikvahethiopia
#Attention

ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ ልዩ ቦታው ጎሃ ፅዮን አካባቢ መንገድ ተዘግቷል። ለመንገዱ መዘጋት ምክንያቱ ምን እንደሆነ አላወቅንም የሚሉት የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ወደመጣንበት እንድንመለስ ተነግሮናል፤ አንዳንድ መኪኖችም እየተመለሱ ይገኛሉ ብለዋል። በርካታ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎች በጉዞ ላይ ስለሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ እንዲፈልጉ ጥሪ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ጥሪ አቅርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#PMOEthiopia

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያገኙት የኖቤል የሰላም ሽልማት ለሰላም የተሰጠ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ። ፅህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ ይህ ለሰላም የተሰጠ ሽልማት በመሆኑም መላው ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለሰላም እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል።

የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማትም የኢትዮጵያውያን የጋራ ድል መሆኑንም አስታውቋል። ኢትዮጵያን አዲሲቷ የተስፋ አድማስ በማድረግ የበለፀገች እንድትሆን የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የማንቂያ ጥሪ መሆኑንም ነው ያመለከተው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ተሸላሚ በመሆን በዘርፉ 100ኛው ተሸላሚ ሆነዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸውን ተከትሎ ባስተላለፉት የደስታ መግለጫ መልዕክት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አመራር ለአፍሪካና ለሌች አገራት ምሳሌ ነው ብለዋል፡፡ ዋና ጸሓፊው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ራዕይ በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ታሪካዊ መቀራረብን ፈጥሯል ብለዋል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
WORLD EXCLUSIVE: Listen to the call between Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed Ali and Olav Njølstad, Secretary of the Norwegian Nobel Committee, recorded shortly after the announcement of the 2019 Nobel Peace Prize.

Via Nobel Prize
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ለጠ/ሚ አብይ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላፉ!

ግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ በመሆናቸው የአንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላለፉ፡፡ ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ወንድም የኢትዮጵያ ህዝቦች የ2019 የኖቤል ሽልማት ዶክተር አብይ አህመድ በማሸናፈቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia