TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ግብፅ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር #ገዱ_አንዳርጋቸው ወደ ግብፅ አቅንተው ከፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል-ሲሲ ተገናኝተዋል። ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ ፕሬዝዳንቱን ሲያገኙ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እና የጠቅላይ ምኒስትሩ ልዩ አማካሪ አቶ ግርማ ብሩ አብረዋቸው ነበሩ።

Via #Eshet_Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ ከሶስትዮሽ ውይይት ውጪ ሌሎች ምክረ ሀሳቦችን እንደማትቀበል የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ዛሬ ገልፀዋል።

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በዛሬው ዕለት ለካቢኔ አባላት እና ለባለድርሻ አካላት የግድቡን አሁናዊ ገፅታ እና በግብፅ ወቅታዊ አቋም ላይ ማብራርያ ሰጥተዋል። ሚኒስትሩ በማብራሪያቸውም የግድቡን አሁናዊሁኔታ እና የወደፊት እቅዶች ላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፥ በዚህም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በትኩረትና በተገቢው ፍጥነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል እየተደረገ ባለው ውይይት ዙሪያም ሚኒስትሩ ገለጻ አድርገዋል። በዚህም ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፥ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የቀጣናውን እና የተፋሰሱን ሀገራት ግንኙነት የሚያጠናከር መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሆኖም ግን ግብጽ ከሶስትዮሹ ውይይት ውጪ በሱዳን ካርቱም በተደረገው ውይይት ላይ ያቀረበችው ምክረ ሃሳብ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚጥስ መሆኑ መሆኑን አስታውቀዋል። ግብጽ ባቀረበችው ምክረ ሀሳብ ላይም በየዓመቱ 40 ቢሊየን ሜትር ኪዮብ ውሃ ይለቀቅልኝ ማለቷ እና የአስዋን ግድብ ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ 165 ሜትር ሲደርስ ኢትዮጵያ ውሃ መልቀቅ አለባት፤ እንዲሁም ሶስተኛ ወገን በአደራዳሪነት ይግባ የሚል አቋም ማቅረቧን አንስተዋል።

ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንደተናገሩት፥ #ግብፅ ያቀረበችው መክረ ሃሳብ ኢትዮጵያ በውሃው ላይ ያላትን መብት የሚጥስ እና ብሄራዊ ጥቅሟን የሚጎዳ በመሆኑ ኢትዮጵያ መቼም ቢሆን የምትቀበለው አይሆንም ብለዋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BREAKING

ኮሮና ቫይረስ አፍሪካ ገብቷል!

በአፍሪካዊቷ ሀገር #ግብፅ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ግለሰብ መኖሩ ተረጋገጠ። ግብፅ የመጀመሪያዋ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ የተገኘባት አፍሪካዊ ሀገርም ሆናለች። ከግብፅ የጤና ሚኒስትር እንደተሰማው ከሆነ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃው ግለሰብ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው፤ ግለሰቡ የምን ሀገር ዜጋ እንደሆነ ግን አልተገለፀም።

#COVID19
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶ/ር አሸብር ወ/ጊወርጊስ የአኖካ የዞን 5 ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ።

11 አባል ሀገራት ያሉት የአፍሪካ የዞን 5 ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ዛሬ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ለፕሬዝደንትነት ኢትዮጵያ እና ግብፅ ለመጨረሻው ምእራፍ ደርሰው #ኢትዮጵያ 7 ድምፅ በማግኘት የፕሬዝደንትነት ቦታውን ተረክባለች።

የኢትዮጵያ ተቀናቃኝ የነበረችው #ግብፅ 3 ድምፅ ማግኘቷ ታውቋል።

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የዞን 5 የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ፕሬዝደንት ሆነው ተመርጠዋል።

ይህንም ተከትሎ ኢትዮጵያ በአኖካ (የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር) ላይ የስራ አስፈፃሚ አባልነት ቦታን ታገኛለች ተብሏል።

መረጃው የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#AFCON

የአፍሪካ ዋንጫ በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል።

የውድድሩ ፍፃሜ ጨዋታ ተፋላሚዎች #ሴኔጋል እና #ግብፅ ሲሆኑ ጨዋታው ተጀምሯል።

ይህ ጨዋታ በመላው አፍሪካ እንዲሁም በዓለም አቅፍ ደረጃ እጅግ በጉጉት የሚጠበቅ ነው።

የዋንጫው 🏆 ባለቤት ማን ይሆናል ?

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ 🌍

➡️ #ሶማሊያ ፦ በሶማሊያ እየተባባሰ ያለው የድርቅ ሁኔታ ለምግብ እጦት እና ለውሃ እጥረት የተጋለጠው ህዝብ ቁጥር 8 ሚሊየን ሊደርስ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል። አሁን ላይ በሀገሪቱ ያለው ድርቅ በገጠር 66 ወረዳዎችና ሰፊ አካባቢዎች ክፉኛ መቷል።

➡️ #ዩክሬን ፦ ዩክሬን በጦርነቱ ምክንያት 243 ህጻናት መሞታቸውን እና 444 ህፃናት መቁሰላቸውን አረጋግጫለሁ ስትል አስታውቃለች።

➡️ #ግብፅ ፦ የግብፅ ፍርድ ቤት በቀድሞው የፕሬዚዳንት እጩ አብደል ሞኒም አቡል ፎቱህ እና በሙስሊም ወንድማማች ቡድን ውስጥ ያሉ ታዋቂ ግለሰቦችን " የሀሰት ዜና በማሰራጨት " እና መንግስትን ለመገልበጥ አሲረዋል በሚል በእስራት እንዲቀጡ ወስኗል። አቡል ፎቱህ 70 ዓመታቸው ሲሆን የ15 አመት እስራት ተፈርዶባቸዋል፣ መሐመድ አል-ካሳስ የአቡል ፎቱህ " Strong Egypt Party " ምክትል ኃላፊ የ10 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል፣ እንዲሁም የ15 አመት እስራት የተፈረደባቸው የወንድማማችነት የቀድሞ የበላይ መሪ ማህሙድ ኢዛት ሲሆኑ እሳቸው ቀደም ሲልም በሌሎች ክሶች የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ነበር።

➡️ #ሱዳን ፦ የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ጥቅምት 25 የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ተጥሎ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳቱን አሳውቀዋል። ቡርሃን " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአገር አቀፍ ደረጃ ተነስቷል " ብለዋል።

➡️ #ሩስያ ፦ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የዩክሬን #ዶንባስ ግዛትን ነፃ ማውጣት ለሞስኮ ምንም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ገልፀው ሌሎች ግዛቶች የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን ለራሳቸው መወሰን አለባቸው ብለዋል።

#ቲአርቲ #AJ #ኤፒ #SNTV

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ከሰሞኑን የፌዴራሉ መንግስት የ #ሰላም_ስምምነቱን በተመለከተ ከ50 በላይ ለማሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማብራሪያ ሰጥቶ ነበር።

ማብራሪያውን ከሰጡት መካከል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር) ነበሩ።

በወቅቱ ፤ የመድረኩ ተሳታፊ የነበሩት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን አቅርበው ነበር።

ምን ተጠየቀ ? ምንስ ምላሽ ተሰጠ ?

- ስለወልቃይት ባለቤትነት፣
- ስለኤርትራ ወታደሮች፣
- ስለሰላም ስምምነቱ ግልጽነትና የመረጃ አሰጣጥ፣
- ስለሰላም ስምምነቱ ተደራዳሪዎች ጥያቄዎች ቀርበው ነበር።

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ (የኢሶዴፓ) ምክትል ፕሬዚዳንት ራሔል ባፌ (ዶ/ር) ፦

" ከወልቃይት ጋር እየተነሳ ያለው ጉዳይ፣ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በአንድ በኩል የባህር በር ስታጣ በሌላ በኩል ደግሞ ወልቃይትን በመቀማት አገሪቱ ከሌላ አገር ጋር እንዳትገናኝ ለመዝጋት የተደረገ እንቅስቃሴ በመሆኑ መንግሥት ጉዳዩን እንዴት እየተከታተለው ነው ? "

የኢዜማ ተወካይ ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) ፦

" በሰላም ስምምነቱ ትግራይ ክልል ከአማራና ከአፋር ክልሎች ጋር በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች የሚነሱ ጉዳዮችን በተመለከተ ስምምነቱ ምን ይላል ? በዚህ የተዳፈነ እሳት ላይ የታሰበ ነገር ካለ ቢነገረን ? "

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) አመራር አባል አቶ ሙላቱ ገመቹ ፦

" የኤርትራ ሠራዊት ከትግራይ ክልል አልፎ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ነው። መንግሥት ለምን ዝምታን መረጠ ? "

የእናት ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሰይፈ ሥላሴ አያሌው (ዶ/ር) ፦

" የሰላም ስምምነት ለአገር ተሰፋ የፈነጠቀ ቢሆንም፣ ድርድሩ ሲካሄድ የተሳተፉ የብልፅግና እና የሕወሓት ሰዎች ብቻ መሆናቸው ቅሬታ ፈጥሮብናል።

በጦርነቱ ውስጥ ዋነኛ ሰለባና ገፈት ቀማሽ የነበሩት የአማራና የአፋር ክልሎች ሕዝቦች ለምን እንዲሳተፉ አልተደረገም ?

በተጨማሪም እየተከናወኑ ያሉ ውይይቶችና ድርድሮች ለሕዝብ እየተነገሩ አይደለም።

ሲዋጋ፣ ሲሞትና ሲቆስል የነበረው ሕዝብ በመጨረሻ ስለተደረሰበት ስምምነት መንግሥት መረጃ ሊሰጠው የገባል።

ከአራት ዓመት በፊት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከነበረበት ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ ሲደረግ መንግሥት ፈጸምኳቸው ያላቸውን ስምምነቶች በርካታ ቢሆኑም፣ ለሕዝብ ግልጽ ሳይደረጉ አሁን የሚታየው ጥፋት ተከስቷል። "

የጠ/ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን ምላሽ ሰጡ ?

አምባደር ሬድዋን ሁሴን ፦

ወልቃይት ...

" የወልቃይት ጉዳይ በ #ሕገ_መንግሥቱ መሠረት ይፈታል።

ከጅምሩ የጦርነቱ ዓላማ ወልቃይትን ማስመለስ እና ሕወሓትን ማጥፋት አልነበረም።

የጦርነቱ ዋና ዓላማ የነበረው የአገሪቱን ሉዓላዊነት ማስከበርና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ማስፈን ነው

ሕወሓትን እንደ ፖለቲካ ኃይል የማጥፋት ዓላማ ያለው ሰው ይኖራል፣ ነገር ግን የፌዴራል መንግሥቱ ዓላማ አይደለም።

ወልቃይት በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል ያለ ፀብ ነው፣ በሁለት ክልሎች መካከል ያለው ፀብ ደግሞ የሚፈታው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚመራው ሥርዓት።

የፌዴራል መንግሥት አቋም ተራ በተራ ጡንቻ እየተፈታተን አንዳችን ሌላችንን ማንበርከክ ይቁም የሚል ነው።

ወልቃይትን ከዚህ ቀደም ሕወሓት ጡንቻ ስለነበረው በጉልበት ወስዷል፣ አሁን ደግሞ ሕወሓት ሸብረክ ሲል ጡንቻ ያለው አካል ይውሰድ ካልን መጪው ትውልድ 20 ዓመታትን ጠብቆ ድንገት ጡንቻ ካገኘ ይወስደዋል ፤ ስለዚህም ዘላቂው መፍትሔ ጡንቻ ሳይሆን ሕግና ሥርዓት ነው።

አንድ ሰው ትግራይን ሲወድ ካርታውን ብቻ ሳይሆን ሕዝቡን ነው፣ ነገር ግን ካርታውን ወዶ ሕዝቡን መጥላት አይቻልም።

ቲፎዞና ደም መርጠን መለቃቀስ ይቅር፣ የትም ቦታ ሰው ሲሞት ሁላችንም  ሊሰማን ይገባል። "

ኤትራን በተመለከተ ...

" የእኛ ወገን ናቸው የምንላቸው የሕወሓት ሰዎች ለ30 ዓመታት ታገልኩለት ያሉትን ሕዝብ ለ30 ዓመታት እየቀለበ፣ እየጠበቀ፣ አብሮ እየሠራና እያረሰ የኖረውን ሠራዊት ከጀርባው አርደው ሜዳ ላይ ሲጥሉት የታደጉት እነዚህ ሰዎች ናቸው፡፡ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ውለታን መርሳት ነውር ነው።

በሦስተኛው ዙር አገሪቱን ለመጨረሻ ጊዜ ለማፍረስ በተካሄደው ጦርነት የፌዴራል መንግሥት በቆቦ በኩል ባለው ዳገት ወደ ላይ መውጣት ላዳገተው፣ ሕወሓት ያለውን መልክዓ ምድራዊ ጠቀሜታ ተጠቅሞ ቆቦን ተቆጣጥሮ ነበር።

ወቅቱ ክረምት ስለነበር በምዕራብ በኩል ተከዜን ሠራዊቱ ማቋረጥ ባለመቻሉ ፣ #በዛላምበሳ እና #በአዲግራት ለመምጣት ተከዜን መሻገር የኤርትራ መንግሥት በመፍቀዱ ጦርነቱ ሊቀለበስ ችሏል።

ለአጭር ጊዜም ቢሆን በራቸውን ባይፈቅዱልን ኖሮ ይኼንን ጦርነት መቀልበስ አይቻልም ነበር፡፡ እንደ አገር ከባድ ፈተና ውስጥ እንወድቅ ነበር።

የኤርትራ መንግሥት ይኼን ያደረገው ሕወሓት በዚያ ጊዜ የጋራ ጠላታችን ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ሕወሓት የጋራ ጠላት የሚሆነው ትጥቁን እስኪፈታ ነው። ትጥቁ ከሌለ አደጋ አይሆንም።

በፖለቲካ መጠላላት እና መለያየት ሲኖር ያለ ሦስተኛ ወገን በራችንን ዘግተን መነጋገር እንችላለን። "

የኤርትራ ሰራዊት ጉዳይ ...

" ' የኤርትራ ሠራዊት ከኢትዮጵያ ይውጣ ' የሚሉት አካላት ለኢትዮጵያ አዝነው አይደለም። ኤርትራ ይውጣ የሚሉ አካላት ሱዳን 50 ኪሎ ሜትር አልፎ ድንበር ወሮ በነበረበት ወቅት አፋቸውን ዘግተው ነበር።

በተመሳሳይ #ግብፅ በሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ መድባ ወደ ኢትዮጵያ መሣሪያ እያስገባች በጋምቤላ ለኦነግ ሸኔና ለሕወሓት ጭምር በአየር እና መሬት ላይ ስታስታጥቅ፣ እነዚህ ምንም አላሉም ፤ ይህ የሚያሳየው መንግሥትን የሚያዳክም ሲሆን ዝምታ፣ መንግሥትን የሚያግዝ ሲሆን ደግሞ ጩኸት ማብዛት የሚወዱ በመኖራቸው ነው።

በመሆኑም ኤርትራ እኛን አስቸገረን ካላልን ምን አሳሰባቸው ? ኤርትራ ባስቸገረን ጊዜ እኛ ራሳችን በቃን እንላለን፡፡

የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ካሳሰባችሁ ሱዳን ትውጣ ብላችሁ መግለጫ አውጡ፡፡ ከዚያ ኤርትራ ትውጣ ብትሉ እኛ መረዳት እችላለን።

በሌላ በኩል በእኛ አስታኮ የኤርትራ መንግሥትን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም፡፡ ቢያንስ ከተፈጠረው የሰላም ስምምነት አንፃር እኛ እንዳንፈርስ አግዘውናል፡፡

የጋራ ጠላት የነበረን ቢሆንም ትጥቁን የፈታ የሕወሓት ታጣቂ ግን ኢትዮጵያዊ ነው። ስለዚህ አቅማችን ባለበት እስኪጠናከር ሕወሓት መጀመሪያ ትጥቁን መፍታት ይጀምርና እንደማንወጋ ስናረጋግጥ፣ ከጀርባችን ያለው አካል ማንም ይሁን ማን ይውጣልን ማለት እንችላለን። "

ምንጭ፦ www.ethiopiareporter.com

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ግብፅ #ሱማሊያ

በግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ግብዣ የተደረገላቸው የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ግብፅ ካይሮ ገብተዋል።

ሁለቱ ፕሬዜዳንቶች በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት በተፈረመ ማግሥት " ከሶማሊያ ጎን እቆማለሁ " ብላ በስምምነቱ ላይ ተቃውሞ ያሰማቸው ግብፅ ነበረች።

ከዚህም ባለፈ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት በስምምነቱ ተቃውሞ ዙሪያ ቀደመው ስልክ ከደወሉላቸው መሪዎች አንደኛው ፕሬዜዳንት አልሲሲ እንደነበሩ አይዘነጋም።

ፕሬዜዳንት አልሲሲም ከቀናት በኃላ ፕሬዜዳንቱ ወደ ኤርትራ ባቀኑበት ወቅት ግብፅን እንዲጎበኙ ጥሪ አድርገውላቸው የነበረ ሲሆን በዚሁ ጥሪ መሰረት ለሁለት ቀን ጉብኝት ትላንት ምሽት ካይሮ ገብተዋል።

ግብፅ#ኢትዮጵያ 🇪🇹 የባህር በር እንዲኖራት እድልን ይሰጣል ከተባለውና ከሶማሌላንድ ጋር ከተደረገው የመግባቢያ ስምምነት ወዲህ ኢትዮጵያን የሚወነጅሉ አስተያየቶችን ስትሰጥ የነበረ ሲሆን ከሰሞኑን " ኢትዮጵያን በአካባቢው የአለመረጋጋት ምንጭ እየሆነች ነው " የሚል ንግግር በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ተናግራለች።

ኢትዮጵያም ግብፅ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ለተናገረችው ንግግር በአምባሳደር መለስ አለም በኩል ፤ " ኢትዮጵያን በአለመረጋጋት መንስኤነት መክሰስ በአንድ ቃል ለመግለፅ #ቧልት ነው፤ የዘመኑ ቀልድ ተብሎ ሊቀመጥ ይችላል። " በሚል የመልስ ምት ሰጥታታለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የግብፁ መሪ ምን አሉ ? የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር የሁለቶሽ ምክክር ካደረጉ በኃላ በጋራ ሆነው መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህም ወቅት የግብፁ መሪ ፤ " የአረብ ሊግ ቻርተር በሉዓላዊነታቸው እና በግዛታቸው ላይ ጥቃት የሚደርስባቸውን የአረብ ሀገራት እንድንከላከል ያስገድደናል " ሲሉ ተደምጠዋል። " ግብፅ በሶማሊያ ደህንነት ላይ ምንም አይነት ስጋት እንዲፈጠር…
ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ስለ ግብፅ ምን አለች ?

" በስምምነቱ ዙሪያ የሚነሱ ማንኛውንም የውጭ #ጣልቃገብነቶችን እንቃወማለን " - ሶማሌላንድ

ዛሬ የራስ ገዟ ሶማሌላንድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል መግለጫ አውጣለች። በዚህ መግለጫም ስለ ለሰሞነኛው የግብፅ ሁኔታ ምላሽ ሰጥታለች።

ምን አለች ?

ሶማሌላንድ ፤ ከግብፅ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት ከፍ አድርጋ እንደምትመለከት ገልጻ በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ላይ ያላትን ስጋትም እውቅና እንደምትሰጥ ገልጻለች።

" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተከሰቱ ክስተቶች አንፃር ቀጠናዊ ጉዳዮችን በውይይት እና በትብብር ለመፍታት ያለኝን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጣለሁ " ብላለች።

ይሁን እንጂ በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እና በ #ኢትዮጵያ 🇪🇹 መካከል ከተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) በኋላ የሚነሱ ማንኛውንም አይነት የውጭ #ጣልቃገብነቶችን እንድምትቃወም በድጋሚ አረጋግጣለች።

በመግለጫዋ ፤ " የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር በተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች አከብራለሁ " ስትል ገልጻለች።

" ሁሉም ፍላጎት ያላቸው አካላት ቀጠናዊ መረጋጋትን እና ገንቢ አጋርነትን በማስፈን ላይ እንዲያተኩሩ አበረታታለሁ " ያለችው ሶማሌለንድ ፤ " በዚህ መንፈስም #ግብፅ በቅርብ ጎረቤቶቿ እንደ ፦
* #ሱዳን
* #ሊቢያ
* #ጋዛ ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ አቅጣጫዋን እንድትቀይር እናበረታታታለን " ብላለች።

" እነዚህ አካባቢዎች (ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ጋዛ) በአሁኑ ጊዜ ጉልህ ከሆኑ ተግዳሮቶች ጋር #እየታገሉ ነው ፤ እናም የግብፅ ገንቢ ተሳትፎ ለዘላቂ ሰላም እና ደህንነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለን እናምናለን " ስትል ገልጻለች።

የሶማሌለንድ መንግሥት በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ልማትን ለማስፈን ከሁሉም ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን እና ትብብርን ያደርጋል ስትል አሳውቃለች።

" የጋራ ጂኦፖለቲካዊ አካባቢያችንን ሁኔታ ለማሻሻል ከግብፅ እና ከሌሎች ተባባሪዎች ጋር #በመከባበር እና #በጋራ_ጥቅም ላይ የተመሰረተ ገንቢ ግንኙነትን ለመፍጠር እንሰራለን " ስትል ገልጻለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia🇪🇹 " #ኢትዮጵያ ሶማሊያ እንደ አገር ትቆም ዘንድ ብዙ መስዋዕትነትን ከፍላለች፡፡ ብዙ ሺሕ የሚቆጣጠሩ ወንዶችና ሴቶች መስዕዋት አድርገናል ገብረናል፡፡ የቆጠብነው ነገር የለም ሕይወት ሰጥተናል፣ ደም ሰጥተናል፣ ላብ ሰጥተናል፣ ጉልበት ሰጥተናል፡፡ ነገር ግን በሶማሊያ በኩል ይህንን አስተዋጽኦ ከቁብ ላለመቁጠርና ውለታ ለማስቀረት የሚደረግ መግለጫ መስማት እንደ ኢትዮጵያዊ ይኮሰኩሳል።…
#ETHIOPIA🇪🇹

የቀን ቅዠት ነው !!!

" እንደ አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምንም ዓይነት የፀጥታ ሥጋት እንዲኖር አልፈልግም ነገር ግን በኢትዮጵያ አቅም በተለይም በሕዝቦቿ ስለምተማመን እንቅልፍ አልባ ሌሊት የለኝም፡፡ #ግብፅ በሶማሊያ በኩል መጥታ ኢትዮጵያን አጣቢቂኝ ውስጥ መክተት ትችላለች ማለት የቀን ቅዠት ነው። " - አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ (የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር)

@tikvahethiopia