TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ እና ሱዳን የደህንነት ተቋማት በጋራ ለመስራት ተስማሙ። ስምምነቱን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጀኔራል ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤል ከሱዳኑ ኢንተለጀንስ ሰርቪስ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አቡበክር ዳምብ ላም ጋር ተፈራርመውታል። በስምምነቱ መሰረትም ሽብርተኝነት፣ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ፣ የገንዘብና የሰዎች ዝውውር እንዲሁም በሃገራቱ የድንበር ወሰን አካባቢዎች የሚፈጸሙ የተደራጁ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል ውይይቶችን በማድረግ መረጃ የሚለዋወጡ ይሆናል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ ክልል ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት!
.
.
ኮማንድ ፖስቱ በክልሉ አንዳንድ ዞኖች እና ወረዳዎች በህግ የማይታወቁ አርማዎችን፣ ሰንደቅ ዓላማዎችን፣ ባነሮችን እና የአድራሻ ማስታወቂያዎችን (ታፒላዎችን) የሰቀሉ አካላት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሁለት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ እንዲያነሱ ሲል አሳስቧል።

በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የክልሉን #ህጋዊ ሰንደቅ ዓላማ በማውረድና የመንግስት ተቋማት የአድራሻ ማስታወቂያዎችን በመንቀል በምትኩ እውቅና የሌላቸውን የመትከል ሙከራዎች መከናወናቸውን ኮማንድ ፖስቱ በመግለጫው አስታውቋል።

በመሆኑም «ህገ ወጥ»ያላቸውን አርማዎችን፣ ሰንደቅ ዓላማዎችን እና የአድራሻ ማስታወቂያዎችን በተሰጠው የሁለት ቀናት የጊዜ ገደብ ውስጥ በማንሳት ህጋዊ» የሆኑትን በአስቸኳይ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ሲል ኮማንድ ፖስቱ አሳስቧል።

በተጨማሪም መግለጫው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በክልሉ ሁሉም ዞኖች ፣ ወረዳዎች ፣ በከተሞች አና በቀበሌዎች የመስተዳድር ክልል ውስጥ የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የግል ተቋማት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች #ትክክለኛ የአድራሻ ማስታወቂያዎችን (ታፒላዎችን) እና ህጋዊ የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ ብቻ እንዲጠቀሙ አመልክቷል።

እንዲሁም በተለያዩ የህትመት ውጤቶች የተዘጋጁና በህግ የማይታወቁ አርማዎችንና ሰንደቅ ዓላማዎችን መልበስ ፣ ይዞ መዘዋወር ፣ መሰቀልም ሆነ መለጠፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው ሲል አስታውቋል። በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ መመሪያውን ተፈፃሚ በማያደርጉ ግለሰቦች፣ ተቋማት እና ድርጅቶች ላይ በየደረጃው በተዋቀሩ የኮማንድ ፖስት አማካኝነት #ህጋዊ_እርምጃ ይወሰዳል ሲል አስጠንቅቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአ/አ የሁለት ሰው ህይወት አለፈ!

አዲስ አበባ በፌደራል ፖሊስ አባላት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ። የፌደራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጀይላን አብዲ እንደነገሩን ከሆነ ዛሬ ረፋድ ላይ በፌደራል ፖሊስ ከሚጠበቁ ተቋማት መካከል አንዱ በሆነው የፌደራል ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ግቢ ውስጥ በተፈጠረ አለመግባባት የ2 ሰው ህይወት አልፏል።

ክስተቱ የተፈጠረው ኤጀንሲውን ከሚጠብቁ የፖሊስ አባላት መካከል አንዱ ለተመሳሳይ #ጥበቃ ስራ ወደ ሌላ ተቋም መቀየሩ የተነገረው የፌደራል ፖሊስ አባል እና በሃላፊው የተሰጠውን ትዕዛዝ ባለመቀበል ምክንያት የተጀመረ ውይይት ወደ አለመግባባት አምርቶ ፖሊሱ የስራ ሃላፊውንና በስራ ላይ በነበረ አንድ አባል ላይ ግድያ መፈጸሙ ተገልጿል። ድርጊቱን የፈጸመው የፌደራል ፖሊስ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን አቶ ጄይላን ተናግረዋል።

Via #ኢትዮኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በCSA የተፈፀመውን ግድያን በተመለከተ፦

ግድያውን የፈጸመው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል። መነሻው የግለሰብ ጸብ ነው፤ ሌላ ምክንያት እየተሰጠው #በማህበራዊ_ሚዲያዎች የሚተላለፉት መረጃዎች ሀሰት ናቸው፤ ከግለሰቦች ግጭት ያለፈ ሌላ ነገር የለም ሲሉ የፌደራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጄላን አብዲ ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕለቱ መልዕክት፦

ከጭፍን ጥላቻ መላቀቅ ይቻላል!

አብዛኞቹ ሰዎች ጭፍን ጥላቻን በመሠረተ ሐሳብ ደረጃ የሚያወግዙ ቢሆኑም ከጭፍን ጥላቻ መዳፍ የሚላቀቁ ግን ጥቂቶች ናቸው። እንዲያውም ሥር የሰደደ ጭፍን ጥላቻ ያላቸው ብዙ ሰዎች ጥላቻ እንደሌላቸው ሊናገሩ ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ ሰዎች ጭፍን ጥላቻቸውን ይፋ እስካላወጡ ድረስ ምንም ጉዳት የለውም ይላሉ።

ይሁን እንጂ ጭፍን ጥላቻ ሰዎችን የሚጎዳና የሚከፋፍል መጥፎ ነገር ነው። ጭፍን ጥላቻ የድንቁርና ልጅ ነው ቢባል የልጅ ልጁ ደግሞ ጠላትነት ነው። ቻርልስ ካለብ ኮልተን የተባሉት ደራሲ (1780-1832) “አንዳንድ ሰዎችን ስለማናውቃቸው #እንጠላቸዋለን። ስለምንጠላቸውም #ልናውቃቸው አንችልም” ብለዋል። ጭፍን ጥላቻን ሰዎች መማር እንደሚችሉ ሁሉ ማስወገድም ይችላሉ።

Via #JW

#ፍቅር #ሰላም #አንድነት #ተስፋ #ኢትዮጵያ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Video Editing Training #Register_Today

Call 0118633128
#ሱዳን

የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት እና በነጻነት እና ለውጥ ኃይሎች መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር የሽግግር ሕገመንግስት እና የፓለቲካ ስምምነት በመፈራረም መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ እና አፍሪካ ሕብረት ሁለቱን ወገኖች በማደራደር ላበረከቱት አስተዋጽኦና ለተጫወቱት ቁልፍ ሚና የምስጋና ፕሮግራም በማዘጋጀት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና ዳይሬክተር ጄኔራሎች በተገኙበት ሽልማት አበርክቷል። ሽልማቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሱዳን ልዩ ልዑክ አምባሳደር መሃሙድ ድሪር ፣ በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ እና የአፍሪካ ሕብረት ልዩ ልዑክ መሃመድ ሃሳን ላባት የተበረከተ ሲሆን፣ የወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት የፓለቲካ ጉዳዮች ተጠሪ ጄኔራል ሸምሰዲን አል ካባሺ በተገኙበት የሱዳን ተጠባባቂ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ኦማር ዳሃብ ሽልማቱን አበርክተውላቸዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ ሞተረኞች፦

መንግስት ስራ አልባ አደረገን፤ እስከዛሬ ስለጉዳዩ ምንም ነገር እየተባለ አይደለም በዚህም በከፍተኛ ሁኔታ ተቸግረናል ሲሉ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ሞተረኞች ቅሬታቸውን አሰምተዎል። ይህ በጊዜያችን እና በህይወታችን ላይ መቀለድ ነው የሚሉት ወጣቶቹ አስፈላጊው ሁሉ ስራ ተጠናቃቆ በህግ አግባብ ወደስራቸው መመለስ እንደሚፋጉ ተናገርዋል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሚሰጥ አካል ካለ @tsegabwolde
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#በአዲስ_አበባ ከተማ ከሰኔ 30 በኋላ በከተማዋ እንዳይንቀሳቀሱ የታገዱ ሞተር ሳይክሎች ኮድ 3 የሆነ የንግድ ታርጋ በማዉጣት በቴክኖሎጂ ታግዘዉ በከተማዋ መንቀሳቀስ እንዲችሉ እየሰራ መሆኑን የተላላኪ ኤክስፕሬስ ሃላፊነቱ የተጠበቀ የግል ማህበር አስታወቀ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ ተገለጸ!

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሃሴ 1/2011 ጀምሮ እስከ መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ። በእያንዳንዱ ችሎት ምርመራና ውሳኔ የሚጠብቁ በርካታ መዝገቦች ምክንያት የፌዴራል ዳኞች ያለምንም ዕረፍት ለ10 ተከታታይ ወራት አድካሚውንና ፋታ የማይሰጠውን የዳኝነት ስራ ሲሰሩ ቆይተው በክረምት ወራት ለዕረፍት እንዲወጡ ማድረግ እንደ አንድ አሰራር ተወስዶ ሲሰራበት ቆይቷል ያለው ፍርድ ቤቱ በዚሁ መሰረት ፍርድ ቤቶቹ ከነሐሴ 1/2011 እስከ መስከረም 20/2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩ ይሆናል፡፡

ፍ/ቤቶች የዜጎች መብቶችን የሚያስከብሩ ተቋማት ስለሆኑ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው 50 ቀናት አስቸኳይና ጊዜ የማይሰጡ ከዜጎች መሰረታዊ መብቶችና ከአገር ሰላምና ፀጥታ ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደ የጊዜ ቀጠሮ፣ የዋስትናና የዕግድ ጥያቄዎች፣ የመያዣና የብርበራ ትዕዛዞች፣ በተፋጠነ ስነ-ስርዓት የሚታዩ የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች እንዲሁም ከቤተሰብና ከሕፃናት ቀለብና አስተዳደግ ጋር የተያያዙ አጣዳፊ መሰረታዊ ጉዳዮች በተረኛ ችሎቶች የሚስተናገዱ መሆኑ ተገልጿል።

ፍርድ ቤቶች በክረምት የሚዘጉበት ምክንያት የዳኞች አመታዊ የዕረፍት ጊዜ እንደማንኛወም የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኛ በመደበኛ ወቅት ማካሄድ አሁን ካለው የዳኝነት አሰራር ጋር የሚጣጣም ሆኖ አለመገኘቱ ነው ተብሏል፡፡

ፍ/ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆኑበት ጊዜ ዳኞች በዳኞች መልካም ፈቃድ የእረፍት ጊዜያቸውን ተጠቅመው ወደ ቀጣዩ ዓመት የተሸገሩ መዛግብትን የማጥራት ስራ እንደሚሰሩም ተጠቁሟል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

“አረና” የመገንጠል አላማ ያላቸውን ሃይሎች አጥብቄ እታገላለሁ አለ!

በትግራይ የተለየ አስተሳሰብን የማፈን እንቅስቃሴ እንዲቆም ጠይቋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተቀነቀኑ ያሉ ፀረ አንድነት ዘመቻዎችን እቃወማለሁ ያለው አረና ትግራይ ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ፤ በትግራይ የመገንጠል አላማ ያነገቡ አደረጃጀቶች መበራከታቸው አሳሳቢ ነው ብሏል፡፡ 

ፓርቲው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባወጣው መግለጫ፤ የትግራይ ክልል ህዝብን ከሌሎች ክልል ህዝቦች ጋር ለማጋጨት በመንግስታዊ ሚዲያዎችና በማህበራዊ ድረ ገፆች ጥረት እየተደረገ መሆኑን በመጠቆም፤ በማንኛውም መልኩ ህዝቦችን ለማጋጨት የሚደረጉ ጥረቶችን በጥብቅ እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡ 

#በጥላቻና ባልተገቡ ዘመቻዎች #መፈናቀል የደረሰባቸው የትግራይ ተወላጆች እርቅ ተፈጽሞ ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ የጠየቀው አረና፤ የወሰን ጥያቄዎችም #በውይይትና #መግባባት መፈታት እንዳለባቸው ገልጿል፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/AA-08-06-2
የሃድያ ዞን ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል። ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሄደው አስቸኳይ ጉባኤው በዞኑ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ይመክራል ተብሏል። ጉባኤው በዞኑ ደኢህዴን ንኡስ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አማካሪነት ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪነት ጀምሮ በአደረጃጀት የተጓደሉ አመራሮች የሚቀርቡ እጩዎችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የቀድሞ የሀድያ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ አያሌው ዝና "የአካባቢውን ህብረተሰብ ደህንነት ሳያስጠብቁ ለስጋት ዳርገዋል" በሚል ደኢህዴን ከስልጣናቸው ማገዱ ይታወሳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የአሸንዳ በዓል ለሰላምና አንድነታችን"

የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የዘንድሮውን የአሸንዳ በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ። የቢሮው ሃላፊ ወይዘሮ ብርክቲ ገብረመድህን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፥ በዓሉ ከነሐሴ 16 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በመቐለ ከተማና በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ብለዋል። የዘንድሮው በዓል “የአሸንዳ በዓል ለሰላምና አንድነታችን" የሚል መሪ ሃሳብ እንዳለውም ተናግረዋል።

Via #ፋና_ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ጾመ-ፍልሰታ ለሕዝብ ሰላም፣ ለአገር ልማትና አንድነት ወደ ፈጣሪ የምንጮህበት ሊሆን ይገባል” – ቅዱስ ፓትርያርኩ

ህዝበ-ክርስቲያኑ የቅድስት ድንግል ማርያም መታሰቢያ ፍልሰታን በሚጾምበት ወቅት ለሕዝብ ሰላም፣ ለአገር ልማትና አንድነት ፈጣሪን አጥብቆ በመማጸን ሊሆን ይገባል አሉ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የ2011 ዓም ጾመ-ፍልሰታን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል። ጾሙ የቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰታን በማሰብ፣ በይቅርታ፣ በምሕረት፣ በጸሎት፣ በአምልኮት፣ በስግደት፣ ቅዱስ ቁርባንን በመቀበል የእምነቱ ተከታዮች ከፈጣሪ ለመገናኘት የሚጾሙት ነው ብለዋል።

ስለዚህም ጾሙን “ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ሕፃን፣ አዋቂ ሳይባል ሁሉም እግዚአብሔርንና ቅድስት ድንግል ማርያምን በመሻት ፍቅርንና መታዘዝን፣ ሰላምንና አንድነትን እንደሸማ በመጎናጸፍ ሁሉም ሊጾመው ይገባል” በማለት ጥሪ አቅርበዋል።

ጾሙ የሕዝቡ ሠላም፣ የአገር ልማትና አንድነት፣ እስከ ዘለቄታው እንዲጠበቅ፣ ፍትሕና እኩልነት፣ ይቅርታና ፍቅር በኢትዮጵያ እንዲነግስ አጥብቀን ወደ ፈጣሪ የምንጮህበት ነው ሲሉም ተናግረዋል።

በተለይም “በሰው ሠራሽ ምክንያቶች ከቀያቸው የተፈናቀሉና ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን እንዲሁም በልዩ ልዩ ምክንያት የኑሮ እጥረት ያጠቃቸውን ወገኖች ካለን ከፍለን በመመገብና በማልበስ ለእግዚአብሔር ያለንን ታዛዥነት ማረጋገጥ ይገባል” ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በአገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ተከታዮች ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ለጥላቻ መሪዎችና ንግግሮቻቸው ትኩረት እንዳትሰጡ"

አሜሪካዊያን ለጥላቻ መሪዎችና ንግግሮቻቸው ትኩረት እንዳይሰጡ የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ተናገሩ፡፡ ፕረዝዳንቱ አሜሪካዊያን ለጥላቻ ንግግርና ለዘረኝነት ቦታ መስጠት የለባችሁም ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ ለጥላቻና ለዘረኝነት ልባቸውን ክፍት ያደረጉ በጎ ያልሆኑ አመለካከቶችን በጋራ ልንከላከላቸው ይገባል ብለዋል በመልክታቸው፡፡

ይህ ንግግራቸውም የአሁኑ የአሜሪካ ፕረዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የነጭ የበላይነት ብሎ ነገር የለም ሁሉም ዜጎች እኩል ናቸው ማለታቸውን ተከትሎ በትራምፕ ንግግር ላይ አጽኖት ለመስጠት እንዳሰቡ የተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ናቸው። የኦባማ የአሁኑ አስተያየት ከሰሞኑ በአሜሪካ ከመሳሪያ ቁጥጥር ጋር ተያይዞ የተከሰቱ የጅምላ ግድያዎች በጥቁሮች ላይ አነጣጥሯል መባሉ፤ የፕረዝደንት ትራምፕ የመሳሪያ ቁጥጥር መላላት የዚህ ሁሉ ቀውስ መንስኤ እንደሆነ ለማመላከትና የሰነዘሩት ነውም እየተባለ ነው። ቴክሳስ ኦሃዮ ውስጥ 31 ሰዎች በጅምላ ጥቃት ከተገደሉ በኋላ ዶናልድ ትራምፕ ጥላቻ እና የነጭ የበላይነትን ማስወገድ አለብን ሲሉ ተደምጠው ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

16 ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው አለፈ!

ከሊቢያ ወደ ጣሊያን በባህር ሲጓዝ በነበረ #ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ የ16 ኢትዮጵያውን ዜጎች ህይወት አለፈ። ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ባጋጠመው በዚህ አደጋ 16 የትግራይ ተወላጆች ህይወት ማለፉን የክልሉ የህዝብና መንግስት ግንኙነት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው በዛሬው ዕለት በሰጠው የሀዘን መግለጫ ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ሲጓዝ በነበረ ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ ህይወታቸው ካለፉት ዜጎች ውስጥ 10ሩ ሴቶች መሆናቸውን ገልጿል። በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ዜጎችም በክልሉ ኢሮብ ተብሎ የሚጠራው ወረዳ ተወላጆች መሆናቸው ታውቋል።

የክልሉ መንግስት በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ፥ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝቷል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የስራ_አጥ_ካርድ

"በእውነት እየተሰራብን ያለው ነገር ግራ ገብቶናል የስራ አጥ ካርድ ለማውጣት ወረፋ በዝቶብን ትላንት ተመለስን፤ ዛሬ ሄደን ስንጠይቃቸው ለ1 ወር አቁመናል፤ ሰው በዝቷል አሉን። ይህን ነገር የሚመለከተው አካል አይቶ ባፋጣኝ ምላሽ ይስጠን ምክንያቱም ጊዜያችንን እያቃጠሉ ነው ያሉት።"

የሚመለከተው አካል ምላሽ ካለው @tsegabwolde
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ!

አንድ ተቋም ተማሪ ለመቀበል በተለያዩ መንገዶች ራሱን ሊያስተዋውቅ ይችላል፤ ኤጀንሲው በፈቀደለት የእውቅና ፈቃድ መሰረት የሚያስተዋውቅ ይኖራል፤ በተቃራኒው ደግሞ ፈቃድ ሳይሰጠው የተሰጠው በማስመሰል በመገናኛ ብዙሃን ወይም በሌላ ራሱን በማስተዋወቅ የዜጎችን ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ የሚቀበሉ አሉ።

ማንኛውም ተቋም በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ ወይም በበራሪ ወረቀት ራሱን ስላስተዋወቀ ብቻ የእውቅና ፈቃድ ወይም የእውቅና ፈቃድ እድሳት ማግኘቱን አያረጋግጥም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/HEQ-08-06
ዘውትር ማክሰኞ ከምሽቱ 12:00-1:00
ልዩ መረጃ ከኤልያስ መሰረት ጋር
በኢትዮ FM 107.8
“የጥበብ ሰው ደበበ እሸቱ ይናገራሉ እኔን የምትወዱኝ ከሆነ ሊድን የሚችለውን የዓይን ብሌን ጠባሳ ማዳን እንችል ዘንድ ከህልፈታችሁ በኋላ የዓይን ብሌናችሁን ለመለገስ ቃል ግቡልኝ ለኔ ልደት ስጦታ ከዚህ የበለጠ ገጸበረከት የለም”
ባሉትም መሰረት ኮሚቴው ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ የተገኝተን ከ31 በላይ የሚሆኑ የሳቸው አድናቂ ታዳጊ እና አንጋፋ የጥበብ ባለሞያወች ቃል ገብተዋል
ጋሽ እሸቱም የዓይን ባንካችን አንባሳደር ሆነዋል። እናመሰግናለን! ብርሃን ይስጡ ብርሃን ኣቅበሩ!! ፔጃችን መከተለወንና መወደደወን አይዘንጉ ለጓደኛወ ያጋሩ
pleas share & invite to your friends https://www.facebook.com/EYEBANKOFETHIOPIA/
የሃይማኖት ተቋማት ከዘረኝነት፣ ከአድልኦ እና ከአፍቅሮተ ንዋይ በፀዳ መልኩ ሕዝብን ሊያገለግሉ እንደሚገባ ተገለጸ። ይህ የተባለው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሃይማኖት ተቋማት ወቅታዊ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ለመመካከር ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው። መድረኩ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኞች እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በመልካም አስተዳደር ችግሮቻቸው ዙሪያ የሚመክሩበት ነው።

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia