TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አቶ ጌታቸው አሰፋ⬇️

የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸው እና ከአገር እንደሸሹ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን በስፋት ሲዘግቡት ሰንብተዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑትን ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሔርን ስለጉዳዩ BBC ጠይቋቸዋል።

ወ/ሮ ፈትለወርቅ ''እንደ ድርጅት በዚህ ደረጃ #የምናውቀው ነገር የለም። ለድርጅት #የክስ መጥሪያ አይመጣም'' ይላሉ።

በአንድ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ላይ ድርጅቱ ሳያውቀው ክስ ሊመሠረት ይችላል ወይ ተብለው የተጠየቁት የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፤
''ውይይት የሚያስፈልገው ነገር ካለ ፖለቲካዊ ግምገማና ይደረጋል እንጂ ክስን በተመለከተ የመንግሥት ሥራ ነው የሚሆነው'' ሲሉ መልሰዋል። ኾኖም የአቶ ጌታቸው ጉዳይ በግምገማም እንዳልተነሳ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ተናግረዋል።

የኢህአዴግና የሕወሓት የሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው አሁን በተካሄደው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ #እንዳልተገኙ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ጠቁመዋል።

የአቶ ጌታቸው በስብሰባው ያለመገኘት ጉዳይ "የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸዋል ከሚለው ዜና ጋር የሚያያዝ ነው ወይ?" ተብለው የተጠየቁት ወይዘሮ ፈትለወርቅ ''አንድ ሰው ሰብሰባ ላይ በግል ጉዳይ ላይገኝ ይችላል። በስብሰባዎች ላይ ሁሉም ሰው ይገኛል ማለት አይደለም። የእሱ ከስብሰባ መቅረት ከዚህ ጋር ይገኛል ማለት #ላይሆን ይችላል። በሥራ ጉዳይም ላይገኙ ይችላሉ'' ብለዋል ወ/ሮ ፈትለወርቅ።

ለመጨረሻ ጊዜ አቶ ጌታቸውን መቼ እንዳይዋቸው ከቢቢሲ የተጠየቁት ወይዘሮ ፈትለወርቅ በቅርቡ ከሁለት ሳምንት በፊት ገደማ #መቀሌ እንዳገኟቸው አረጋግጠዋል።

📌በሌላ በኩል የፌዴራል አቃቢ ሕግ በአቶ ጌታቸው አሰፋ ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።

©BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ ተስፋዬ ኡርጌ⬇️

ፍርድ ቤቱ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ባልደረባ በሆኑት አቶ #ተስፋዬ_ኡርጌ ላይ የ15 ቀናት #የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል።

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ 1ኛ ወንጀል ችሎት በዛሬው ውሎው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ባልደረባ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ በመስጠት ለጥቅምት 27 ቀን 2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

መርማሪ ፖሊስም የምርመራ ስራውን አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ማስረከቡን ገልጿል።

አቶ ተስፋዬ በአዲስ አባባ በሰኔ 16ቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተፈጸመውን #የቦምብ ጥቃት በማሰተባበር፣ በመምራትና በቦምብ ፍንዳታ የሚሳተፉ አካላትን በመመልመል ነው የተጠረጠሩት።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia