TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update "በአርባምንጩ ተቃውሞ ግጭት እንዳይሰፋ ለተጠቀምንበት ባህላዊ ክዋኔ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው እውቅና #ለሠላም ይበልጥ እንድንሠራ የሚያበረታታ ነው" ሲሉ የጋሞ ባይራ ሽማግሌዎች ገልፀዋል።

©ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ⬆️በሀገሪቷ የተጀመረውን ለውጥ ከግብ ለማድረስ ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ጎን በመሆን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን #የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች በድጋፍ ሰልፍ ገልፀዋል።

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ⬆️ከሰሞኑን ስለሀዋሳ ከተማ ስለሚወሩ ጉዳዮች ህብረተሰቡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር #ውይይት እያደረገ ይገኛል።

©KAL(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሀገር አቀፍ ደረጃ በጋምቤላ ክልል የሚከበረውን የአለም የቱሪዝም ቀን ለማስተናገድ የሚደረገው ዝግጅት #መጠናቀቁን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል። በዓሉ “የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሽግግር ለቱሪዝም ልማት” በሚል መሪ ቃል በክልሉ እንደሚከበርም ተገጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቡልቡላ⬇️

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቡልቡላ ከተማ የሚገኘውን የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን እየገበኙ ነው። የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ በጉብኝቱ ላይ እንደተገኙ ታውቋል። ከቆይታ በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሻሸመኔ ከተማ የሚገኘውን የትራክተር መገጣጠሚያ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ በባቡር እየመጡ የነበሩት ተጓዦች መንግድ ላይ ለረጅም ሰዓታት እንዲቆሙ መገደዳቸውን አሳውቄያችሁ ነበር። አሁን በደረሰኝ መረጃ ችግሩ ተፈቶ ተጓዦቹ ጉዟቸውን ቀጥለዋል።

ሰላም ግቡ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 23 እስከ 25 #በሀዋሳ ከተማ ይደረጋል። ጉባኤው «በልማታዊ ዴሞክራሲ ማዕቀፍ የለውጥ እንቅስቃሴያችንን በማስቀጠል የኢትዮጵያን ሕዳሴ እናረጋግጥ» በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ይሆናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ከግንቦት 7 ጋር መለያየቱን አሳወቀ፡፡ድርጅቱ ከግንቦት 7 ጋር መለያየቱን አስመልክቶ #ዛሬ በባሕር ዳር መግለጫ እየሰጠ ነው፡፡

©AMMA
@Tsegabwolde @tikahethiopia
#update ኢትዮጵያ #የኒውክለር ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ተፈራረመች፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በድረ ገፁ እንዳስታወቀው ከሆነ የኒውክሌር ቴክኖሎጂዎቹ በግብርና ፣ በጤና ፣ በኢንዱስትሪ፣ በውሀ ሀብት አያያዝና በጨረራ መካከል ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡

ሚኒስቴሩ ቴክኖሎጂዎቹን በሚቀጥሉት አምስት አመታት ተግባራዊ ለማድረግ ከአለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ኤጀንሲ ጋር በዚህ ሳምንት መፈራረሙ ተነግሯል።

በዚህም መሰረት ከ2018 እስከ 2023 ተግባራዊ የሚደረጉት ፕሮጀክቶቹ በውስጣቸው የሰው ሀይል አቅም ግንባታ፣ የኒውክለር ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን፣ የላብራቶሪ መሰረተ ልማት ግንባታንና የጨረራ አመንጪ መሳሪዎች ደህንነት ጉዳዮችን ይዘዋል ተብሏል፡፡

©shegr FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዘርማ⬆️

"ሄይ "ፀግሽ እንዴት ነህ" ትናንትና ቅዳሜ 12/01/2011 ዓ.ም የጉራጌ ዘርማዎች የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና የንግዱን ሕ/ሰብ በማስተባበር በጉራጌ ዞን ውስጥ በ መስቃን እና ማረቆ ወረዳ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች መገልገያ የሚሆን 200 ፍራሽ፣ 200 መመገቢያ እቃ እና 70 አንሶላ ና የ እናቶች ልብስ......ወዘተ. ለሁለቱም ወረዳ ተፈናቃዮች በ ሁለት Isuzu መኪና በመጫን ቦታው ድረስ በመሄድ ለግሰናል፡፡ ዘርማ ኢትዮጵያ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ የተለያዩ ካምፖች ተጠልለው ከነበሩ ወገኖቻች መሐል የተወሰኑት ወደ ቀዬያቸው በዛሬው እለት ተመልሰዋል። የቀሩት ደግሞ አዲስ አበባ ባሉ አዳዲስ ካምፖች ተዛውረዋል።

በዛሬው እለት ወገኖቻችንን ለመርዳት ያዘጋጃችሁትን እህል ውሀ እና ቁሳቁሶች ለመለገስ የሚቻለው #በዊንጌት ትምህርት ቤት ብቻ ነው።

የከዚህ ቀደም ካምፖች እየተዘጉ በመሆኑ ደጋግ ሰዎች እንዳይንገላቱ መልዕክቱን ሼር በማድረግ ተባበሩን።

©ያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት በግንባታ ላይ የሚገኘውን የሻሸመኔ የተቀናጀ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ማዕከል
ጎብኝተዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከቡራዩ ከተፈናቀሉ ዜጎች በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ #ተፈናቃይ ዜጎች ቁጥር 1 ሺህ 514 ብቻ ናቸው፡፡ በቡራዩ በአሁኑ ወቅት በተፈጠረው #መረጋጋት በአዲስ አበባ ጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ከነበሩ 11 ሺህ 902 ያህሉ ወደመጡበት የመኖሪያ ቀያቸው በአዲስ አበባ አስተዳደር አማካይነት ተመልሰዋል፡፡

©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia