TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

ከኬንያ ጤና ሚኒስቴር መግለጫ ፦

- በ24 ሰዓት የ300 ሰዎች ናሙና ምርመራ ተደርጓል።

- ምርመራ ከተደረገላቸው መካከል ሀያ ሁለቱ (22) ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጧል።

- ቫይረሱ የተገኘባቸው 13 ወንዶች 9ኙ ደግሞ ሴቶች ናቸው።

- 18 ኬንያውያን ፣ 2 የፓኪስታን ዜጎች፣ 2ቱ ደግሞ የካሜሮን ዜጎች ናቸው።

- ከ22ቱ የቫይረሱ ተጠቂዎች ሀያ አንዱ (21) ኳራንታይን ላይ ያሉ ናቸው።

- በኬንያ ዛሬ ሪፖርት የተደረገው የ22 ሰዎች የኮቪድ-19 ፖዘቲቭ ኬዝ በአንድ ቀን የተመዘገበ #ከፍተኛው ቁጥር ሆኗል።

- በተመሳሳይ በአንድ ቀን ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥርም እስካሁን ከታየው ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MutahiKagwe

በኬንያ በአንድ ቀን 66 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተረጋገጠ!

በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ ስድስት (66) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። እስካሁን ከተመዘገቡት የአንድ ቀን ኬዞች #ከፍተኛው ነው። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 1,029 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኬንያ ውስጥ በአንድ ቀን 80 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋገጠ!

በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3,102 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ (80) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

እስካሁን ከተመዘገቡት የአንድ ቀን ኬዞች #ከፍተኛው ነው። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 1,109 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት ተጨማሪ ስድስት (6) ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 375 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ስርጭት በእጅጉ እየጨመረ ነው!

ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ 100 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህ ቁጥር ወረርሽኙ ሀገራችን ከገባበት ጊዜ አንስቶ የተመዘገበ #ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

94 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ናቸው፤ ከነዚህ 94 ሰዎች መካከል 60 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው ናቸው። የቀሩት 34 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው ናቸው።

ሌላው ከአዲስ አበባ ውጭም የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ሳይኖራቸው በቫይረሱ መያዛቸው የሚረጋገጥ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።

ዛሬ ብቻ በኦሮሚያ ክልል በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠ 3 ሰዎች መካከል ሁለቱ (2) የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።

ከዛሬዎቹ አንድ መቶ (100) ሰዎች መካከል አንድ (1) ሰው ከትግራይ ክልል (በለይቶ ማቆያ ያለ) እንዲሁም ሁለት (2) ሰዎች ከሱማሌ ክልል (በለይቶ ማቆያ ያሉ) ይገኙበታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

ባለፉት 24 ሰዓት የተመዘገበው በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወረርሽኙ ወደ ሀገር ከገባ ጀምሮ በአንድ ቀን የተመዘገበ #ከፍተኛው ቁጥር ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 22 (8 ከጤና ተቋም እና 14 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Alert😷

በኢትዮጵያ የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር 591 ደረሰ።

ዛሬም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከገባ ጊዜ አንስቶ #ከፍተኛው የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ተመዝግቧል።

ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 5,338 የላብራቶሪ ምርመራ 1,490 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 18 ሰዎች ሞተዋል።

ትላንት 660 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 178,108 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,573 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 144,488 ሰዎች አገግመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Alert😷

በኢትዮጵያ የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር 600 ደረሰ።

ዛሬም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከገባ ጊዜ አንስቶ #ከፍተኛው የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ተመዝግቧል።

ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 8,055 የላብራቶሪ ምርመራ 2,057 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 10 ሰዎች ሞተዋል።

ትላንት 330 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 181,869 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,602 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 145,349 ሰዎች አገግመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ዳግም የሀገራችንን ስም በዓለም ከፍ ያደሩጉት ወጣቶች !

ላለፉት 6 ተከታታይ ቀናት በኮሎምቢያ ካሊ የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሲካሄድ ሰንብቷል።

በዚችም ሀገራችን በ19 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በ10 የውድድር ተግባራት ብቻ ተሳትፋለች።

የአትሌቲክስ ቡድናችን በሻምፒዮናው ፦

🥇6 ወርቅ፣
🥈5 ብር
🥉1 ነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎች በማግኘት ከዓለም ሃገራት አሜሪካንን እና ጃማይካን በመከተል 3ኛ ደረጃን ይዘን አጠናቀናል።

የተመዘገበው ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪካችን ዘንድሮ #ከፍተኛው ውጤት ነው።

ከተሳተፍንበት ውስን የውድድር ተግባራት አንፃር እጅግ የሚያኮራ ውጤት ነው።

ሜዳሊያ ያስመዘገቡ የነገዎቹ የሀገር ተስፋዎች እነማን ናቸው ?

#ወርቅ

🥇ኤርሚያስ ግርማ (800 ሜትር)
🥇መልክነህ አዘዘ (3000 ሜትር)
🥇አዲሱ ይሁኔ (5000 ሜትር)
🥇ሳሙኤል ዱጉና (3000 ሜትር መሰናክል)
🥇 ብርቄ ሀየሎም (1500 ሜትር)
🥇መዲና ኢሳ (5000 ሜትር)

#ብር

🥈ኤርሚያስ ግርማ (1500 ሜትር)
🥈ሳሙኤል ፍሬው (3000 ሜትር መሰናክል)
🥈ፅዮን አበበ (3000 ሜትር)
🥈መልክናት ውዱ (5000 ሜትር)
🥈ሲምቦ አለማየሁ (3000 ሜትር መሰናክል)

#ብር

🥉መሰረት የሻነህ (3000 ሜትር መሰናክል)

እንኳን ደስ አለን አላችሁ !

ይቀላቀሉ : @tikvahethsport
https: //t.me/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia