ዶ/ር አሸብር ወ/ጊወርጊስ የአኖካ የዞን 5 ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ።

11 አባል ሀገራት ያሉት የአፍሪካ የዞን 5 ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ዛሬ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ለፕሬዝደንትነት ኢትዮጵያ እና ግብፅ ለመጨረሻው ምእራፍ ደርሰው #ኢትዮጵያ 7 ድምፅ በማግኘት የፕሬዝደንትነት ቦታውን ተረክባለች።

የኢትዮጵያ ተቀናቃኝ የነበረችው #ግብፅ 3 ድምፅ ማግኘቷ ታውቋል።

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የዞን 5 የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ፕሬዝደንት ሆነው ተመርጠዋል።

ይህንም ተከትሎ ኢትዮጵያ በአኖካ (የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር) ላይ የስራ አስፈፃሚ አባልነት ቦታን ታገኛለች ተብሏል።

መረጃው የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT