TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በኳታር ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከሀገሪቱ ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ጋር በዶሃ ተወያይተዋል።

Via #PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከአዲስ አበባ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ሀሳቦች አዲስ አበባ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ባህር ዳር፣ መቐለ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ ነቀምት ሂዶ እንደሚሰራውና የኔ ናቸው እንደሚለው ሁሉ አዲስ አበባም ተመሳሳይ ነች፤ #የሁሉም ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ነች ብለዋል። #ODP

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቱ🔝

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ ከኦሮሚያ ክልል ዋና አስተዳዳሪ አቶ #ለማ_መገርሳ ጋር በመሆን ከኢሉባቡር ዞን ነዋሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቱ🔝

በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ እና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት አቶ #ለማ_መገርሳ የተመራውና መቱ ከተማን በመጎብኘት ላይ የሚገኘው ልኡክ በከተማው ወደ 66 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ በ3ሺህ 2 መቶ ሔክታር መሬት ላይ ለሚገነባው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ማዕከል መቱ ቅርንጫፍ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል። ልዑኩ በማረሚያ ቤት የተገነባውን የመዝናኛ ማዕከልን በመጎብኘት የመቱ ዩንቨርስቲ መንገድ ፕሮጀክት የመረቀ ሲሆን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋርም ተወያይቷል።

Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቱ...

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከመቱ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ከሰዓታት በፊት ተወያይተዋል። #PMOEthiopia

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ዮናስ ከስልጣናቸው ተነሱ...

(ከጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት @eliasmeseret)

ላለፉት ስምንት አመታት የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል የነበሩት አቶ ዮናስ ደስታ በጠ/ሚር #አብይ_አህመድ ትእዛዝ ከስልጣናቸው ተነስተዋል። አቶ ዮናስ ዛሬ ማለዳ ለአለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በላኩት የፅሁፍ መልዕክት "ወደሚቀጥለው የህይወቴ ምእራፍ ስሸጋገር የተደበላለቀ ስሜት ቢኖረኝም የጠ/ሚር አብይን እርምጃ በፀጋ ተቀብያለሁ" ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ለአራት ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ።

በዚህ መሰረት፦

ዶክተር አለሙ ስሜ - የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር

አቶ ጃንጥራር አባይ - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር

ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን - በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ

አቶ ገዛኸኝ አባተ - የኢትዮጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሃምሊን ፊስቱላ ማዕከል መሥራች ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን ሐውልት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በተገኙበት ተመረቀ። ሐውልታቸው የቆመው በአዲስ አበባ ጦር ኃይሎች በሚገኘው የሃምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል ውስጥ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትሩም ሆስፒታሉን ጎብኝተዋል።

"ዶ/ር ሃሚሊን ለምን እንደተፈጠሩ ያወቁ እድለኛ እናት ናቸው” ጠ/ሚ ዶ/ር #አብይ_አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ተፈናቃዮች እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ወደ ቀያቸው ይመለሳሉ" - የሰላም ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ወደ ቀያቸው እንደሚመለሱ የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ። በሀገሪቱ ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ አንድ ሚሊዮን ገደማ ሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውንም ገልጿል።

በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን በተመለከተ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ተግባር “በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ እና ክብራቸውን በጠበቀ” መልኩ የተከናወነ ነው ብለዋል። “ተፈናቃዮች አለፍላጎታቸው እየተመለሱ ነው” በሚል የሚቀርቡ ወቀሳዎችም “ሀሰት” ሲሉ ሚኒስትሯ አስተባብለዋል።

ወ/ሮ ሙፈሪሃት በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ሁለት ሚሊዮን 332 ሺህ ገደማ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫቸው አስታውሰዋል። ከእነዚህ መካከል ግማሽ ያህሉ የተፈናቀሉት ከመጋቢት 2010 ዓ ም በፊት መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሯ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑት በክልላቸው ውስጥ የተፈናቀሉ መሆኑንም ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አህመድ ስልጣን ከያዙ ከሚያዝያ 2010 ዓ. ም. ወዲህ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር 1.1 ሚሊዮን ነው ተብሏል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ር ዶ/ር #አብይ_አህመድ የመንግስትን የ2011የሥራ አፈጻጸም ሪፓርት ሰኞ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባሉ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 8ኛ ልዩ ስብሰባውን ሰኞ ሰኔ 17 ቀን 2011ዓ.ም ጠዋት ያካሂዳል።

Via #EPA
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኢንተርኔት #መዘጋቱ ያስፈለገው የሰዎችን #ህይወት እና ንብረት ከጥቃት ለማትረፍ ነው። ኢንተርኔት ውሀ ወይም አየር አይደለም። ለመዝጋት ምክንያት የሆኑንን ምክንያቶች ካልፈታን ለሳምንት ሳይሆን እስከ ወዲያኛው #ሊዘጋ ይችላል!" ጠ/ሚ ዶ/ር #አብይ_አህመድ

Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#PMO

ጠ/ሚ ዶክተር #አብይ_አህመድ ብሄራዊ የኢንቨስትመንት እና የስራ እድል ፈጠራ መሪ ኮሚቴን ስራ አስጀመሩ። የብሄራዊ ኮሚቴው መቋቋም ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ የሱዳን ተቃዋሚዎች ስብስብ ከሆነው የነፃነትና የለውጥ ሀይል አባላት ጋር ተወያዩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የነፃነትና የለውጥ ሀይል አባላት በሱዳን የይቅርታ እና የአንድነት ባህልን እንዲያዳብሩ አበረታተዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትሩ 25,000 ዩሮ ለመልካም ወጣት ግንባታ ማዕከል አበረከቱ!

ጠ/ሚ ዶ/ር #አብይ_አህመድ ከሰሞኑን በሰላም ሽልማት ያገኙትን 25,000 ዩሮ ለመልካም ወጣት የማዕከል ግንባታ እንዲውል አበርክተዋል።

በአሁን ሰዓት በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ በሚገኘው "#የመልካም ወጣት ለኢትዮጵያ አንድነት" የመዝጊያ ዝግጅት ላይ ምክትል ጠ/ሚ ክቡር አቶ ደመቀ መኮንንም ተገኝተዋል።

#TIKVAH_ETHIOPIA

ፎቶ📸#SignorinaSolomon
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከአውሮፓውያኑ የ2019 የሔስያን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25 ሺህ ዩሮ ለመልካም ወጣት ማእከል ግንባታ አበርክተዋል።

የዛሬን ውሎ የተመለከተ ዘገባ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-06-5
#ሆሳዕና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ በሃዲያ ባህል አዳራሽ ዞኑ ነዋሪዎች ጋር ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ። በርካታ ጥያቄዎችም ተነስተው ምላሽ ሰጥተዋል። ወደበኃላ ዝርዝር ጉዳዮች ይኖሩናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
WOLAITA SODO

በጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ የተጻፈው ‘’መደመር’’ መጽሐፍ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ተመርቋል፡፡

Via SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia