TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት⬇️

የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ 1ኛ የወንጀል ችሎት መርማሪ ፖሊስ በአቶ #ተስፋዬ_ኡርጌ ላይ ምርመራ አጠናቆ ለማቅረብ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ፈቀደ።

መርማሪ ፖሊስ በአቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ በርካታ የምርመራ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን በመጠቆም፤ ምርመራውን አጠናቆ ለማቀረብ ተጨማሪ የሰው ምስከር ቃል ለመቀበል እና ከቤሄራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ የተደረገ የስልክ ልውውጥ የድምፅ ቅጂ ማስረጃን ለማቅረብ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ጠይቋል።

ተጠርጣሪው አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በበኩሉ በተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቁን በመግለፅ ዋስትና እንዲፈቀድለት አሊያም፤ አጭር ቀጠሮ እንዲሰጥ ጠይቋል።

መርማሪ ፖሊስም ጉዳዩ ውስብስብ በመሆኑ ቃል የምቀበለውን ተጨማሪ ምስክሮች ሊያሸሽብን ስለሚችል የዋስትና ጥያቄውን እቃወማለሁ ብሏል።

ጉዳዩን የተከታተሉው ፍርድ ቤትም የዋስትና ጥያቄውን በማለፍ፤ ፖሊስ ቀረኝ ያለውም ምርመራ አጠናቆ እንዲቀርብ ለመስከረም 5/2011 ዓ.ም ተለዋጭ #ቀጠሮ ሰጥቷል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሰኔ 16ቱ ጥቃት⬇️

በሰኔ 16ቱ የቦምብ #ፍንዳታ ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘው የብሄራዊ መረጃ ደህንነት መምሪያ አዛዢ #ተስፋዬ_ኡርጌ ፖሊስ በቢሮው አገኘሁት ያለወን #ቦምብ መስቀል አደባባይ ከፈነዳው ቦምብ ቅሪት አካል ጋር ለማመሳከር ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የጠየቀበትን ምክንያትና የተጠርጣሪውን አስተያየት አዳምጧል።

መርማሪ ፖሊስ ምርመራችንን አጠናቀን ለፌዴራል አቃቢ ህግ ያስረከብን ቢሆንም አቃቢ ህግ መስከረም 15 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ቢሮ ውስጥ ያገኘነውን ቦንብ መስቀል አደባባይ ከፈነዳው ቦምብ ቅሪት አካል ጋር በቴክኒክ ለማመሳከር ተጨማሪ ማስረጃ ይቅረብልኝ ማለቱን ተከትሎ ለፌዴራል ፖሊስ ፈንጅ አምካኝ ኦፕሬሽን ዲቪዢን ደብዳቤ ልከናል ሲል አብራርቷል።

ይህንን የቴክኒክ ምርመራ ምላሽ ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ብሏል።

ጉዳዩ ያለ አግባብ እየተራዘመ መሆኑን የገለጹት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በበኩላቸው ፍርድቤቱ አጭር ቀጠሮ ሰጥቶ ለመጨረሻ ትዛዝ ይስጥልኝ ሲሉ ጠይቀዋል።

ፍርድቤቱም በተጠየቀው የጊዜ ገደብ የቴክኒክ ምርመራው ለምን #አልተጠናቀቀም የሚል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፥ ፖሊስም ደብዳቤ ልከን ምላሽ ስላልተሰጠ እየጠበቅን ነው ሲል አብራርቷል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድቤት ተረኛ ወንጀል ችሎትም ፖሊስ ለመጨረሻ ጊዜ የቴክኒክ ምርመራውን ይዞ እንዲቀርብ ለተጨማሪ ስምንት ቀን ቀጠሮ በመስጠት ለጥቅምት አራት(4) ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የሰኔ 16ቱ ጥቃት⬇️

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ የወንጀል ችሎት የሰኔ 16ቱን የቦምብ ጥቃት አስተባብረዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩት የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት ባልደረባ የነበሩት አቶ #ተስፋዬ_ኡርጌ ላይ ፖሊስ የሚያደርገውን ምርመራ እንዲያጠናቅቅ የመጨረሻ ቀጠሮ ሰጠ፡፡

ፖሊስ ችሎቱ በፈቀደለት 10 ቀናት የሰው ምስክር መቀበሉን ብሎም ከመስሪያ ቤታቸው የተገኘው ቦምብ ለምርመራ መወሰዱንና ሌሎች ተግባራትን ማከናወኑን ጠቅሷል፡፡ ለተጨማሪ የምርመራ ስራ 10 ቀናት እንዲፈቀድለትም ጠይቋል፡፡

የሰኔ 16ቱን የቦምብ ጥቃት አስተባብረዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በቁጥጥር ስር ከዋሉ 4 ወራት መቆጠሩንና ፖሊስ የሚጠይቃቸው የግዜ ቀጠሮዎች ተገቢነት የላቸውም በማለት ቅሬታችውን አቅርበዋል፡፡

አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ቦምብ ከቤቴ ሳይገኝ ከቤቱ ተገኝቷል እያሉ በመዘገባቸው ሰብአዊ መብቴ ተነክቶብኛል የሚለውንም ጠቅሰዋል
ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለመጨረሻ ግዜ በማለት ትእዛዝ እንዲሰጥም አመልክተዋል፡፡

ግራ ቀኙን የመረመረው ችሎቱ ] ከእውነታው ውጭ የሚዘግቡ መገናኛ ብዙሃን እንደሚጠየቁና ፖሊስ ምርመራውን እንዲያጠናቅቅ የመጨረሻ ቀጠሮ በማለት 7 ቀናት በመፍቀድ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለጥቅምት 12 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ ተስፋዬ ኡርጌ⬇️

ፍርድ ቤቱ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ባልደረባ በሆኑት አቶ #ተስፋዬ_ኡርጌ ላይ የ15 ቀናት #የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል።

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ 1ኛ ወንጀል ችሎት በዛሬው ውሎው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ባልደረባ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ በመስጠት ለጥቅምት 27 ቀን 2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

መርማሪ ፖሊስም የምርመራ ስራውን አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ማስረከቡን ገልጿል።

አቶ ተስፋዬ በአዲስ አባባ በሰኔ 16ቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተፈጸመውን #የቦምብ ጥቃት በማሰተባበር፣ በመምራትና በቦምብ ፍንዳታ የሚሳተፉ አካላትን በመመልመል ነው የተጠረጠሩት።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update አቃቢ ሕግ ዛሬ በዋለ #ችሎት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ባልደረባ በነበሩት የወንጀል ተጠርጣሪ #ተስፋዬ_ኡርጌ ላይ የጀመርኩትን ምርመራ በሥራ መደራረብ ሳቢያ ማጠናቀቅ አልቻልኩም ብሏል፡፡ በባለፈው ችሎት አቃቢ ሕግ ክስ እንዲመሰርት የፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አሳስቦ የነበረ ቢሆንም ዛሬም እንደገና አቤቱታውን እንደገና ተቀብሎ የመጨረሻውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል፡፡

ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው‼️

መርማሪ ፖሊስ ሜጀር ጀኔራል #ክንፈ_ዳኘውን በተመለከተ እስካሁን በሰራው የምርመራ ስራ አገኘኋቸው ያላቸውን ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤት አቅርቧል።

ፖሊስ በዛሬው እለት ግለሰቡን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ካቀረባቸው ማስረጃዎች በተጨማሪነት አዳዲስ ያላቻውን ነው ያቀረበው።

በዚህም በ2003 ዓ.ም በሜቴክ ስም ከተለያዩ ተረፈ ምርቶች ወይም ቆሻሻ የናፍጣ ነዳጅ ማምረቻ ፋብሪካን ለመግዛት ያለ ምንም ጨረታ ኬዲቪ ከተባለ የጀርመን ኩባንያ ጋር የ8 ሚሊየን ዩሮ ግዥ ውል በመፈጸም፥ ከዚህ ውስጥ 4 ሚሊየን 800 ሺህ ዩሮ ለኩባንያው
እንዲፈጸም በማድረግ እንደጠረጠራቸውና ከዚህ ጋር የተያያዙ በርካታ የሰነድ ማስረጃዎች መሰብሰቡን ጠቅሷል።

በተጠቀሰው ዓ.ም ሜቴክ ከኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በመመሳጠር ከመመሪያ ውጭና ያለ ግዥ ፍላጎት የ22 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው 20 ተሽከርካሪዎች ግዥ እንዲፈጸምና ለተፈጸመው ግዥ ክፍያ እንዲፈጸም ለኮርፖሬት ኢንቨስትመንትና ፋይናንስ ማኔጅመንት አላግባብ ትዕዛዝ ሰጥተዋል በሚል የተጠረጠሩ፤ ተጠርጣሪው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር በነበሩበት ወቅት ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመበት አላማ ውጭ ስልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም #የኢምፔሪያል_ሆቴል ግዥ በ71 ሚሊየን ብር ከአክሰስ ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ እንዲፈጸም በማድረግ፣ ባለ አምስት
ወለል ህንጻ በ15 ሚሊየን ብር ከያማሉክ ኢንተርናሽናል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ግዥ እንዲፈጸም በማድረግና በማፅደቅ።

ባለ አራት ወለል ህንጻ በ24 ሚሊየን 56 ሺህ ብር ከአቶ አለሙ ደምሴ ግዥ እንዲፈጸም በማድረግ፣ ባለ አንድ ወለል የመኖሪያ ህንጻ በ5 ሚሊየን 700 ሺህ ብር ከአቶ ጌታቸው አቃኔ ግዥ እንዲፈጸም በማድረግ፣ ባለ ሁለት ወለል ህንጻ የመኖሪያ ህንጻ በ8 ሚሊየን 700 ሺህ ብር ከአቶ ሙላቱ ረዳ እና ከወይዘሮ ሄለን በለጠ ግዥ እንዲፈጸም በማድረግ እና ባለ ሶስት ወለል ህንጻ በ12 ሚሊየን 700 ሺህ ብር ከጌት ፋም ሃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር ባለቤት አቶ ጌታሁን በሻህ ግዥ እንዲፈጸም ትዕዛዝ በመስጠት፥ ውሎችን በማፅደቅ ግዥ እንዲፈጸምና የህዝብና የመንግስት ሃብት እንዲባክን በማድረግ ከቆሻሻ የጄት ነዳጅ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ ከግዥ መመሪያ ውጭ ጨረታ ሳይወጣ ኢ ቪ ጂቲዲሲ ዌስት ቱ ኢነርጅ ከተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር የ347 ሚሊየን 948 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ውል ስምምነት ኮሎኔል ሙሉ ወልደገብርኤል 2005 ዓ.ም ላይ ውል እንዲዋዋል በማድረግና ውሉን በማፅደቅ፣ የውጭ ምንዛሪ እንዲፈቀድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኤል ሲ በማስከፈት፣ ለባንክ አገልግሎት የሚውል ክፍያ 5 ሚሊየን 616 ሺህ 648 ብር ከ60 ሳንቲም የግንባታ ስራ ውል ስምምነት ከተፈጸመ በኋላ ውሉ ባልታወቀ ምክንያት በመቋረጡና ስራው ሳይሰራ ያለ አግባብ የመንግስት ገንዘብ እንዲባክን በማድረግ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የተከለለ ቦታ ላይ የሚገኘውን ጫካ ምንጣሮ ስራ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ስራውን በመውሰድና 2 ቢሊየን 92 ሚሊየን 303 ሺህ 113 ብር ከ22 ሳንቲም በመቀበል፥ ስራውን በሌሎች ንዑስ ተቋራጮች ያለ ምንም ጨረታ በመስጠት የምንጣሮ ስራው በአግባቡ ተመንጥሮ ሳያልቅ ገንዘብ ወጪ በማድረግ ክፍያ በመፈፀምና ቀሪ ገንዘብ የት እንዳለ ባለመታወቁ ለግል ጥቅምና ሌሎች እንዲጠቀሙ በማድረግ ከዚህ ባለፈም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመበት አላማ ውጭ እንዲሁም ከፋይናንስ ህግ ውጭ በሆነ ሁኔታ በነሃሴ ወር 2003 ዓ.ም ለአቤራ ኪነ ጥበባት ማዕከል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በስፖንሰር መልክ 536 ሺህ ብር በመስጠትና 306 ሺህ ብር በብድር መልክ መስጠትና የተበደረው ተቋም ገንዘብ ያልተከፈለ መሆኑ፥ የኮርፖሬሽኑ አባላት ያልሆኑትን አባላት እንደሆኑ በደብዳቤ በመግለጽ ለተጠርጣሪ #ፍጹም_የሽጥላ_በቀለ እና ለአቶ #ተስፋሁን_ሰብስቤ ለ30 ቀን የአሜሪካ ቆይታ 23 ሺህ ዶላር በሃምሌ ወር 2008 ዓ.ም እንዲከፈል በማድረግ፤ እንዲሁም ለአቶ #ዝናህብዙ_ፀጋዬ ለ20 ቀን የአሜሪካ ጉዞና ቆይታ 7 ሺህ 687 ከ50 ዶላር ከንግድ ባንክ እንዲከፈል በማድረግ ወጪው ከኮርፖሬት ፋይናንስ ኢንቨስትመንት እንዲሸፈን ደብዳቤ በመጻፍ፣ ለኮሎኔል አታክልት ወልደሚካኤል #ልጅ ዮናስ አታክልት የውጭ ሃገር ህክምና 86 ሺህ 889 ሺህ ከ54 ዶላር ክፍያ እንዲፈጸም በማድረግ፣ ለወይዘሮ ንግስቲ ከሰተ የውጭ ሃገር ህክምና 18 ሺህ 454 ሺህ 51 ዶላር ክፍያ እንዲፈጸምና ሌሎችም እንዲጠቀሙ ክፍያ እንዲፈጸም በማድረግ በ2004 ዓ.ም የግዥ ዘመን ከግዥ መመሪያ ውጭ አለም አቀፍ የጨረታ ውድድር ሳይደረግ ከመስሪያ ቤቱ ሃላፊዎቹ ጋር በመሆን የግዥ ውል በማፅደቅ 10 ሚሊየን 670 ሺህ 184 ዶላር በማውጣት፥ ኖሮኮን ከተባለው የቻይና ኩባንያ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ግዥ በህገ ወጥ መንገድ እንዲፈጸም በማድረግ መንግስት ከጨረታ ውድድር ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅም በማሳጣት ከግዥ መመሪያ ውጭ አለም አቀፍ ጨረታ ውድድር ሳይደረግ ከመስሪያ ቤቱ ሃላፊዎች ጋር በመሆን የግዥ ውል በማፅደቅ 660 ሺህ ዶላር በማውጣት፥ ዳኑቢያን ኤርክራፍት ከተባለ አለም አቀፍ ድርጅት የአገልግሎት ግዥ በህገ ወጥ መንገድ እንዲፈጸም በማድረግ መንግስት ከጨረታ ውድድር ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅም በማሳጣት፤ ሜቴክ ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ከ13 በላይ አለም አቀፍ ኩባንያዎችን ያለምንም ጨረታ እና ውድድር በሰላሳ የተለያዩ የውል ስምምነቶች ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ ግዥዎች እንዲከወኑ ተደርጓል፤ ተጠርጣሪው እነዚህ ውሎች ውስጥ ለጊዜው የተረጋገጠ 15 የሚሆኑ ውሎችን አፅድቀዋል እንዲሁም ተፈራርመዋል።

የእርሳቸው #ወንድም የሆኑት አቶ ኢሳያስ ዳኘውን የተጠረጠሩባቸውን የሙስና ወንጀሎችም ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል። በዚህም ግለሰቡ የኢትዮ ቴሌኮም የኤን ጂ ፒ ኦ ፕሮግራም ዳይሬክተር ሆነው ሲሰሩ ለሜቴክ በሶማሌ ክልልና በባሌ ዞን የሞባይልና ሲ ዲ ኤም ኤ ሳይቶች ግንባታ ስራ፥ 204 ሚሊየን 981 ሺህ 630 ብር የተደረገው ውል ስራው ሳይጠናቀቅ ቫትን ጨምሮ 322 ሚሊየን 628 ሺህ 124 ብር ከ55 ሳንቲም ክፍያ እንዲፈጸም ለፋይናንስ ደብዳቤ በመጻፍ ደረጃውን ያልጠበቀና ጥራት የሌለው ስራ እንዲሰራ በማድረግ፣ እንዲሁም ስራው ሳይጠናቀቅ የመጀመሪያውን ውል በማሻሻል የቴሌ ታወር ግንባታና ተከላ ስራ 321 ሚሊየን 710 ሺህ 424 ብር ከ55 ሳንቲም ውል በማሻሻል ለሜቴክ በመስጠት የተጠረጠሩ ናቸው ብሏል።

ከዚህ ባለፈም በአቶ #ተስፋዬ_ኡርጌ_ላያ ባደረገው ምርመራ ተጠርጣሪው ፈጽመዋቸዋል ያላቸውን ድርጊቶች በጽሁፍ አቅርቧል፤ በዚህም ግለሰቡ የተለያ ሰዎችን የኦነግ ድርጅት አባል ናቸሁ በማለትና ያለአግባብ እንዲታሰሩ በማድረግ በስውር እስር ቤት በማሰርና በማሰቃየት እንዲሁም በማስፈራራት ከሌሎች ግብረ አበሮቻቸው ጋር 6 ሚሊየን ብር እና 22 ሺህ ዶላር በመቀበል ለግል ጥቅማቸው አውለዋል ሲል ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

የደረሰውን ጉዳት ኦዲት ማስደረግ፣ ያለጥቅም የተቀመጠውን ፋብሪካ ያለበትን ደረጃ የባለሙያ ቃል መቀበልና የምስክሮች ቃልን መቀበልን ጨምሮ ሌሎች ቀሪ ስራዎች እንዳሉትም ለችሎቱ አስረድቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikahethiopia